|
Read In PDF
ሰው በላው የወያኔ ቡድን ከግንቦት 97 ዓ/ም ምርጫ ወዲህ አምባገንነቱ እየባሰበት እንደ መጣ የሥነ መንግሥት ጠበብት በጥናት አስደግፈው ተናግረዋል፡፡ ኤች.አር 2ዐዐ3 ልዩ ትኩረት ሊያገኝ የበቃውም በዚሁ በዕኩይ ተግባር በደደረው የወያኔ ቡድን አቋም መነሻ መሆኑን ዕልፍ አዕላፋት ይሰማሙበታል፡፡
የወያኔ ቡድን ኤች.አር 2ዐዐ3 በዩናይትድ ስቴትስ ተወካዮች ምክር ቤት በተቃውሞ አልባ አቋም ከፀደቀበት ወቅት አንስቶ ሕጉ የኢትዩጰያን ሉዓላዊነት የሚጻረር በማስመሰል ብዙ ተንጫጭቷል፡፡ ለአያሌ ጊዜ አላዝኗል፡፡ ከኢትዮጰያ ሕዝብ ቀምቶ በኢትዮጰያ ሕዝብ ላይ በሚጫወትበት መገናኛ ብዙሃን አሰልቺ ወሬውን በተከታታይ አሰምቷል፡፡ ሆኖም የራሱን ድምፅ መልሶ ከማዳመጥ በስተቀር በክፍልፋይ እርከን እንኳን አጋር አጥቷል፡፡ ምክንያቱም ዴሞክራት ኃይሎች ሁሉ ከዚህ ዘረኛ ቡድን በተቃራኒ ረድፍ ቆመዋልና፡፡
ሰለዕውነት በዕውነት እንነጋገር፡፡ ኤች.አር 2ዐዐ3 ከሀገራችን ሉዓላዊነት ጋር አንዳችም ግንኙነት የለውም፡፡ ሰለዚህ ሕዝብን ለማሞኘት መሞከር የራስን ሞኝነት ያውጃል፡፡ ወያኔ ለሉዓላዊነታችን ጥብቅና ለመቆም ለመሆኑ ምን የሞራል ብቃት አለው?
በዓለም አቀፍ ደረጃ የአንድን ሀገር ሉዓላዊነት መደፈር የሚያረጋግጡ ምልክቶች በሥነ መንግሥት ጠብብትና በወታደራዊ እስትራቴጂስቶች ዘንድ በግልፅ ይታወቃሉ፡፡ ቀዳሚው ቀጥታ ወረራ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ከታሪክ ማህደራት ማስረጃዎች ሞልተዋል፡፡ በቅድሚያ the civilizing mission ወይም የማሰልጠን ተልዕኮ በሚል ርዕስ በነደፈችው የወረራ እቅድ በሉዓላዊቷ ኢትዮጰያ ላይ በ1928 ዓ/ም ፋሽስት ኢጣሊያ የፈፀመችው የግፍ ወረራ እንደ አንድ ጠንካራ ማስረጃ ይቀረጻል፡፡ እንዲሁም ናዚ ጀርመን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በሶቭየት ሕብረት፣በፈረንሣይ፣በቼኰዝላቫኪያ፣ በዴንማርክ፣ በኖርዌይና በመሳሰሉ ሉዓላዊ ሀገሮች ላይ ወረራ ፈፅማባቸዋለች፡፡ በተዛመደ መልኩ በወቅቱ የናዚ ጀርመን የጦር ተባባሪ የነበረችው ሚሊታሪሰት ጃፖን እ.ኤ.አ ዴሴምበር 7 ቀን 1941 ዓ/ም በፒርል ሃርቦር ላይ የፈፀመችው ወረራ የዩናይትድ ስቴትስን ሉዓላዊነት ያለ ጥርጥር ተዳፍሯል፡፡ አንድ በሉ!
