|
ባሁኑ ወቅት በኢትዩጰያ ውስጥ የምግብ ምርት ዋጋ በጣም አሻቅቧል፡፡ ሰበቡ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ሰው በላው ወያኔ ከዙፋን ላይ ከተቀመጠበት ወቅት አንስቶ በኢትዩጰያ የገበያ ዋጋ ተረጋግቶ ግን አያውቅም፡፡ በዚህ መነሻ በገበያ ውስጥ የሽያጭና የግዢ ሽብር ቋሚ ትርዒት ሆኗል፡፡ ከምርጫ 97 ወዲህ ግን ተባብሶ ቀጥሏል፡፡ በዚህም መሠረት የዛሬ 2 ዓመት በብር 45ዐ.ዐዐ ተሽጦ የነበረው አንድ መቶ ኪሎ ግራም አንደኛ ደረጃ ጤፍ ዛሬ በብር 68ዐ.ዐዐ ይሸጣል፡፡ የዛሬ ሁለት ዓመት የተሸጠበት ዋጋም ቢሆን በኢትዩጰያ የገበያ ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ ሰለነበረ የአዲስ አበባን ሕዝብ ብዙ አነጋግሯል፡፡ ያሁኑ ግን ብሷል፡፡ በአገዛዙ ባለሥልጣናትና በባለሟሎቻቸው ካልሆነ በስተቀር በደሀው ሕዝብ አቅም የማይቀመስ ሆኗል፡፡ እንዲሁም ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት በብር 3ዐ የተሸጠው የምግብ ዘይት ዛሬ በመጠኑም ሆነ በዓይነቱ አንዳችም ለውጥ ሳይደረግበት ባሁኑ ወቅት በብር 62.ዐዐ ሲሸጥ ይስተዋላል፡፡ በተዛመደ መልኩ በብር 7.ዐዐ ይሸጥ የነበረው ምሥር ክክ በነበረበት መጠንና ዓይነት በአሁኑ ወቅት በብር 11.ዐዐ ይሸጣል፡፡ የስኳር ዋጋ በኪሎ በጣም ንሯል፡፡ የሽንኩርት፣የቃሪያና የቅመማ ቅመም ዋጋ ከዚህ ቀደም በኢትዮጰያ ገበያ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ አሻቅቧል፡፡
የዛሬ ሶስት ወር በብር 3.5ዐ ይሸጥ የነበረው አንድ ኪሎ ግራም ብርቱካን በአሁኑ ወቅት በብር 9.ዐዐ ይሸጣል፡፡ እንዲሁም የዛሬ ሁለት ወር በብር 3.5ዐ የተሸጠው አንድ ኪሎ ግራም ማንጎ ዛሬ በብር 6.5ዐ ይሸጣል፡፡ የዋጋ ማሻቀብ በምግብ ምርት ላይ ብቻ ተወስኖ አልቆመም፡፡ በዚህም መሠረት አንድ ኩንታል ሲሚንቶ ከብር 176.ዐዐ በላይ ይሸጣል፡፡ እርግጥ ነው፡፡ የሙገር ስሚንቶ በኩንታል በብር 17ዐ.ዐዐ እንደሚሸጥ ተመልክቷል፡፡ የብረት ዋጋ እንዲሁ አሻቅቧል፡፡ የቤት ቀለምና የኖራ ዋጋም ሊታመን በማይቻልበት ደረጃ ከፍ ብሏል፡፡ የግንባታ መሣሪያዎች ሁሉ ዋጋቸው ወደ ላይ ወጥቷል፡፡ በመላው ኢትዮጰያ የዋጋ ንረት ከጡዘት እርከን ገብቷል፡፡ ኤሎሄ!ኤሎሄ! ላማሳባቂታኒ!
