RSS 2.0 Email us: webmaster@mahder.com

Ethiopia: Mahder.com -Ultimate Ethiopian News and Information Portal

Saturday
Nov 22nd
Home arrow News arrow ከኬንያ ህዝብ ምን እንማራለን ?- ከጌታቸው ጋረደው
ከኬንያ ህዝብ ምን እንማራለን ?- ከጌታቸው ጋረደው Print E-mail
Monday, 10 March 2008

                የቅርብ ጎረቤታችን የኬንያ ህዝብ በታህሳስ ወር 2000 ባደረገው ምርጫ እንደ መለስ ዜናዊ ያሉ ፐሬዜዳንት ኪባኪ የሚባሉ አጭበርባሪ መሪ ስለገጠሙት፣ ህዝቡ በድምጹ አሽንፎ ያገኘውን መብት አሳልፎ ለመስጠት ስላአልፈለገ፣ ከአንድ ሺህ በላይ የሆነ ህዝብ ሲሞት አምስት መቶ ሺህ የሚሆን ህዝብ አገሩን ለቆ ለመሰደድ ተገዷል. በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ቆስልዋል፣

ይህ ችግር ያለ አስታራቂ ግቡን ለመምታትት ስለማይችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ የነበሩት አቶ ኮፊ አናን በአስታራቂነትስለቀረቡ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለሁሉም የሚስማማ  የእርቅ መንደርደሪያ አዘጋጅተው ሁለቱም ባላንጣዎች የተስማሙበት የእርቅ ሐሳብ ስለቀረበ ሁለቱ ባላንጣዎች ለኬንያ ህዝብ የገቡትን ቃል በተግባር ለማዋል በየስራቸው ተሰማርተዋል፣ የተቀዋሚው ድርጅት መሪ አቶ ኦዲንጋ ከጠበቁት በላይ  የጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣን ስለአገኙ በጣም ተደስተዋል። ብዙ ህዝብ ቢሞት፣ ቢስደድና ቢቆስልም የተደረገው ድካምና መስዋእትንት በከንቱ አልቀረም። የኬኒያ ህዝብ ላደረገው ታላቅ ትግል ለተጎናጸፈው ድል አንድ ህዝብ በችግር ጊዜ ማድረግ የሚገባውን አድርጎ የተነጠቀውን መብት ለማስመልስ በመቻሉ አንኳን ደስ ያለህ እንልዋለን።

 በኬንያ ህገ መንግስት አገሪቱንና ህዝቡን የሚወክልና የሚመራው ፐሬዜዳንቱ ብቻ ስለነበር መንግስቱን የሚመራ ጠቅላይ ሚኒስትር አልነብረም፣ አሁን በተደረገው ስምምነት የተቃዋሚው መሪ አቶ ኦዲንጋ አዲስ በሚዘጋጀው ህገ መንግስት መንግስቱን የሚመራ አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲጨመርበት ሰለጠየቁ ተቀባይነት አግኝትዋል። ይህም የስልጣን ክፍፍል በቀላል የተገኘ አይደለም። ኮፊ አናን በአስታራቂነት ከመጡ በኋላ ፕሬዜዳንት ኪባኪ ይህንን ሀሳብ በፍጹም የማይቀበሉ መሆናቸውን ደጋግመው ሲያሳስቡ፣ ኦዲንጋ በበኩላቸው ይህ ካልተደረገ፣ የኬንያ ህዝብ እንዲያምጽ  የሚቀሰቅሱ መሆናቸውን ደጋግሙ ስለገለጹ የአገሪቱ ፕሬዜዳንት አሻፈረኝ ካሉ፣ በሚወሰደው እርምጃ ከስልጣን ሊባረሩ ስለሚችሉ ሳይወዱ በግድ መቀበል ተገደዋል። ይህ ድል የተገኘው በኬንያ ህዝብ ጠንካራ ትግል በኦዲንጋ ቆራጥ ውስኔ ነው፣ መለስ ዜናዊ ያዘጋጅውን የራሱን ህገ መንግስት በትክክል ሥራ ላይ እንዲያውል ተጠይቆ አሻፈረኝ ሲል፣ ወኔ ያለው ኦዲንጋ  ፕሬዜዳንቱን አስገድዶ አዲስ ህገ መንግስት እንዲዘጋጅ ለማስገደድ በመቻሉ አድናቆታቸን ይድረሳቸው። ቆራጥ መሪና ወኔ ያለው ህዝብ ባለበት አገር አንባ ገነን መሪ ስፍራ የለውም፣፣ ይህንን በኬንያ አይተናል።