የሀገሮች ሉዓላዊነት ጥሰት በርዕዮተ-ዓለማዊ ወገናዊነት ሳቢያ ይከሰታል፡፡ ይህ ደግሞ በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት በግልፅ ታይቷል፡፡ በተለይ ሶቭየት ሕብረትና ዩናይትድ እስቴትስ በሀገሮች ውስጥ ጣልቃ በመግባት ሉዓላዊነትን በመዳፈር በኩል ቀዳሚውን ሥፍራ ይዘው ቆይተዋል፡፡ ሁለቱም በየበኩላቸው በሀገሮች የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባታቸውን ከርዕዩተ-ዓለማዊ ወገናዊነት አኳያ በመተንተን ሕጋዊ እንደ ነበሩ አውጀዋል፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ ሶቭየት ሕብረት በርዕዮተ-ዓለም ገለልተኝነት ሊኖር እንደማይችል በግልፅ ተናግረዋል፡፡ በዚህም መሠረት ሶቭየት ሕብረት በወቅቱ በየትም ሀገር ዘልላ ትገባ የነበረው ከሚኒዝየምን ለማዳን እንደ ነበር ገልጻለች፡፡ እንዲሁም ዩናይትድ እስቴትስ የጦር ኃይሏ በሀገሮች የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ እየገባ ወረራ የፈጸመው ዴሞክራሲን ለማዳን እንደ ነበር ስትናገር ቆይታለች፡፡ ሆነም ቀረ ልዕለ ኃይላኑ የሀገሮችን ሉዓላዊነት ለዓመታት በተጨባጭ ተዳፍረዋል፡፡ ይሄን ሁለት በሉ!
በዓለም ላይ የሀገሮቻቸውንና የሕዝቦቻቸውን ሉዓላዊነት በማስደፈር በኩል ጥገኛ መንግሥታት ይጠቀሳሉ፡፡ ይህ ደግሞ በታሪክ ላይ ተደጋግሞ ታይቷል፡፡ጥገኛ መንግሥታት በሥልጣን ኮርቻ ላይ የሚወጡትም በባዕዳን ጠንካራ ድጋፍ መሆኑን አንጣ፡፡ በመሆኑም እስከ ሕልውናቸው ፍጻሜ ለባዕዳን እንዲያገለግሉ የግድ ይሆናል፡፡ የሥልጣን ምንጫቸው ሕዝብ አይደለምና፡፡ ጥገኛ መንግሥታት አምባገነን በመሆናቸው የሕዝብ አመኔታን አያገኙም፡፡ ለሕዝብና ለሀገር ደንታ የላቸውም፡፡ ጥገኛ መንግሥታት ያለ ባዕዳን እርዳታ ከባሕር ውስጥ የወጡ ዓሳዎች መሆናቸውን ጠንቅቀው ሰለሚያውቁ የሀገራቸውን ሉዓላዊነት በመናኛ ጥቅማ ጥቅሞች ለመሸጥ ቅንጣት ታህል አያቅማሙም፡፡
ዘረኛው የወያኔ ቡድን ለባዕዳን በማጎብደድና የሀገራችንን ሉዓላዊነት በማስደፈር ተልዕኮው ጎልቶ ይታወቃል፡፡ ይህ ፀረ-አንድነትና ፀረ-ሠላም ቡድን ከመነሻውም የፀረ-ኢትዮጰያ ኃይሎች የእጅ ሥራ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ለሥልጣን የበቃውም የኢትዮጰያን ሕልውና በማይሹ ወገኖች ትዕዛዝ መሆኑን አንጣ !
ይህ ፀረ-ሕዝብ ቡድን ሥልጣን በመያዝ ራሱን መንግሥት አድርጎ በኢትዮጰያ ሕዝብ ሀብት ላይ ከአዛዥነትና ናዛዥነት እርከን ከመድረሱ ከዓመታት በፊት የሻዕቢያ ተላላኪ በመሆን ውስጥ ለውስጥ በሚሽሎከሎክበት በ1969 ዓ/ም የዚያድ ባሬ ተስፋፊ ሠራዊት በኢትዮጰያ ላይ የፈጸመውን ወረራ በመደገፍ ከሀገራችን ሉዓላዊነት መከበር በተቃራኒ ቆሞ ተሟግቷል፡፡ ታዲያ ዕውን ወያኔ ኢትዩጰያዊ ነው?
