RSS 2.0 Email us: webmaster@mahder.com

Ethiopia: Mahder.com -Ultimate Ethiopian News and Information Portal

Saturday
Nov 22nd
Home arrow News arrow የማይወዳደሩትን ማወዳደር? ይድረስ ለአብርሀ በላይ
የማይወዳደሩትን ማወዳደር? ይድረስ ለአብርሀ በላይ Print E-mail
Tuesday, 22 January 2008
 
አብርሀ በላይ ለኢትዮጵያትቅደም( EthiopiaFirst) ሬዲዮ ጣቢያ ለሰጠው ቃለ መጠይቅ አውገርግሮታል ያልኩትን እንዲያስተካከል ውይም እንዲያርም የቀረበ አሰተያየት።

 
በመጀመሪያ ቃለ ምልልሱ እንዳለ ጥሩ ነው የሚል የግል አስተያየት አለኝ። አንድ የተጠየቀውን አንድም ሳያስቀር መልሷል። ሁለት ግለ-ህይወቱንም ሆነ የግል አስተያዬቱን/ሃሳቡን ሁላችንም እንድናውቀው በማድረጉ ላቃቂርም ሆነ አስተያተት ራሱን በማቅረቡ ለዲሞክራሲያዊው ግንባታ አተዋጽኦ ይኖንረዋል እላላሁ።፡ ከዚህ ቀጥዬ ወደ ዋናው አስተያየቴ ልግባ።
 
ዕርማት ያስፈልገዋል የምለው ከላይ እንደ አርዕስት የተገለገልኩበት የማይወዳደሩትን በማወዳደሩ ነው። ይሄውም በቃለ መጠይቁ ውስጥ ጥሬውን ወያኔ ሲዬ አብርሀን አንስቶ ይቅር ማለት ይገባል ያለፈውን እያነሳን የምንወጋገዝ ከሆነ የወደፊቱን ይዘጋብናል በማለት የደርግን፣ የመኢሶንና የኢህአፓን አባሎች ለዋቤ አቅርቧል። በኔ በኩል ይህ የማይወዳደሩትን ማወዳደር ነው እንዲያው ባንድ ላማብራራት ወያኔን ከደርግ፣ ከመኢሶንና ከኢህአፓ ከማወዳደር ዱባና ቅል እጅግ በጣም ይቀራረባል። ሌላውን ዝርዝር ትቼ ላፋቸውም ቢሆን ሶስቱ ኢትዮጵያ ብለው ሲነሱ ዳር ድርበሯን አጥር ዙሪያውዋን አንድ ናት በውስጧ ያሉት በዕኩልነት ይስተዳደሩ ባጭሩ ጉልታዊነት ይጥፋ ነው። ሶስቱም አገር የጋራ መሆኗን ዘንግተው አስፍስፎ የሚጠብቀውን ጠላት ወደጎን ትተው ስልጣን ለግሌ በማለት ተባልተው ዳር ሆነው ለሚጠብቁት ለወያኔና ለሻዕብያ አሳልፈው ሰጡን። ሶስቱን አንድ የሚያደርጋቸው የኢትዮጵያ አንድነትና ሉዓላዊነት ሲሆን የሚለያያቸው አዚህ ላይ መዘርዘር ለዚህ መጣጥፍ አስፈላጊ ስላልሆነ አላነሳውም።
 
የወያኔን ስናነሳ ግን ከመነሻቸው ጀምሮ ጭራሽ ኢትዮጵያ የሚል እንዳልነበር ሚኒሊክ እንደፈጠሩት ከትግሬ (ወያኔም ሻዕቢያም ትግሬዎች ናቸው) በስተቀር ሌላ እንደሌለ የተነሱትም ነጻ ለመውጣት እንደሆነ ከኢትዮጵያ ጋር የማይታረቅ ቅራኒ እንዳላቸው በመሳሪያ እንደሚፈቱት ነው። ታዲያ አብርሀ በላይ ምኑን ከምን አገናኝቶ ነው ለሁለቱም ይቅር ለኢትዮጵያ እንበላቸው የሚለው። እንዳትሳሳቱ በይቅርታ አምናለሁ ሰው አጥፍቻለሁ ይቅር በሉኝ ካለ የማይባልበት ምክንያት አይታየኝም። አንድ የማይባል ካለ ባገር ላይ የሚመጣ ነው። ስለዚህ "አስር ቤቱ ኦሮሚኛ ...፣" ባዩ ሲዬ (ሲያስራቸው ትግሬኛ ይናገሩ ነበር?) ይቅር የማይባል ያገር ክህደት የሰራ ትላንት "" ኢትዮጵያ የሚባል ወይም ብሄራዊ ነገር ሲነሳ "ይቺ ነገር ትምክህት ትምክህት ሸተተችኝ" የሚለው መደዳው ወያኔ ሲዬ አብርሀ ይቅር ከማይባሉት የሚጣፍ ነው። ስድስት አመት ስለ ታሰረ በዚሁ ይብቃው አይባልም በወያኔነቱ ያረገውም አልቆጨውም እንዲያውም ይኩራራበት ይሆናል። በህዝብ የተጠላውን ደርግ ስለተኩ ብቻ እንደ ሽልማት ተቆጥሮላቸው ኢትዮጵያን ከነባቂው እንድትከፍላቸው ሲቀራመቱ መደዴው ሲዬም ከነ ቤተሰቡ ብዙ ብር ለመቁጠር በቅቶ ነበር። ታዲያ ዛሬ አዲሱ ሲዬ ነኝ ቢል ማን ሊሰማው። የህዝብ ጆሮም እንዲያገኝ እየተማጠናችሁ ወንጀሉን በማቅለል "ሌሎችን ወያኔዎች እንሳብ" በሚል ተልካሻ ወሬ እየማገጣችሁ ያላችሁና የተባበራችሁ በሙሉ የምትጠየቁ መሆናችሁን እንዳትዘነጉ። በወያኔ ስንቱ ወገኔ በረሀብ አለንጋ እየተጠበሰ በየማመቂያ ሰፈሩ የሚሰቃየው ተዘንግቶ ጊዜ ለጣለው መደዴ ወያኔ እጃችሁን ስትዘረጉ ታሳዝናላችሁ። የብርሀኑ ነጋ በመታሰቢያነት ያነሳው ንዴቱ ሳይለቀኝ አብርሀ በላይ ደሞ ከይቅርታ በላይ ይለናል።
 
በኔ በኩል ላገር በሎ የተሰራ ወንጀልና ባገር ላይ የተሰራ ወንጀል የማይወዳደሩትን ማወዳደር ስለሆነ አብርሀ በላይ እንዲያርም እላላሁ።
 
k.m.
ጥር 2000 ዓ/ም
ሜልበርን፣ ኽታች ኽስር





Reddit!Del.icio.us!Facebook!Slashdot!Netscape!Technorati!StumbleUpon!Newsvine!Furl!Yahoo!Ma.gnolia!Free social bookmarking plugins and extensions for Joomla! websites! title=
Comments (0)Add Comment

Write comment
quote
bold
italicize
underline
strike
url
image
quote
quote
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley

security code
Write the displayed characters


busy
 


Quick Jump

Ethio Date & Time

ዛሬ ቀኑ:

Calendar Converter




Daylight Saving