RSS 2.0 Email us: webmaster@mahder.com

Ethiopia: Mahder.com -Ultimate Ethiopian News and Information Portal

Saturday
Nov 22nd
Home arrow News arrow የአለቃ አያሌው የመቃብር ኃውልት እንዳይሰራ ታገደ
የአለቃ አያሌው የመቃብር ኃውልት እንዳይሰራ ታገደ Print E-mail
Tuesday, 12 February 2008
      
Ethiopia Zare (እሁድ የካቲት 2 ቀን 2000 ዓ.ም. Feb. 10,2008)፦ የአለቃ አያሌው ታምሩ አስክሬን ባረፈበት ደብረ አሚን ተክለኃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ኃውልታቸው እና የመታሰቢያ ጸሎት ቤት እንዳይሰራ ቤተ ክርስቲያኗ ከለከለች።

የአለቃ አያሌው ቤተሰቦች በደብሩ የመታሰቢያ ኃውልት እንዲሁም የጸሎት ቤት ለማሰራት እንዲፈቀድላቸው ከነኀሴ 29 ቀን 1999 ዓ.ም. ጀምሮ ጥያቄ ቢያቀርቡም ከቤተክርስቲያኗ መልካም ምላሽ እንዳላገኙና ጥያቄያቸውን ለደብሩ ብቻ ሳይሆን ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤትና ለፓትርያኩ ለማቅረብ ቢሞክሩም እስካሁን ድረስ መፍትሄ እንዳልተሰጣቸው ምንጮቻችን ዘግበዋል።

የቤተክርስቲያኗ ሰዎች ማንም ሄዶ ቢጠይቃቸው ለአለቃ አያሌው የመቃብር ቤት እንዳይሰራ መከልከላቸውን ሳይፈሩ በድፍረት ይናገራሉ። ለዚህ የሚሰጡት ምላሽ ደግሞ ‘አለቃ አያሌው ከቤተክርስቲያን ቀኖና ወጥተው ራሳቸውን እንደ ቤተክርስቲያን የሚያዩ ሰው ስለነበሩ ነው።’ የሚል ሲሆን፤ በቀብር ስነ-ስርዓታቸው ወቅት ለአለቃ አያሌው የፍትሃት ጸሎት በቤተክርስቲያኒቷ ካህናት አልተፈጸመም።

ይህም ደግሞ የቤተክርስቲያኗን ስርዓት ያልተከተለ ነው። በወቅቱም ፍትሃት እንዲደረግላቸው የአለቃ አያሌው ቤተሰቦች የተጠየቁ ሲሆን፣ "... 'አባታችን በሕይወት እያለ ራሱን ፈቷል' ሲሉ ስለተናገሩ ነው፤ አሁን ታዲያ ለምን የመቃብር ቤት በቤተክርስቲያኗ ግቢ ማሰራት ያስፈልጋቸዋል?" ሲሉ መከልከላቸውን ለማወቅ ችለናል።

አለቃ አያሌው በሕይወት እያሉ ፓትሪያርኩን ያወገዙ ሰው ሲሆኑ፣ በዚህም በቤተ ክህነት አካባቢ በ1988 ዓ.ም. ያለጡረታ የተገለሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ከነበሯት ታላላቅ ሊቃውንት አንዱ ነበሩ። ብዙ ተከታዮችን ያፈሩ በመሆናቸው ውግዘታቸውን በተቀበሉ ካህናት ፍትሃት ተደርጎላችው መቀበራቸው ይታወሳል።






Reddit!Del.icio.us!Facebook!Slashdot!Netscape!Technorati!StumbleUpon!Newsvine!Furl!Yahoo!Ma.gnolia!Free social bookmarking plugins and extensions for Joomla! websites! title=
Comments (0)Add Comment

Write comment
quote
bold
italicize
underline
strike
url
image
quote
quote
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley

security code
Write the displayed characters


busy
 


Quick Jump

Ethio Date & Time

ዛሬ ቀኑ:

Calendar Converter




Daylight Saving