|
Saturday, 22 September 2007 |
|
ልደት ሞት መሆኑን እሱው ገልጦልናል
ንቡት ዝንብን ስትሆን እራሱ አሳይቶናል፤
ጴጥሮስ ክዶ ሲምል በብያኔ አሳይቶ
መራራው ባቋሙ በሬትነት ፀንቶ
ኃይል ከኃይል ጋር ለእውነት ትግል ገጥሞ
አሳይቶን ነበረ ስንቱን አወሳልቶ
ስንቱን አንበሳ አርጎ
ጊዜን እየቸረ ጊዜ ጊዜን ሰጥቶ፤
አሁንም አልበቃው ጊዜ ጉድ ማውጣቱ
ብርሃን ፀልሞ መሽቶ እየጠቆረ
የብርቱካኑ ዛፍ አሜኬላ ሆነ፤
የብርሃን ውላጅ ጨለማው ሲዳፈን
እሾህ አሜኬላው ይተናኮስ ጀመር፤
ፎልፎሌው የውሃ እናት
የባሕር ዳሩ ዐባይ
ወንዙን ላለት ትቶ
ለዱር አውሬ መርቶ
ሕዝቡን ጣናን ከድቶ
እጅ ወደ ላይ አለ
ውሃውን ነጠፈ፤
ያዕቆቡ እሥራኤል
ምድረ ምሥር ቃሊቲ ከበረሃ ገብቶ
ንግሥና አማለለው
አገሩን ወገኑን እሥራኤልን ከድቶ፤
አርአያ ሁን ብለው ኃይልን ቢጠይቁ
ይሻለኛል አለ መለየት መውጣቱ
አርአያ ከመሆን ብልጣ ብልጥ መሆኑ
ከኃይል መራቁ፤
ግዛ እሚል መጠሪያ እናት ቢሠይሙ
ልጅን በስተርጅና ሸወደው ትርጉሙ
ስም የግብር ብሎ ሊደርስ ከግቡ
እሱም ተደመረ ከክሁድ ሽምቁ፤
እንግዲህ በል ፎልል የሴራው አርበኛ
አሐዱ ተብሏል የዱለታህ ትልሚያ፤
የሕዝብሕ ምህላ አንድ አርግ ነበረ
አደራህን በልተህ ግብርህ በትን ሆነ?!
እንግዲህ በል ጠንክር ቀረርቶው ይቆይህ
ኃይል ከሕዝብ ጋር
ኃይልም የሕዝብ ነው
የብተናው መረብ መና ቀርቶ ሲቋጭ
ኋላ ሲጸጽትህ
ቀረርቶውን ያኔ ከቅሌትህ ጋራ በእንባ ታዜማለህ፤
ጊዜ ዛሬን ሲገልጥ በዚህ መሰል ፊልሙ
ለነገም ስንቅ አለው አይጎድልም ጉድጓዱ፤
ዋ ጊዜ ሸውራራው
ዋ ጊዜ ገልባጣው
ዋ ጊዜ ጣይ ጥላው
ጊዜ ወላ ዋዩ
ጊዜ መስታወቱ
ስንቱን ያሳየናል በነጋ በጠባው!
ነገ ተነጎዲያስ ደሞ ምን ይኖረው?!
|