ከመካከኛው ክፍለ ዘመን አንስቶ የኢትዮጰያን ሉዓላዊነት ለመግፈፍ ለሚመጡ ወራሪ ኃይሎች ሁሉ መሣሪያ በመሆን የማገልገል ባህል ካለው ጎሳ ማህፀን የተቀፈቀፈው ይህ ቅጥረኛ ቡድን ኤርትራን ከእናት አካሏ ለማስገንጠል በየበረሃው ለዓመታት የውሻ ሞት ሞቷል፡፡ ለዚህ እርካሽ ዓላማው ደግሞ ምንጊዜው የኢትዩጰያ የችግር አካል ከመሆን በስተቀር የመፍትሔ መነሻ ሆነው የማያውቁ ወገኖቹን አስተባብሯል፡፡ በዚህም ኤርትራን አስገንጥሎ ሀገራችንን ወደብ አልባ ለማድረግ ችሏል፡፡ ይህ ድርጊቱ ፀረ-ሉዓላዊነት መሆኑን ማን ያጣዋል?
ዛሬ የኢትዮጵያን ሕዝብ መሬት በዘመቻ በመሸጥና የዜጎችን ሀብት በመቀማት በዓለም ላይ ከታወቁ ከበርቴዎች ተርታ ራሱን ለማሳለፍ በመገስገስ ላይ የሚገኝው የወያኔ ቡድን ለኢትዮጰያ ሉዓላዊነት እንዴት ሊከራከር ይችላል? እስቲ እውነተኛ ኢትዮጵያውያን እናስብ! ኢራቅን ለመወረር የሚጓዘው የዩናይትድ ስቴትስ የጦር አይሮኘላን በኢትዮጵያ ምድር እንዲያልፍ መፍቀድ የሀገራችንን ሉዓላዊነት ማስደፈር አይደለም እንዴ? ዛሬ ደርሶ ኤች.አር 2ዐዐ3 የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚጻረር መሆኑን የሚናገረው የወያኔ ቡድን ከዓለም ፍርድ ቤት ቀርቦ ዘ-ሔግ ላይ በብዙ አሥር ሺህዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ልጆች መሥዋእት የሆኑለትን ባድመን ለሻዕቢያ ፈርሞ ለቅቆ የተመለሰ ልፍስፍስ ቡድን አይደለምን? ግልፅ ነው! ወያኔ የባዕዳን ጥገኛ ነው፡፡ጥገኛ መንግሥታት ደግሞ ፀረ-ሉዓላዊ ናቸው፡፡ ሶስት በሉ!
እንዲሁም በአቻነት አቋም ያልተቀረፁ ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ወታደራዊ ውሎች የሀገሮችን ሉዓላዊነት በቀጥታ እንደሚጥሱ ጠበብት ይስማማሉ፡፡ ይህ ደግሞ በዓለም ታሪክ ተደጋግሞ ታይቷል፡፡ መነሻ ማስረጃችን ደግሞ የውጫሌ ውል ይሁን፡፡ የውጫሌ ውል በኢትዮጵያ ንጉሰ ነገሥትና በኢጣሊያ የቄሳር መንግሥት መካከል የተፈረመ እንደ ነበር አንዘንጋ፡፡የውሉ አንቀጽ 17 ግን የሁለቱን ሀገሮች ጥቅም በአቻ እርከን የሚያስጠብቅ አልነበረም፡፡ ዳግማዊ ምኒሊክ ይህን ለማወቅ ጊዜ አልፈጀባቸውም፡፡ አንቀጽ 17 ላይ የሰፈረውን እስቲ እንመልከት፡፡ እንዲህ ይነበባል፡፡
የኢትዩጵያ ንጉሠ ነገሥት ከአውሮፖ ነገሥታት
ለሚፈልጉት ጉዳይ ሁሉ በኢጣሊያ መንግሥት
አጋዢነት መላላክ ይቻላቸዋል፡፡
ይህ እንግዲህ የውሉ የአማርኛው ትርጓሜ ነው፡፡ አንዲት ቃል እስቲ እንምዘዝ፡፡ "ይቻላቸዋል" ይህች ቃል የኢትዮጵያ ንገሰ ነገሥት መንግሥት ፈቃዱ ከሆነ ሊያደርገው እንደሚችል ታሳያለች፡፡ ይህ ምን ማለት ነው? የኢትዮጵያ መንግሥት ያለ ኢጣሊያ አጋዢነት መላላክ ይችላል ማለት ነው፡፡
