| ያመኑት ፈረስ ይጥል በደንደስ እንዲሉ(ሳተናው ቀበሮ) |
|
|
| Thursday, 06 December 2007 | |
|
ከአዲስ አበባ
መቼም ዘንድሮ የማይሰማ ነገር የለም አንዳንዴ በምንሰማው ነገር ሁሉ ዘና ማለታችን እንዳለ ሆኖ አንዳንዴ ደግሞ ቆሽትን እርር ድብን የሚያደርግ ይሆንና መፈጠራችንን እስከ መርገም ደረጃ ላይ የሚደረስበት አጋጣሚ መኖሩ እውነት ነው በተለይ በግንቦቱ የሶስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ ግዜ ለሊት በውድቅት ጨለማ ከመኝታችን ተነስተን የምንፈልገውንና የምናምንበትን ድርጅት መርጠን አመራሮቻችንን ሰይመን በድምጻችን መድፍ የማንፈልገውን አንደባለን ጥለን ነበር
በዚህ አልቆምንም አምባገነኖች መቸነፋቸውን ባወቁ ምሽት ጣታችሁ ይቆረጣል ሲሉን አልፈራንም አለመፍራታችን ለእነሱ ፍርሃት ሆኖ መራድ የጀመረው ሰውነታቸውን ለማቆም ሲሉ ጠብ መንጃ በታጠቀ ሰራዊታቸው በአደባባይ እንድንገደል አደረጉና ጠንከር ያለ ትእዛዝ ሰጡ ያሉትንም አደረጉ ህጻን አዛውንት ሳይቀር በአደባባይ ተገደሉ አመራሮቻችንም ወደ ወህኒ ተጋዙ ..በቃ.. ያመንናቸው ሲከዱን ፤የጠበቅናቸው ሲቀሩብን ፤የወደድናቸው ሲጠሉን ፤አየን እውነትም ያመኑት ፈረስ ይጥል በደንደስ የሚለውን የቆየ የአበው ብሂል መጥቀሱና አስረግጦ መነጋገሩ አስፈላጊነቱ ከመቼውም ግዜ ይበልጥ ግዜው ዛሬ መሆኑ ይሰማኛል ያመንናቸው እና የመረጥናቸው አንዳንድ አመራሮቻችን ድራማቸውን መተወን ከጀመሩበት ግዜና ሰአት መነሳት ግን ለሃሳባችን ፍሰት መሰረት ይሆናል ወያኔ በግፍ አስሮ መሰረተ ቢስ ክስ አቅርቦ በገንዘብ እና ሸራ ጫማ እየገዛ የደለላቸው አባላቱና ሆድ አደር ምስክሮቹ ራሱ በሚያዝበት ፍርድ ቤት እያቀረበ ውንጀላውን ሲያጡዋጡፈው በነበረ ግዜ በተለይ ይህ ሬዲዮ ጣቢያ እስራታቸውን ታስሮ ፤ ህመማቸውን ታምሞ ፤ ስቃያቸውን ተሰቃይቶ ፤ በእነሱ ላይ የሚያርፈው የወያኔ ዱላ እያመመው መሪዎቻችን ይፈቱልን ጩኸቱን ለ20 ወራት አሰማ ህዝብ በመረጥከው መሪዎችህ ላይ እንዲህ ሲደረግ ዝም አልክ? መርጠህ ወደሞት ሸኘሃቸው? እያለ ጠየቀ ታሪክና ትውልድ ሊፈርዱት እና ብድራቱን ይክፈሉት እንጂ ጣቢያውና መላው የዝግጅቱ ተሳታፊዎች ያላሰለሰ ጥረት አድርገው የህዝብን የትግል ስሜት ሳይበረዝ በወያኔ ከንቱ ፕሮፓጋንዳ ሳይታለል እና ሳይዘናጋ በሆድ አደር የጥፋት ተላላኪዎቹ እኩይ ድርጊት ሳይሸነፍ መሪዎቹ በሰላምና በጤና ከወያኔ ወህኒ ቤት እንዲወጡ በተደረገው አድካሚ ትግል ውስጥ ግንባር ቀደም ሚና ተጫውቶዋል በእርግጥም ህዝብ መርጦዋቸው የታጠቁ አምባገነኖች በግፍ ያሰሩዋቸው የህዝብ መሪዎች ከእስራት ወጡ ህዝቡም በእጅጉ ደስ ተሰኘ ግን ደስታውን በወጉ ሳያጣጥመው ሌላ ችግር ገባው ያልታደለ በተለይ መሪ አታግኝ ተብሎ የተረገመ ይመስል አንድ ትውልድ እምሽክ አድርጎ ከበላው ከደርግ አገዛዝ መባቻ ጋር በተያያዘ የፖለቲካው ታሪኩ በእንጥልጥል የቀረበት ተብሎ ጣት እንዲጠቁዋቆምበት ያስቻለውን ጉድፍ ማየት ቻለ ቅንጅትን ያህል በህዝብ የተመረጠ ድርጅት ቀርቶ አንድ እድር እንኩዋን የራሱ ወግና ደንብ አለው አቶ እገሌ ሊቀመንበሩ ሆነው ሌላው እንደፈለገው የሚንቡዋችበት እድል ከቶ የለም ሊቀመንበሩ በሌለ ግዜ ምክትሉ መሸፈኑ ግድ ነው ቢሆንም ሊቀመንበሩ በህይወት እንደሌሉ ያክልን በራስ ፍላጎት ቡድን አቡዋድኖ ባህር ማዶ በመሻገር እሰጥ አገባ መግጠም ከምሁራን ኤሊቶች የጠበቀ መሃይም አልነበረም ህዝቡ ማንን ጠርጥሮ ? የሆነውና የተሰማው ሁሉ እንዲያው በግርድፉ የአጋጣሚ ክስተት እንጂ እንዲህ ስር የሰደደ ነው ብሎ የገመተም አልነበረ ችግሩ ግን እየቆየ እዚያው እርስ በእርስ በሚደረግ የቡድን ፍጭት እየተለየ መምጣቱን ምን ተባለ ? ብሎ ለሚያነፈንፍ እፎይታን ማስገኘት ጀመረ እናም ምሽትን ወስዶ የማለዳውን ውጋጋን በሚፈነጥቅ ፤ቀንን ለሰው ለሊትን ለእንስሳት ፤ማግኘትንና ማጣትን በአንጻርዮሽ አድርጎ በፈጠረው ፈጣሪ ስም አዘንን ያላለ ወገን አልነበረም ተስፋ መቁረጥ ሳይሆን የወደዱትን ሲያጡ ያመኑት ሲለወጥ የትናንቱ አላማ ሌላ ሆኖ ሲገኝ ምንዋ አይታዘን ?