RSS 2.0 Email us: webmaster@mahder.com

Ethiopia: Mahder.com -Ultimate Ethiopian News and Information Portal

Tuesday
Jan 06th
Home arrow News arrow ቅንጅትን የመቀልበስ ሴራ ከወያነ ጋር እየተካሄደ ነው
ቅንጅትን የመቀልበስ ሴራ ከወያነ ጋር እየተካሄደ ነው Print E-mail
Tuesday, 01 January 2008

    አዲስ አበባ ፡- በቅርቡ በቅንጅት ሊቀመንበር በኢ/ር ኃይሉ ሻውል ከስራ የታገዱት የአመራር አባላት ከገዢው ፓርቲ ተወካዮች ጋር በሚስጢር ድርድር መጀመራቸው ተሰማ። ከአዲስ አበባ ባገኘነው መረጃ መሰረት ድርድሩን መሪዎቹ ያደረጉት ውክልናውን ማን እንደሰጣቸው ባይታወቅም በቅንጅት ስም እንደሆነ ታውቁአል። በዚህ ድርድር በቅንጅት ስም የቀረቡት ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳና ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው ሲሆኑ ከወያነ በኩል ደግሞ የማስታወቂያ ሚኒስትሩ አቶ ብርሃነ ኃይሉ ናቸው ተብሉአል። በባ ፡- በቅርቡ በቅንጅት ሊቀመንበር በኢ/ር ኃይሉ ሻውል ከስራ የታገዱት የአመራር አባላት ከገዢው ፓርቲ ተወካዮች ጋር በሚስጢር ድርድር መጀመራቸው ተሰማ።

በዚህ ስብሰባ ከገዢው ፓርቲ በኩል ይገኛሉ ተብሎ የነበረው በረከት ስምኦን ለጊዜው ይፋ ባልሆነ ምክንያት አልተገኙም።

         ሁለቱ ወገኖች በእስካሁኑ ንግግራቸው መረጃውን ይፋ ባለማድረግና በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ መስማማታቸውን የዜናው ምንጭ ገልጹአል። በዚህም መሰረት "አክራሪ" ሲሉ የአገዛዙ ባለስልጣናት የሚወነጅሉአቸውን የቅንጅቱን የአመራር አባላት ከፓርቲው በማስወገድ ረገድ በጋራ ለመስራትም ተስማምተዋል። በተለይም በአሁኑ ወቅት በፓርቲው ጽ/ቤትነት የሚያገለግለውን ቢሮ በየትኛውም መንገድ ለመንጠቅ የሚደረገውን ጥረት ማሳካት የሚቻልበትን ሁኔታ ለማካሄድ ስለሚወሰዱ ርምጃዎችም ተነጋግረው ከስምምነት መድረሳቸው ተያይዞ ተገልጹአል። በተጨማሪም እነ ብርቱካን ሚደቅሳ እና ኢ/ር ግዛቸው በበኩላቸው በዚህ መሰል ሁኔታ ንግግር ማድርጋቸው በህዝቡ ዘንድ ተቃውሞ ሊያስነሳ ይችላል በሚል ቀደም ሲል ቅንጅቱ ያቀረባቸውን ስምንት ጥያቄዎች በማንሳት በነዚህ ላይ መነጋገር እንደሚፈልጉ ተደርጎ እንዲገለጽላቸው መጠየቃቸውንም ካገኘነው መረጃ ለማወቅ ተችሉአል።

        ከዚህ ጋር ተያይዞ በቅርቡ እነዚህ ግለሰቦች ጥቂት ሰዎችን በማስተባበር ጽ/ቤቱን በሃይል ለመቆጣጠር ተደጋጋሚ ጥረቶችን አድርገው ሳይሳካላቸው መቅረቱን መዘገባችን ይታወሳል።በዚህ ዙሪያ የሚካሄደውን ድብቅ ሴራ እና ብዙ ህዝብ የሞተለትን ትግል በመቀልበስ ያገዛዙ መጠቀሚያ ለማድረግ የሚካሄደውን ደባ ወደፊት እየተከታተልን ለማቅረብ የምናደርገውን ጥረት እንቀጥላለን።






Reddit!Del.icio.us!Facebook!Slashdot!Netscape!Technorati!StumbleUpon!Newsvine!Furl!Yahoo!Ma.gnolia!Free social bookmarking plugins and extensions for Joomla! websites! title=
Comments (0)Add Comment

Write comment
quote
bold
italicize
underline
strike
url
image
quote
quote
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley

security code
Write the displayed characters


busy
 

Useful Resources


Other top stories


Quick Jump

Ethio Date & Time

ዛሬ ቀኑ:

Calendar Converter




Daylight Saving