የኢጣሊያንኛው አተረጓጎም ግን ከአማርኛው ፅንሰ-ሐሳብ ለወጥ ብሏል፡፡ እንዲህ ተቀርጿል፡፡
የኢትዩጵያ መንግሥት ከውጭ አገር መንግሥታት
ጋር የሚያደርገውን ግንኙነት በኢጣሊያ መንግሥት
አማካይነት ማድረግ ይገባዋል፡፡
ምንጭ የኢትዮጵያ ታሪክ ከአጼ ቴዎድሮስ እስከ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ገጽ 84፣
ልብ እንበል! በአማርኛውና በኢጣሊያንኛው ይዘት መካከል ሰፊ ልዩነት ይስተዋላል፡፡ የኢጣሊያንኛው ትርጉም በቀጥታ የኢትዩጵያን ሉዓላዊነት ይጻረራል፡፡ ምክንያቱም በይዘቱ ግዴታ አስቀምጧልና፡፡ ሰለዚህ የኢትዮጵያ መንግሥት ውሉን ውድቅ አደረገው፡፡ ወዲያውም ዳግማዊ አጼ ምኒልክ ኢትዮጵያ የማትደፈር ሉዓላዊት ሀገር መሆኗን በመግለጽ ለአውሮፖ ኃያላን መንግሥታት ደብዳቤዎች ፅፈዋል፡፡ ያም ሆነ ይህ በውጫሌ ውል አንቀጽ 17 ምክንያት የአድዋ ጦርነት ተነሣ፡፡ ጀግኖቹ ቀደምት ኢትዮጵያውያን ይህንኑ ጦርነት በደል ደመደሙት፡፡
የወያኔ ሹማምንት ኤች.አር 2ዐዐ3ን ከውጫሌ ውል ጋር ያገናኙታል፡፡ ጊዜ የሰጣቸው ፀረ-አንድነትና ፀረ-ሰላም ቡድኖች ሰለ ውጫሌ ውል መጠነኛ ግንዛቤ እንኳን አልታጠቁም፡፡ አሊያም ሰለኤች.አር 2ዐዐ3 አንዳችም ዕውቀት አጥተዋል፡፡ ኤች.አር 2ዐዐ3 በኢትዮጵያ ሰላምንና ደህንነትን ለማዳበር፣ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ፣ዴሞክራሲና የኢኮኖሚ ነፃነት እንዲሰፍኑ ለማበረታታት የቀረበ ሰነድ ነው፡፡ የኢትዮጵያን ሕዝብ ጥያቄ የሚጠይቅ ሕግ ነው፡፡ ሰለዚህ በምንም ዓይነት መንገድ ከውጫሌ ውል ጋር አይዛመድም፡፡
በዓለም ላይ ከአቻነት በተቃራኒ ወደ ታሪክ ከወረዱት ውሎች መካከል የቨርሳይ ውል( Versailles treaty) ትልቅ ስፍራ ይዟል፡፡ ጀርመን በአንደኛው የዓለም ጦርነት ስትሸነፍ ይህንኑ ውል ተገድዳ እንድትፈርም ተደረገች፡፡ ውሉ ለአንደኛው የዓለም ጦርነት ጀርመንን በቀጥታ ተጠያቂ አድርጓታል፡፡ በዚህ ውል መሠረት የጀርመን ሉዓላዊነት ክፋኛ ተደፍሯል፡፡ ታሪክ ይናገራል፡፡ በቋንቋ አንድ!
But what hurt most was that Versailles virtually
disarmed Germany* it restricted the army to
100,000 long-term volunteers and prohibited
it form having planes or tanks. The General
staff was also outlawed. The navy was reduced
to little more than a token force and forbidden
to build submarines or vessels over 10,000
tons. ምንጭ The Rise and Fall of The Third
Reich page 91.