ይታዘን እንጂ ይለቀስ እንጂ.. እዚህ ላይ በተከበሩ ኢንጂነር ሃይሉ ላይ ያለኝን አንድ ስሜት ጠቅሼ ማለፍ ወደድኩ ያ ሁሉ ሲባልና ሲደረግ ክቡርነታቸው የተናገሩት ያንኛውን ወገን ወይንም ይህኛውን ወገን ያስቀየመ አባባል ያሳዘነ ንግግር ከግምት የጣላቸው ገለጻ ለመስጠት አልደፈሩም ይህ ለምን ሆነ? አፍርጠው ለምን አያወጡትም? ብዬ ከራሴ ጋር ተሙዋግቼ ነበር እንዲህ አለማድረጋቸው ግን አውቃለሁ የምለውን የብስለታቸውን ደረጃ በእጥፍ ጨምሮ እንዳገኘው አድርጎኛል የእሳቸው መቆጠብ «ጂ 5» የሚል ቅጽል መጠሪያ የተሰጣቸውን በወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የተመራውን ቡድን እንደፈለገ እንዲዘልና የራሱ ስህተት ጠልፎት እንዲጥለው ያደርገዋል ብዬ አለመገመቴ ስህተት ነበር .. ውሎ እያደረ ግን የምንሰማውና የምናየው እንዲህ ሆነ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ በዚያው በአገረ አሜሪካ ሁነው ስለታሰሩበት አጋጣሚ በሰጡት ማብራሪያ «እኔን ያሳሰረኝ ራሱ መለስ ዜናዊ ነው .. ምክንያቱም በመጪው ግዜ ጠቅላይ ሚኒስትር የምሆነው እኔ እንደሆንኩ ያውቅ ስለነበር ነው » አሉ ይህን ስሰማ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ትውስ አሉኝ «ጠቡ የስልጣን ሽኩቻ» ነው ያሉትን አስታወስኩ አንድም ልቤ ይህን የጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣን ሁኔታ ጉዋደኛቸውና «መቼም አንተን አምኜ ነው.. ታስጥለኛለህ »እያሉ ሲማጸኑዋቸው የነበሩት በረከት ስምኦን ቢሰሙ በትግርኛም ቢሆን የሽሙጥ ተረት መተረታቸውና በሳቅ መዝናናታቸው አይቀርም.. ደግሞስ እንዲህ ያለ የስልጣን ጥም ያለበት ሰው ሲያስተዳድረን ላይገድለን ዋስትናችንስ ምንድ ነው ? አጃኢብ አትሉም ጎበዝ ? የስልጣን ጥም መሆኑንማ ራሳቸው ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ነገሩን እኮ ጠቅላይ ሚኒስትር የምሆነው እኔ ስለሆንኩ ነው ማለት እና አሁን ቅንጅትን የሚያብጠው ማን እንደሆነ ስንረዳ መንስኤውና መጨረሻውን በማን ስህተት እንደተከናወነ ለመረዳት የሚያዳግተን ያለን አይመስለኝም አንድ ሌላ ማሳያ መጨመር ይቻላል «ኢሌክሽን» ወይንም «ምርጫ» እና «ሴሌክሽን» ወይንም «መርጦ መሾም» ያላቸው ልዩነት በገሃድ እንደሚታወቀው ሆኖ ይህ ትርጉዋሜ የጠፋባቸው ዶክተር ብርሃኑ ነጋና ለብጥብጡ ከኤርትራዊው ተወላጅ ኤልያስ ክፍሌ ጋር በመሆን ቀደምት ተዋናይ የነበሩት አንዳርጋቸው ጽጌ ሆድና ጀርባ ለመሆን መብቃታቸውን መጥቀስ ይቻላል አቶ አንዳርጋቸው በዶክተር ብርሃኑ ነጋ ተሹሜያለሁ ሲሉ ዶክተር ብርሃኑ በበኩላቸው እኔ አልሾምኩም አሉ በልደቱ አያሌው ተጀመረ የተባለው የስልጣን ሽኩቻ በተከበሩ ኢንጂነር ሃይሉ ሻውል ክልኤቱ ብሎ በአንዳርጋቸው ጽጌ ሰለስቱ ሊል ነው ቢባል የሚሙዋገት የለም አንዳፍታ ወደ ሁዋላ መለስ በሉና ለዶክተሩ የሰጠናቸው ውዴታ ምን ያህል ነበር? ይፈቱ .. ታመሙ .. ተጎዱ .. እያለ |