ዛሬ በአንድ ብር የገዙት ዳቦ በነጋታው በዚያው ዋጋ አይታሰብም! ቢያንስ የስሙኒ ጭማሪ የማይቀር ይሆናል፡፡ አሊያም በሃምሳ ሳንቲም ያድጋል፡፡ልመና ተፋፍሟል፡፡ ሕጻናት፣ወጣቶች፣ጎልማሶች፣ሽማግሌዎችና አረጋውያን ለማኞች በአዲስ አበባ ይርመሰመሳሉ፡፡
በዚህ ሒደት ሰሞኑን በፍልውኃ አካባቢ አንድ የውጭ ዜጋ በአሥራ ስምንት ለማኞች ተከብቦ ታይቷል፡፡ ከመካከላቸው ሁለቱ ሕፃናት ያዘሉ እናቶች ነበሩ፡፡ በአብያተ ክርስቲያን ደጆች የሚቀመጡ ለማኝ ዜጎች ወደፊት በአሐዝ ከተሳላሚ ምዕመናን በአቻ እርከን እንደማይመዘገቡ ማንም ማረጋገጫ አይሰጥም፡፡ በተዛመደ መልኩ በየሆቴል ቤቱ በጓሮ በር በኩል ተኮልኩለው የሚጣል ትርፍራፌ የሚጠባበቁ ወላጅ አልባ ሕጻናት ቁጥር ከምንጊዜውም አሻቅቧል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የውኃ እጥረት ችግር በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍል ተባብሷል፡፡ በዚህም መሠረት በደቡብ ኢትዮጰያ በአላባ ወረዳ በመኪና መንገድ ዳር ለውኃ ፍለጋ የወጡ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በየቀኑ በሰልፍ ይቆማሉ፡፡ በተዛመደ መልኩ በአያሌ መቶዎች የሚቆጠሩ ውኃ ለመጫን ከሩቅ ርቀት የመጡ አህዮች ይኰለኩላሉ፣ ጀሪካን፣ ኮዳና ታኒካዎችም ለትርዒት የቀረቡ መስለው ይደረደራሉ፡፡ እንዲሁም በአርባ ምንጭ ከተማ በሆቴል ቤቶች የሚገኙ የገላ መታጠቢያዎች በውኃ መጥፋት ሳቢያ አገልግሎታቸውን አቋርጠዋል፡፡ ከሩቅ ርቀት በአህያ ጀርባ ከመጣ ውኃ ለገላ መታጠቢያ ለሆቴሉ ደንበኛ አንድ ባልዲ መቸር በሆቴል ቤቱ ባለቤት መልካም ፈቃድ ብቻ የሚፈጸም ይሆናል፡፡
በተያያዘ ሁኔታ ከአርባ ምንጭ ወደ ጂንካ የሚሄድ ተጓዥ እጃቸውን ወደ ሰማይ ሰቅለው በሐይላንድ ውኃ እንዲጣልላቸው እየለመኑ መኪና ተከትለው የሚሮጡ ሕፃናትን በየቀኑ ያያቸዋል፡፡ በአርባ ምንጭና በጂንካ መካከል ባሉ አነስተኛ መንደሮች ማንም ተጓዥ በቀላሉ ውኃ ሊያገኝ አይችልም፡፡ በጂንካ ከተማ የውኃ ችግር በጣም አሻቅቧል፡፡ በዚህም መሠረት ማንም ሰው በሆቴል ቤት ውስጥ ምግብ ገዝቶ እየተመገበ ካልሆነ በስተቀር በከተማው ውስጥ በየትም ቦታ ለመጠጥ ውኃ ለምኖ አያገኝም፡፡ በየሆቴል ቤቱ ውስጥ በየትም ቦታ ለመጠጥ ውኃ ለምኖ አያገኝም፡፡ በየሆቴል በቱ ውስጥ የተተከሉ የገላ መታጠቢያዎች ደግሞ በውኃ አለመኖር ደርቀው ቆመዋል፡፡
የትራንስፖርት ዋጋ በበኩሉ በመላው ኢትዮጰያ በጣም ንሯል፡፡ በዚህም መሠረት የዛሬ ሁለት አመት ከአዲስ አበባ ወላይታ ብር ሰላሳ የነበረው አሁን ብር ሃምሳ ሆኗል፡፡ እንዲሁም በቅርብ ጊዜ ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር ብር ሰማኒያ የነበረው የትራንስፖርት ዋጋ በአሁኑ ወቅት ወደ ብር 1ዐዐ.ዐዐ/አንድ መቶ ብር/ አሻቅቧል፡፡ እንዲያውም የትራንስፖት ዋጋ ያልጨመረ የጉዞ መስመር ፈፅሞ የለም፡፡ በዚያው ባሻቀበው ዋጋ እንኳን የትራንስፖርት አገልግሎት ቶሎ ያለመገኘት ሁኔታ ደግሞ ጎልቶ ይስተዋላል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከየካቲት 6 ቀን 2ዐዐዐ ዓ/ም አንስቶ የአዲስ አበባ ከተማ የአውቶብስ የትራንስፖርት አገልግሎት ዋጋ ከሃምሳ ሳንቲም ወደ ሰባ አምስት አድጓል፡፡ የታክሲ ሒሳብም እንዲሁ በጣም ጨምሯል፡፡