እኛ ኢትዮጵያውያን ከኬንያ ህዝብ የምንማረው ጠቃሚ ነገር አለ?  ኬናውያን የተጠቀ ሙበትም ዘዴና ስልት ከተከትልን ብዙ ነገር ለመማር እንችላለን፣፣ በመጀመሪያ ከአባ ቶቻችን የወረስነውን ግን አሁን የረሳነውን የአገር ፍቅር ስሜትና ያጣነውን ወኔና ጀግንነት መልሰን ማግኘት ሲገባን፣ ያለችን አንድ፡ኢትዮጵያ፡ብቻ፡ስለሆነች ቅጥረኞች ከአለም ካርታ ሰርዘው እንዳያጠፏት ማናቸውንም መስዋእትነት ለመቀበል ዝግጁ መሆን ይገባናል፣ የዘር ጠላቶቻቸን ኢትዮጵያን የቅኝ ተገዥ ለማድሩግ ደጋግመው ያደረጉት ሙከራ ባይሳካላቸውም፣ አሁን በቅጥረኛው በመለስ ዜናዊ ድጋፍ ህልማቸው እውን ለመሆን የተቃረበ ስለሚመስል ይህ ከሆነ፣ አገር አልባ ሆነን የምንቀረው አኛ ብቻ ሳንሆን ልጆቻችምን እንደፍልስጢኤም ልጆች ሜዳ ላይ ተወልደው ሜዳ ላይ የሚያድጉ  ስደቶች ሁነው ይቀራሉ፣ ይህንን ስንል ማጋነን ይመስለናል፣ አይደለም፣ መለስና ግብረ አበሮቹ  በ1983 የተበጣጠስ ጨርቃቸውን እንደለበሱ  በአህያ ተጭነው አዲስ አበባን ሲወሩ፣ ከሶስት ወራት በኋላ ወደመጡበት ወደ በረሀቸው ተመልሰው ይሄዳሉ እያልን እናሾፍ ነብር፣ ዛሬ የት ደረሱ? በዘረኛ ፖለቲካቸው እኛን በታትንው  ካዳከሙን በኋላ ከጎንደርና ከወሎ ግዛቶችን ቆርጠው ወደትግራይ ክልል በመቀላቀል ነዋሪውን ስደተኛ ከማድረ ጋቸው ሌላ የቀረውን የጎንደር ግዛት እየቆራረጡ ለሱዳን  ሸልመዋል፣ ከኤርትራ ጋር ባደረጉት የጌታና የሎሌ ስምምነት ወሰኑን ያለጠባቂ ስለተዉት የሻዕቢያ ጦር አንድ ጥይት ሳይቶኩስ  የኢትዮጵያን ግዛት ለመውርውር ቻለአ። በመለስ ዜናዊ ስህተት ትርጉም ለሌለው ጦርነት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ልጆቻችን በከንቱ መስዋእት ሆነው ቀሩ፣ መለስ በዚህ ብቻ ሳይወሰን የአሜሪካ ቅጥረኛ በመሆን ወታደሮቻችንን ወደ ሱማሊያ ልኮ ሲያስፈጃቸው አስከሬናችው መንገድ ላይ እንዲጎተት ከመደረጉም በላይ ሰላሳና አርባ  አስከሬን በአንድ ጉርጓድ ይቀበራል፣ ጠላት ይጠላል እንጂ አይናቅም የሚባለውን የአባቶች ምሳሌ ሰምተናልን?

