|
ብርቱካንና የፓርላማ አባላቱ ሳይስማሙ ቀሩ |
|
|
|
Monday, 11 February 2008 |
|
|
| ከጌታቸው ንጋቱ |
|
የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ የፓርላማ ተመራጭ የሆኑ አባላት ከወ/ሪት ብርቱካን ጋር ያደረጉት ንግግር ያለስምምነት ተቋጨ፡፡ እነ ወ/ሪት ብርቱካን የላዕላይ ምክር ቤት መምረጥ አይችሉም፤ የጠቅላላ ጉባኤው ስልጣን ነው ሲሉ የፓርላማ አባላቱ ተናግረዋል፡፡
|
|
|
|
|
የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ የፓርላማ ተመራጭ የሆኑ አባላት ከወ/ሪት ብርቱካን ጋር ያደረጉት ንግግር ያለስምምነት ተቋጨ፡፡ እነ ወ/ሪት ብርቱካን የላዕላይ ምክር ቤት መምረጥ አይችሉም፤ የጠቅላላ ጉባኤው ስልጣን ነው ሲሉ የፓርላማ አባላቱ ተናግረዋል፡፡
ሰኞ ዕለት ቄራ አካባቢ በሚገኘውና እነ ወ/ሪት ብርቱካን ለመሰብሰቢያና ለመገናኛነት በሚጠቀሙበት የኪራይ ቤት ውስጥ የሃያ አምስት ፓርላማ አባላት ውክልና አለን የሚሉ አምስት የፓርላማ አባላት ከወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳና ከአቶ አለማየሁ የኔነህ ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል፡፡
የፓርላማ አባላቱን ወክለው ለኤ.ቢ.ቢአይ ዊክሊ መግለጫ የሰጡት አቶ ጌታቸው ባይፈርስ እንደገለፁት “ወደእነ ወ/ሪት ብርቱካን የሄድነው እያደረጉ ያለውን እንቅስቃሴ ተገቢ ባለመሆኑ እንዲያቆሙ፤ የላዕላይ ም/ቤት መምረጥ የሚችለው ጠቅላላ ጉባኤው እንጂ እነሱ አለመሆናቸውን ለማስረዳት ነበር፡፡ አዲስ ፓርቲ መመስረትም ከጠቅላላ ጉባኤው ውሳኔ ውጪ በመሆኑ ከዚህ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ ጠይቀናል” ብለዋል፡፡
የፓርላማ አባላቱ ከዚህ በተጨማሪ ከአቶ ተመስገን ጋር የወ/ሪት ብርቱካን ቡድን ያደረገውና እያደረገው ያለው ውህደት አግባብ አለመሆኑንና ሂደቱ ቅንጅትንና የኢትዮጵያን ሕዝብ የመታገል መንፈስ የሚገድል በመሆኑ መቆም እንዳለበት መጠየቃቸውን አቶ ጌታቸው ጨምረው ገልፀዋል፡፡ የተጀመረው የሽምግልና ሂደትንና የዴሞክራሲ ጥረቱን የነወ/ሪት ብርቱካን አካሄድ እንደሚጎዳ እንደገለፁላቸው የሚናገሩት እኝሁ የፓርላማ አባል ከነወ/ሪት ብርቱካን በተሰጣቸው ምላሽ ደስተኛ አለመሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ወ/ሪት ብርቱካን በሰጧቸው ምላሽም [በያዝነው መንገድ እንቀጥላለን፤ ሥራ መስራት ስላለብንም የላዕላይ ም/ቤቱን ማሟላታችን ትክክለኛ እርምጃ ነው] ማለታቸውን አቶ ጌታቸው ገልፀዋል፡፡
ወ/ሪት ብርቱካንን ስለተደረገው ስብሰባ ለማነጋገር በትላንትናው ዕለት ያደረግነው ጥረት ስልካቸውን ባለመመለሳቸው ሊሳካ አልቻለም፡፡
http://www.abbimedia.com.et
|
|