ዛሬ በሀገራችን ብዙዎች "ትግሬ" የሚለውን ቃል ለማንሳት ይፈራሉ፡፡ ምክንያቱም በአዲሱ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ መሠረት ዘር ማጥፋት የሚል ትርጉም ሊያሰጥባቸው እንደሚችል በመጠርጠር እንደሆነ ይነገራል፡፡ አሊያም አንድ ሰው በአፅንኦት "ትግሬ" በማለቱ ብቻ የአገዛዙ ደህንነቶችና ፖሊሶች ክትትል ሊጠብቅበት እንደሚችል ይታሰባል፡፡ በግርድፍ ምልከታ የሁሉም ሰዎች ግምት ይህን ይመስላል፡፡ በተያያዘ ሁኔታ " ትግራይ" የተባለውን የክፍለ ሀገር ስም ለመጥራት የማይደፍሩም ታይተዋል፡፡ "ትግራይ በመልማቱ የምቀኝነት መንፈስ አንፀባርቃችኋል" በሚል መነሻ ለፈጠራ ክስ ላለመመቸት ከማሰብ እንደሆነ ይነገራል፡፡ በሌላም በኩል ትግሬዎች ራሣቸውን "ትግሬ ነን!" አይሉም፡፡" ትግራይ ነን!" ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ የሥነ ልቦና ችግራቸውን ያስወገዱ መስሏቸው ዙሪያ ጥምጥም ይጠራሉ፡፡ የሕዝቡንም ስሜት የለወጡ መስሏቸው በከንቱ ይደክማሉ፡፡ ወደዱም ጠሉም "ትግሬ" ሌላ ስም የለውም፡፡ ህዝቡ "ትግሬ" ሲሆን፣ ክፍለ ሀገሩ "ትግራይ" መሆኑን አይጡ፡፡ ኘሮፌሰር አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ ዳግማዊ አጤ ምኒሊክ በተባለው መፅሐፋቸው "ችጋር ያባረረው ትግሬና ባሩድ የሸተተው አውሬ አንድ ናቸው!" ብለዋል፡፡ ደጃች በዝብዝ ካሣና መሰል ትግሬዎች ኢትዮጰያን ቆርሰው ለመስጠት ለባዕዳን በጻፏቸው ደብዳቤዎች ሁሉ ትግሬዎች መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ ታዲያ የዛሬዎቹ ትግሬዎች ለምን በስማቸው ያፍራሉ?
ያም ሆነ ይህ ባሁኑ ወቅት የኢትዮጰያ ሕዝብ በኑሮ ውድነት ሕይወቱ ተበላሽቷል፡፡ ተስፋ ባይቆርጥም ብሩህ ነገር አጥቷል፡፡ ለአገዛዙ ያለው ጥላቻ በቃላት ሊገለፅ ከሚችለው በላይ አሻቅቧል፡፡ ይጮኻል! ኤሎሄ!ኤሎሄ! ይላል፡፡ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይጮኻል! በለቅሶ ቤት እንዲሁ ይጨኻል! በሠርግ ቤት ውስጥም ይጮኻል! መልስ ግን የለም! ሆኖም ይጮኻል! ለፖለቲካ ሥልጣኑ ይጮኻል! ለሰብዓዊ መብቱ ይጮኻል! ለክብሩ ይጮኻል! ኤሎሄ !ኤሎሄ !ይላል፡፡ አሁንም ይጮኻል፡፡
በዝምታም ይጮኻል! በጩ¤ትም ይጮኻል፡፡ ኤሎሄ!ኤሎሄ! ይላል፡፡ ኤሎሄ!ኤሎሄ! ላማሳባቂታኒ! በመኖርና ባለመኖር መካከል ምን ልዩነት ይስተዋላል? ኤሎሄ!ኤሎሄ! እስከ መቼ ኤሎሄ?ኤሎሄ!ኤሎሄ! ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ኤሎሄ!ኤሎሄ!ኤሎሄ! ላማሳባቂታኒ!
|