ይህ የታሪክ ዕውነታ ነው፡፡ እንደ ወረደ አስቀምጠነዋል፡፡ ግን ደግሞ በቋንቋ ሁለት የግድ ይላል፡፡ እንዲህ ይነበባል፡፡
የቨርሳይ ውል በእርግጠኝነት ጀርመንን
ትጥቅ አስፈትቷታል፡፡ በዚህም መሠረት
ጀርመን የጦር ሰራዊቷ በአንድ መቶ ሺህ
ውስን ጊዜ አገልጋይ በጎ ፈቃደኛ አባላት
እንዲገደብ የተደረገ ሲሆን አይሮኘላኖችንና
ታንኮችን ደግሞ ፈፅሞ እንዳትታጠቅ
ተከለከለች፡፡ እንዲሁም የጄኔራል እርከን
ስብስብ እንደ ሕገ ወጥ ተወስዷል፡፡
የባሕር ኃይል ደግሞ በጣም በጥቂቱ ሆኖ
ሰርጓጆች ወይም ወደ አሥር ሺህ ቶን ክብደት
ያላቸው በጣም ትልልቅ መርከቦች ግንባታ
ጨርሶ ተከልክሏል፡፡
በሀገሮች መካከል በአቻነት መርህ ላይ ያልተቀረፁ ሌሎችንም ውሎች አላጣንም፡፡ በግልፅ ቋንቋ ግን ግልፅ እንዳደረግን ይሰማናል፡፡ በአቻነት ላይ ያልተመሰረተ ውል ፀረ-ሉዓላዊ ይዘት ይሰንቃል፡፡ አራት በሉ!
ጌቶቹ በሎሌያቸው በወያኔ ላይ በጠጠረ አቋም የተነሱት በእርግጥ ከምርጫ 97 መጭበርበር ወዲህ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን ቀደም ሲልም አያሌ ታዋቂ የሥነ መንግሥት ጠበብትና ፀሐፍት በሀገራችን ደሞክራሲን ለማስፈን ወያኔ ተነሣሽነት እንዳጣ ተናግረዋል፡፡ በተለይም የ1992 ዓ/ም የተወካዮችና የክልል ምክር ቤት ምርጫ ተብዬውን በቅርብ የተከታተሉ ፀሐፍት ይህንኑ ዕውነታ በማስመልከት የምርምር ውጤታቸውን በመፅሐፍ አደራጅተው ለንባብ አብቅተዋል፡፡ በዚህ ይዘት ከተደራጁት መጻሕፍት ከአንዱ ውስጥ በጣም በጥቂቱ መዝዘናል፡፡ በቋንቋ አንድ ይዘናል፡፡ እንዲህ ይላል፡፡
The EPRDF has shown an astonishing lack
of initiative to seriously confront the many
obstacles in democratisation process and to
open up for a true pluralistic discourse in the
country. Democracy is not achieved by holding
elections every five years. Democracy is about
giving people confidence as subjects, not
objects of political life.ምንጭ The Ethiopian 200 Elections አርትኦት Siegfried pause Wang and kjetil tronvall.
ከቋንቋ አንድ ወደ ሁለት መንዝረነዋል፡፡ ቃናው እንዳይለወጥ ተጠንቅቀናል፡፡ ይዘቱን ጠብቀናል ፡፡ እነሆ!
ዴሞክራሲን ለማስፈን በሚደረገው እንቅስቃሴ
ሒደት የሚያጋጥሙትን አያሌ መሰናክሎች ከምር
በመቋቋም በሀገሪቱ ውስጥ ዕውነተኛ የብዙ
ፖርቲ ውይይት ለመክፈት ገዢው የፖለቲካ
ማህበር በሚገርም ሁኔታ ተነሣሽነት
ማጣቱን አሳይቷል፡፡ ዴሞክራሲ በየአምስት
ዓመቱ ምርጫ በማካሔድ ብቻ አይመጣም፡፡
ዴሞክራሲ በፖለቲካ ሕይወት ሕዝብ ተቀባይ
መሣሪያ ሳይሆን የፖለቲካ ዋናው ባለቤት
እሱ ለመሆኑ በራሱ እምነት እንዲያድርበት
የማድረግ አካሔድ ይሆናል፡፡
ያም ሆነ ይህ እውነተኛ ኢትዮጵያውያን ወያኔን ወደ ታሪክ ትቢያነት የመቀየር ትውልዳዊ ግዴታ አለብን፡፡ ሰው በሰው የሚገዛበት ሥርዓት ተወግዶ የሕግ ልዕልና እንዲመጣ ጠንክረን ልንገኝ ይገባል፡፡ ከባርነት ለመውጣት እንጣር በዚህ ሒደት ኤች.አር 2ዐዐ3 ተግባራዊነት የራሱ አስተዋጽኦ እንዳለው ለአፍታም አይዘንጋ፡፡ እርግጥ ነው፡፡ ጊዜ የሚጠብቁ ጉዳዩች አሉ ፡፡ ነገር ግን አጀንዳው እንዳይሞት አሁንም ትኩረት ሊሰጠው ይገባል እንላለን፡፡
|