RSS 2.0 Email us: webmaster@mahder.com

Ethiopia: Mahder.com -Ultimate Ethiopian News and Information Portal

Friday
Nov 21st
Home arrow News arrow ምን አልባት ..ይህንንም በጭብጨባ ይቻል እንደሆነ እንጂ...
ምን አልባት ..ይህንንም በጭብጨባ ይቻል እንደሆነ እንጂ... Print E-mail
Wednesday, 10 October 2007

ከእንግዲህ ለሚፈጠረው ግጭት ጥይት ማብረጂያ እሆናለሁ ብሎ የሚነሳ ኢትዮጵያዊ መገኘቱና ከኢህአዴግ ጋር ጎን ለጎን ይቆማል የሚል የተሳሳተ ሂሳብም ለውርደት ይዳርጋል

ምን አልባት ..ይህንንም በጭብጨባ ይቻል እንደሆነ እንጂ...

ሣተናው ቀበሮ

ከአዲስ አበባ

      መቼም ግዜ ሢያልፍ እንደዘበት ማውጋቱ አይቀሬ ነው እንዲህ ያለውን ወግ ደግሞ ጣፋጭም ሆነ መራር የሚደርገው ዛሬ ላይ ተሁኖ እንዲታወስ ምክንያት የሆነው አጋጣሚ ነው

     እንዲህ አይነቱን ወግ ዛሬ እናወጋለን ለዚህም ከትናንቱ ጋር እያመሳሰልን ትናንት አልፎ አውግቼው ያልንበት ርእሰ ነገር የዛሬ አጀንዳ ሆኖ ሲታይ ቢገርመን አግራሞታችንን ብንነጋርበት ምን ይለናል?

 

      በዚያን ሰሞን ቁንጮው መለስ ዜናዊ አንድ ስብሰባ ጠሩ የወጣቶች ስብሰባ  ከመላው አገሪቱ በኢህአዴግ ቸርነት ሆዳቸውን ያስገዙ አንዳንዶችም በነገው ተስፋቸው የዋህ አስተሳሰብ ይዘው ተሰበሰቡ ልክ እንደ ኢሰፓው ግዜ

       የዚያን ግዜ የኢሰፓ   አባላት    ከየአቅጣጫው    አዲስ አበባ   እየተሰባሰቡ  የሚያደርጉት ስብሰባ በጭብጨባ  ተጀምሮ በጭብጨባ  ታጅቦና   ጐልቶ   በጭብጨባ    ይዘጋ  ነበር፡፡

      ጓድ  መንግስቱ   /ማርያም  ጥቂት    ዓረፍተ ነገር  ነገሮችን   ጣል  ሲያደርጉ  ጭብጨባው ነበር  የሚያቋርጣቸው ፡፡ ጓድ  መንግስቱ  /ማርያም   ወደ ጉባኤው   አዳራሽ   ሲገቡ   የሚጀምረውና የማያቋርጠው   የተሰብሳቢዎቹ  ጭብጨባ  እሳቸው የሚያነቡት    የእያንዳንዱ   መስመር ንግግር   በአዳራሹ   በተገኙ   ተሰብሳቢዎች  ጭብጨባ  እየቀጠለ እየተገታ እሳቸውም  ትንፋሻቸውን  እያሰባሰቡ   በጭብጨባ  እየታጀቡ እንደነበር  አንዘነጋውም

    ኢህአዴግ  ከጫካ አዲስ አበባ ከገባ  ወዲህ   ግን በጭብጨባ   በተሞላ  ስብሰባ ስናይ    ኖረን    በዚያን ሰሞን ቁንጮው መለስ ዜናዊ ከወጣቶች  ጋር ያደረጉት  ስብሰባ በየሰኮንዷ ሽርፍራፊ  ይካሄድ   የነበረው ጭብጨባ   ሪከርዱን   ለመስበሩ   እርግጠኛ ሆኖ   መናገር የተቻለበት አጋጣሚ ነበር

      ቁንጮው መለስ ዜናዊ  በየትኛውም  አቅጣጫ    የሚቀርብን  ጥያቄ ሸፋፍኖና አለባብሶ ወይንም አደናግሮ የመመለስ   ክህሎት   የተላበሱ ሰው በመሆናቸው ቁጥራቸው 6 ይሆናሉ የተባሉትን ወጣቶችን ልብ ለማማለል የወረወሩዋት እያንዳንዷ  ሐረግ   በከፍተኛ  ጭብጨባ   ነበር    የምትቋረጠው የማያስጨበጭብ ሁሉ  ያስጨበጨበበት ስብሰባ  ነበር፡፡

      « .  .  .   ሆድ  መሙላት  ስለተጀመረ   ለመዝናናትና   ስፖርት ለመስራት    በቂ ትኩረት  መስጠት   የምንገደድበት  ትንሽም  ቢሆን  ገንዘብ ለዚህ  ሥራ   መመደብ የምንችልበት  ሁኔታ  ተፈጠረ . . .»አሉ ቁንጮው ሰውዬ

        ከእሳቸው የተሰብሳቢዎቹ ከተሰብሳቢዎቹ የእሳቸው መሳቂያ መሆን ግን አገር ሁሉ አንገቱን እንዲደፋ ያደረገ ክስተት ነበር ለምን አትሉም አድማጮች?