 

የኬንውያንን ዘዴና ስልት በተግባር ከማዋላችን በፊት ጎርፍ ጠራርጎ የጣለብንን ጠላቶች ሰብስበን ለመጣል በህብረት በአንድነት መታገልን መማር ይገባናል፣ መቻቻልን መደማመጥን፡መተማመንን ዋጋ እንስጠው፣ ሁሉም ሰው በተገቢው ስፍራ ከተገኘ ጠቃሚ ስለሆነ እርስ በአርሳቸን መናናቅን ትትን፣ መከባበርን፣ መቀራረብን፣ እንልመድ። በአንድ የነጻነት ትግል መሳሪያ አንግቶ የተዋጋ፣ ለተዋጊው ውሀ ያቀመሰ ምግብ ያቀረበ፣ የጠላትን አቀማመጥ ተመልክቶ ወገንን ያስጠነቀቀ፣ ሁሉም የሚችለውን   ግዳጁን ከፈጸመ፣ ማቅረብ ማበረታት በጣም አስፈላጊ ስለሆነ የታጋይን ድካም አውቅና መስጠት የበለጠ ያጠናክረዋል። ከአመታት በፊት የተቃውሞ ትግላችንን ስንጀምር፣ ላንስማማ ስለተስማማን  አንዲት ጠቃሚ ነገር ሳንሰራ አስራ ሰባት አምታት አሳለፍን፣ ለዚህ ተጠያቂው እኛው ራሳቸን ስለሆን መለስን ልንውቅስ አንችልም፣ እርግጥ ነው መለስ ብዙ እንቅፋቶችን ደቅኖብናል ግን ተባብረን በመታገል ፈንታ አርስ በአርሳችን ስንጎሻሸም ስንነካክስ መለስ እየቀደመን ስለሄደ የበለጠ ተጠናክሮ ዛሬ ከአጁ  ለማምለጥ የማንችልበት ደረጃ ደርሰናል ።

መለስ ከአሜሪካ መንግስት በሚያገኘው ድጋፍ በመተማመን ምን እደረጋለሁ በማለት የልብ ልብ ስለተሰማው፣ ምርጫውን አጭበርብሮ ስልጣኑን ስለያዘ ፣ህዝቡ ተቃውሞ አቅርቦ ሰሚ ስለአጣ ወጣቶች በሰላማዊ ሰልፍ ተቃውሞ ቢያሰሙ በመልስ ትእዛዝ መሳሪያ ያነገቱ ወታደሮች ተኩሰው 193 ወጣቶችንና ስድስት ፖሊሶችን ስለገደሉ፣ መለስ ስለተኩሱ በሰጠው መግለጫ ተማሪዎች ወታደሮቼ ላይ ደንጋይ ስለወረወሩ የእነሱን ደህንነት ለመጥበቅ እንዲተኩሱ አዝዢያለሁ ይህም ትክክል ነው። በማለት ነፍስ ገዳይነቱን አረጋገጠ። በዚህ ወንጀል ሳይወሰን የቅንጅት መሪዎችን በሙሉ አስሮ በር ዘጋባቸው፣ ይህ ሁሉ በደል ሲሰራ በኢትዮጵያ ያሉ ኢምባሲዎች ወይም የውጭ አገር መንግስታት አንድም የተቃውሞ መግለጫ አላወጡም። መለስ ዜናዊ ይህንን ወንጀል የፈጸመው የአሜሪካንን መንንግስት በመተመመን ሲሆን የምአራብ መንግስታት መለስን ለመቃወም ምንም የወሰዱት እርምጃ አልነበረም ምክንያቱም መለስ የአሜሪካ ቅጥረኛ ታማኝ አገልጋይ ስለሆነ መለስን መንካት አሜሪካንን መቃውም ስለሆነ ድምጻቸውን አጥፍተው ተቀመጡ። የአሜሪካ መንግስት ራሱን የአለም ፖሊስ አድርጎ ስለሾመ፣ ሽብረተኛ አለ በሚባልበት አካብቢ አሜሪካ እየተከታተለ ሲገል በመጀመሪያ በራሱ ወታደሮች በኋላ  የናቶ አባል አገሮች በገደላው እንዲካፈሉ ስለጠየቀ አደጋ በማይበዛበት አካባቢ ወታደሮቻችውን መላክ ሲገደዱ፣ አንድ ወታደር ሲገደልባቸው፣ ወታደሮቻችንን እናስወጣለን ይላሉ፣ ይህም ቢሆን የናቶ አገሮች እንደ አሜሪካ በአለም ህዝብ አንዳይጠሉ ጥቃቅኑን ስራ እየሰሩ ከባዱን የገደላ ወንጀል ለአሜሪካና ለቅጥረኛው       ለመለስ ዜናዊ ለቀዋል፣፣

