|
Wednesday, 27 February 2008 |
|
በደቡብ ኢትዩጰያ በጎፋ ልዩ ዞን የዛላ ወረዳ የቅንጀት ለአንድትና ለዲሞክራሲ ፖርቲ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ኃይለ ሚካኤል ዝጳታ ከየካቲት 1ዐ ቀን 2ዐዐዐ ዓ/ም አንስቶ በእሥር ላይ መሆናቸው ተገለጠ፡፡ የወረዳው ሰብሳቢ ሊታሰሩ የቻሉት በፖርቲው የወረዳ ጽ/ቤት በር ላይ የኢትዩጰያን ሰንደቅ ዓላማ ሰቅለው በማውለብለባቸው ብቻ እንደ ወንጀል ተቆጥሮባቸው መሆኑ ታውቋል፡፡
አቶ ኃይለ ሚካኤል ዝጳታ በ1997 ዓ/ም በተካሔደው በተወካዩችና የክልል ምክር ቤት ምርጫ በከፍተኛ ድምፅ ያሸነፋ ሲሆን፣ ወያኔ በመላ ሀገሪቱ ምርጫውን ሲያጭበረብር የእሳቸውም የምርጫ ውጤት በወቅቱ የተቀማ መሆኑን የጎፋ ልዩ ዞን የቅንጅት ፖርቲ ኮሚቴ በስልክ ገልጾልናል፡፡
ግለሰቡ እስከ አሁን ወደ ፍርድ ቤት ያልቀረቡ ከመሆናቸውም በላይ ቤተሰብ፣ ጓደኛና ዘመድ እንዳይጠይቋቸው ፖሊስ እንደሚከለክል ለማወቅ ተችሏል፡፡
|