    ስራ አጡ ወጣቱ ነው አደገኛ ቦዘኔው ወጣቱ ነው መሄጂያ ስፍራ ያጣው ወጣቱ ነው እየተባለ ስራ አጥ መሆኑ እየተነገረው ስራ ከሌለው የሚበላው ከቤተሰቡ ጉሮሮ እየተካፈለ እንጂ ሰርቶ በሚያገኘው ገንዘብ አለመሆኑ በግልጽ እየተነገረው ጥቂት ወረድ ብሎ ደቂቃዎች በሰአታት ከተለወጡ ቅጽበት በሁዋላ አሁን ሆድ መሙላት ጀምሮዋል ብለው የእነሱን የአራት ኪሎ ቤተ መንግስትን የኑሮ ሁኔታ በግልባጭ አሳይተውት እንደእነሱ ቁንጣናም የሆነም መስሎዋቸው አሉት

         እንዲህ በሞራሉ ላይ እየተረማመዱ ልክ ልኩን ሲነግሩት ተሰብሳቢው ሞቅ ያለ ጭብጨባ አስከተለ በእፍረቱ የሚዝናና ትውልድ ያሉት አንድ አባት ይህን አጋጣሚ አስተውለው ንድድ ብሎዋቸው ነው

            ከዚህ  ጥያቄ  የቁንጮው መለስ ዜናዊ ምላሽ  በፊት ከወጣቶቹ የተጠየቀው የሥራ አጥነት  ችግር መላ  አገሪቱ በተለይም በወጣቱ ላይ  መንሰራፋቱን በእሮሮ መልክ የቀረበ ነበር፡፡ የገጠሩ   ወጣት ችግር   ምንጩ መሬት መሆኑን በመግለፅ   መልሳቸውን ጀመሩ፡፡

       የገጠር መሬት   በወጣቶች   ወላጆች  መያዙን  ጠቁመው በወላጆቹ የተያዘውን መሬት   እንደገና በጣጥሰን   እንስጥ ብንል መሬቱን  ከመበጣጠስ አልፎ   የሚያስገኘው  ልማት     አይኖርም፡፡   መሬቱን   ሳናከፋፍል ስንቀር  ደግሞ ወጣቱ  መሬት  ስሌለው በግብርና  ሥራ ላይ በብቃት  ለማሰማራት   ችግር    ያጋጥመው ይሆናል፡፡    ስለዚህ የገጠሩን   ወጣት ችግር   ለመፍታት  አንዱ መሠረታዊ ጥያቄ መሆን  ያለበት   የመሬትን ጉዳይ  በምን  መልኩ ነው የምንቀርፈው  . . .  እያሉ በባዶ ሜዳ መፍትሄ አልባ ንግግር በማድረግ ለማደናቆር ሞከሩ እንዲህም ሲደናቆር ለደናቁርትነቴ ምስጋና ይግባኝ ያለ ይመስል ያጨበጭባል

      የመሬት  ችግር  ካለ    አብዛኛው  የገጠር ወጣት ያለሥራ  እንደሚኖር ከታወቀና ይህም በዚሁ መድረክ  ላይ ተገልፆ  እያለ ነው ቁንጮው መለስ ዜናዊ «ሆድ እንዳይሰፋ ስፖርት » የሚለውን  ንግግራቸውን  ያስከተሉት፡፡

      የሚበላ   እንደማይኖር   በተነሱት ሃሳባቸው ግንዛቤው የነበራቸው የወያኔው መሪ ወጣቱ ይኑረን   ብሎ የጠየቀው የመዝናኛና  የስፖርት ማዘውተሪያ  ስፍራን የተመለከተ ጥያቄ መልስ ነው ብለው የሰጡት ሚስድ ኮል ይመስላል

     ሚስድ ኮል ተንቀሳቃሽ ስልክዎ ለወጪ ጥሪ የሚያገልግል ገንዘብ ሳይኖረው በቀረ ግዜ የሚፈልጉት ሰው ወደ እርስዎ እንዲደውልዎ የእርስዎ ቁጥርን ደውለው አጥፍተው ይደወልልኛል ብለው በተስፋ የሚጠብቁት ጥሪ ነውና ልክ ይህን ሂደት በሚመስል መልኩ የስፖርት ስፍራ ብሎ ለቀረበ ጥያቄ የተሰጠው  ሆዱ እንዳይሰፋ  ስፖርት  ሊሰራ እንደሚገባ መናገር እና በጥጋብ የተቸገረ አስመስሎ ስፖርት መስራትን ተገቢ ነው ማለት ሚስድ ኮል ነው ያልኩዋችሁ እንዲህ ያለው  ማስጠንቀቂያ የሚጠቁመው  ዘርፈ ብዙ ችግር አለብን ለዚያውም  ብዙ  ዘመን የሚዘልቅ ስለዚህ ስለሆዳችሁ አታስቡ ድሮ እንዳልኩዋችሁ በቀን ሶስት ግዜ አትበሉም ችግሩ ጠና ኑሮ ተወደደ ለኤርትራና ለሶማሌ መጋጠሚያ ገንዘቡንም የጦር መሳሪያ ገዛንበት እናም ለሆድ  ፊት አትስጡት የማለትን ያህል ይመስላል፡፡

      «ወጣቱ    ትኩስ  ኅይል  ነው፡፡  ወጣት የነብር  ጣት» የሚባሉት  ማሞካሻዎችን ብቻ  እየሸለሙት በደመ ነፍስ የሚኖርን   ወጣት   ፈልፍለው   ለዚህ  ያበቁት ያለፉ መሪዎች    የስተማሩን   ሽወዳ ቢኖርም፣ አሁን ደግሞ   በአዳራሽ