RSS 2.0 Email us: webmaster@mahder.com

Ethiopia: Mahder.com -Ultimate Ethiopian News and Information Portal

Saturday
Nov 22nd
Home arrow News arrow ለምትሰሩት ስህተት ሁሉ ህዝቡ ምን ይላችሁ መሰላችሁ?
ለምትሰሩት ስህተት ሁሉ ህዝቡ ምን ይላችሁ መሰላችሁ? Print E-mail
Friday, 05 October 2007

በቅንጅት ስም ለምትሰሩት ስህተት ሁሉ ህዝቡ ምን ይላችሁ መሰላችሁ?

አደብ ግዙና ጠላት መሳቂያ ሳያደርገን ቆም ብላችሁ አስተውሉ ሰድባችሁ ለሰዳቢ አትስጡን

ስጋችሁን በጎመን አትለውጡ

                                  ሳተናው ቀበሮ

                                    ከአዲስ አበባ

        በቅርቡ ጆሮ አልሰማው አይል የሆነበት በግንቦቱ ምርጫ የመረጥናቸው አመራሮቻችን በግፍ ከታሰሩበት ወህኒ እግረ ሙቁ ወልቆላቸው ከእስር እንዲወጡ ብርቱ ትግል ያደረገውን በውጭ ነዋሪ ወገንና የውጪ ተወላጆችን ለማመስገን ባህር ማዶ ከሄዱ በሁዋላ በመካከላቸው ተፈጠረ እየተባለ ስለሚራገበው ወሬና እንዲህም እንዲሆን መንገዱን ላሳዩ፤ ላመላከቱ ስለሆነው ሁሉ እኔ ጸሃፊው ቅር ስለተሰኘሁባቸው አንዳንድ አመራር አባላት የተሰማኝን ለመግለጽ አስቤ ፤ያሰብኩትን በማድረጌ ይህ እውነት በዚህ ለመላው ህዝባችን አማራጭ የመረጃ ምንጭ በሆነ ሬዲዮ ይተላለፍ ይሆን? ወይንስ ይስተጉዋጎል ይሆን? የሚለው ነበር ፍርሃቴ

 

ምክንያቱም ይህ ነገር መራገብ በያዘበት ሰሞን ለማንም አለማድላቱን ልብ ይሉዋልና ነው የእኔን የግለሰቡን ነጻ አስተያየት ያፍንብኝ ይሆን ወይ? የሚለው የሚያሰጋኝ አንሶ ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በዚያ ሰሞን ይህ የህዝብ ልሳን አይንና ጆሮ የሆነው ሚስጥር አያመልጤ የሆነው ሬዲዮ ሰማይና ምድርን እማኝ አድርጎ ለማንም በምንም ሁኔታ የሚያደላ አለመሆኑን ማረጋገጡን ሰማሁና ምን አልባት ይህ ነጻ የሆነው ከማንም በምንም ሁኔታ ያልተጣባ አስተያየቴ ወገንተኛነት ይንጸባረቅበታል ብለው የቅርጫት እራት ቢያደርጉትስ? የሚለው ሃሳብ እየተደጋገመ እየመጣብኝ ፍርሃቴን ጨመረው

      

   በመቀጠል ለዚህ ሃሳቤ መንደርደሪያ እንዲሆነኝ ሳነብ ያገኘሁትን የፖለቲካ ፓርቲዎች አጀማመርና ውህደት ላይ ያላቸው ፍርሃት መተባበራቸውን እየነሳ አንጃዎችን ሲያበቅሉ ከተስተዋሉበት የትናንት ታሪካችን ጠቀስ አድርጌ ለማዋዛት እሞክርና ወደ ዋናው ቁም ነገር አልፋለሁ

        ግርማዊ ቀዳማዊ /ሥላሴ  በሥልጣን ዘመናቸው  ለኢትዮጵያ  ሕዝብ  ሊያከብሩለት፣  ሊጠብቁለት ከሚገቡት    መብቶቹ አንዱ በሕግና  በደንብ ተደራጅቶ፣   ፓርቲ  አቃቁሞ   በሐገሩ የመንግስት  አስተዳደር    እንዲሳተፍ   ማድረግ ነበር፡፡    

ይህን  አለማድረጋቸው መንግስታቸውን   ለረዥም  ጊዜ  ለተካሄደ መፈንቅለ  መንግስት   እንዲጋለጥ፣   ለእሳቸውና   ብዙ የንጉሱ ባለሥልጣናት   መረበሽ፣  ከዚያ  ጊዜ ጀምሮ    ላለው  የአገራችን   የፖለቲካ ሁኔታ መመሰቃቀል ምክንያት ሆኗል ብለው የሚያስቡና የሚናገሩ ሰዎች መኖራቸውን በተለያየ አጋጣሚ ስንሰማ ነበር

  እውነትም በንጉሱ   አገዛዝ ዘመን የፖለቲካ  ፓርቲዎችን  ማቋቋም   ተችሎ  ቢሆን  ኑሮ፣ ሕዝቡ ስለ ፓርቲ   አሰራርና   አመራር  የተሻለ    ልምድ ይገነባ እንደነበር ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡

የፖለቲካ    ፓርቲ  አመሰራረትና አሰራር ባልታወቀባት   ባልተለመደባት  ኢትዮጵያ፣ 1966  ዓም የካቲት  ወር የፈነዳው  ሕዝባዊ አመፅ   የሚመራወ የተደራጀ  ክፍል ባለመኖሩ   የተጓዘው በስሜትና  ፍላጐት እንደነበር እና አጋጣሚውን ተጠቅሞ ከአስተባባሪነት   ወደ መንግስትነት   ከፍ ከፍ እያለ  የመጣው ደርግ መንግስት   የሆነው እሱም  ደጋግሞ    እንደተናገረው  ቤቱ ወይም   መስመሩ  ባዶ  ስለነበር  ነው፡፡    የነፃነት  ግንባሮች  ሆኑ  በሐገራችን   የፖለቲካ    ፓርቲ   ታሪክ  ውስጥ  በቀደምትነት  የሚጠቀሱት ኢህአፓ መኢሶን፣ ኢጭአት፣ ኢኮፓ  ወዘተ ሁሉም  የፖለቲካ  ልምዳቸው ከተማሪ ቤት ህይወታቸው የጀመረ ስለመሆኑ የሚተርኩልንም የዚያን ዘመን ትውልዶች አሉ

የዚያን ግዜ የፓርቲዎቹ ምስረታ በሕግ በተፈቀደ  መንገድ ባለመሆኑ በህቡና    በአመፅ በመሆኑ አንድ  አይነት   አስተሳሰብ  አንድ አይነት   የትግል መሥመር ላይ   ቁመው   በመካከላቸው  መተባበርና  መዋሐድ    ሳይፈጥሩ ሁሉም   እኔ ነኝ ትክክል እንዳሉ፣  ያንን ለውጥ   ዘመን ያሳለፉ   ፓርቲዎች   መሆናቸው ዛሬ ላለንበትና ለደረስንበት የፓርቲዎች እንተባበር እንቀናጅ የማለት የመተባበር መንፈስ አስተምህሮት ሰጥቶ አልፎዋል

    ፓርቲዎቹ በግልፅ  በአደባባይ  በሕጋዊ መንገድ   የተቋቋሙ  ባለመሆናቸው  እያንዳንዱ አባል  የሌላውን  ፓርቲ   አባል  ማወቅ የሚችልበት  መንገድ   እምብዛም   ባለመኖሩ፣ አንድ ሰው የሁለት  ፓርቲዎች   አባል የሚሆንበት   ሁኔታ  ይፈጠር ነበር

  ይህ አይነቱን   አጋጣሚ  በመጠቀም   የአንደኛው   ፓርቲ አባል በሌላኛው   ፓርቲ  ውስጥ  ችግር አስከትሏል፡፡ ይህ  ብዙ    ፓርቲዎች   ውስጥ ከፍተኛ   ጥፋት   እንዲከተል    ከማድረጉ   በላይ፣  ፓርቲዎች እርስ በእርስ እንዳይተማመኑ   የሚያደርግ    መጥፎ  ልማድ    ተክሎ አልፏል፡፡   

ኢህአዴግ 1983 ዓም ከጫካ አዲስ አበባ ገብቶ የመንግስት ሥልጣን ከያዘ  በኋላ  ያፀደቀው    ቻርተር   የመደራጀት መብት ስለሚፈቅድ በሐገር ውስጥ  በርካታ  የፖለቲካ  ድርጅቶች   እንዲመሰረቱ  መንገድ  ከፍቷል፡፡    እጅግ  ብዙ   የብሔረሰቦች   ጥቂት  የብሔር  ድርጅቶችም  ለመመሥረት ችለዋል፡፡   እንደ ወላይታ፣   ከምባታ፣ ሐድያ፣   ሲዳሞ፣  አፋር  ቤንሻንጉል  ወዘተ ባሉ ብሔረሰቦች  ስም የሚንቀሳቀሱ ሁለት   ፓርቲዎች  እየተፈጠሩ   በመምጣታቸው  የፖለቲካ   ትግሉን   ይብስ አደጋ ላይ  መጣል  ጀመሩ፡፡ ሕዝብ  ላይ   ተቃውሞ በመሰማቱ  የመተባበር ጥያቄ እየጐላ መጣ፡፡  የደቡብ   ሕብረትና የአማራጭ  ኃይሎች    ምስረታ ከተቃዋሚዎች  በኩል የሚጠቀስ  ሲሆን፣   በኢህአዴግ በኩል ደግሞ የኢህአዴግ መመሥረት የሚታወስ  ነው፡፡ ምን አልባትም ወያኔ  ሥልጣኑም ጉልበቱም ስላለው ሊሆን ይችላል፡፡   በጋምቤላ፣  በቤንሻንጉል፣ በአፋር ወዘተ  የነበሩ የተቃዋሚ   የብሔር  የፖለቲካ  ድርጅቶች  ብዙዎች ከኢህአዴግ ተዋህደው አጋር ድርጅት ሆነዋል

በተለይ 1993  ዓም   ወዲህ የተለየ   የተቃዋሚ    ፓርቲዎች  ውህደቶች የሚያረካ  ውጤት ማሳየት    ባለመቻላቸው   «ተባበሩ ወይም ተሰባበሩ»  የሚል ሕዝባዊ   ተቃውሞ ከዳር   ዳር ተቀሰቀሰ፡፡ 1997 ዓም  ምርጫ ላይ ከስልሳ   ያላነሱ የብሔርና የሕብረ  ብሔር ድርጅቶች  ለውድድር   ቢቀርቡም፣ ሕዝብ ድምፅ   የሰጣቸው    ለአራት ድርጅቶች  ብቻ ነው፡፡  እነሱም ቅንጅት፣ ኢህአዴግ፣  ሕብረትና