መላው አለምና የአውሮፓ መንግስታት በአኛ ምርጫ ድምጻቸውን አጥፍተው ሲቀመጡ ኬንያ በደረሰው ችግር ሁሉም ተንጫጩ፣ የአውሮፓ ህብረት አርች የኮመን ዌልዝ አባል አገሮችና ሌሎቸም እረፍት ሳያደርጉ የኤኮኖሚ ማእቀብ አናደርጋለን እያሉ ያስፈራሩ ነበር፣ እነዚህ አገሮች ይህንን እርምጃ ለመውሰድ የተገደዱት ኬንያ ውስጥ ብዙ ሀብት ስለአፈሰሱ ከእጃቸው እንዳይወጣ፣ በተጨማሪም የኬንያ መንግስት የአሜሪካ ቅጥረኛ በመሆን ሽብረተኞችን ለመግደል እንደማይፈልግ ስለተገነዘቡ ሳይሆን አይቀርም።ኢትዮጵያ  በአለም አንድም ወዳጅ እንደሌት የተረዳነው በምርጫው ሰሞን ነበር፣ አሁንም ቢሆን ወዳጅ የለንም፣  ኢትዮጵያ ለአፍሪቃ አገሮች በተለይም ለደቡብ አፍሪቃ ከቅኝ ገዢዎች ነጻ ኣንዲወጡ ከፍ ያለ አስትዋጽኦ አድርጋለች፣ ግን አንድም የአፍሪቃ መሪዎች ሊያጽነኑን ሊለዱን አልፈልጉም። በተለይም ከደቡብ አፍሪቃ መሪ
ከፕሬዜዳንት ኒልሰን ማንደላ ብዙ ጠብቀን ነበር። በደቡብ አእፍሪቃ የነበረው የአፓርታይድ አገዛዝ ተውግዶ ዛሬ በአገራቸን በጥቁር መሪ አፓርታይድ ስንሰቃይ  ሁሉም የውሀ ሽታ ሆነው ቀሩ፣ ይህ የሆነበት ያለ ምክንያት አይደለም፣ አንደኛ መለስን ቢቃወሙ የአሜሪካ መንግስት የሚሰጣቸውን አረዳታ ያቆምባቸዋል፣ ሁለተኛ ቁጥራቸው ሀምሳ የሚበልጡ የአፍሪቃ መሪዎች ለኢምባሲዎቻቸው የጽህፈት ቤቶች የሚሰሩበት ሰፋፊ ቦታ መለስ ስለሰጣቸው ምስጋና ቢስ ለመሆን አይፈልጉም ። ለአገራቸው ታላላቅ ስራ የሰሩ ጀግኖች ለመታሰቢያ በስማችው የተሰየመላችው የጎዳና ስም በአፍሪቃ አገሮችህ ስም በመለወጡ በጣም ያሳዝናል።መለስን የእነዚህ ጀግኖች አጽም ይፋረደዋል። እኛ አሁን ከመለስ ጋር አስታርቁን ብለን ብንጠይቅ አስታራቂ አናገኝም፣ ምክንያቱም እኛ እርስ በርሳችን ለመስማማት ስለአልቻልን፣ በራሳቸን ድክመት ሌላው ሊያምነን ስለማይችል አይቀርበንም። ይህ ለእኛ ትልቅ ውርደት ነው፣ ከአገርና ከህዝብ የበለጠ ነገር የለም፣ አገር ሲጠፋ ህዝብ ሲችገር፣ አዛውንት ሰብሳቢ አጥተው በጸሀይና በዝናብ በብርድና በረሃብ ሲንገላቱ፣ በኤድስ በሽታ ወላጆቸቸው የሞቱባችው ህጻናት በየሜዳው ፈሰው ሲያለቅሱ፣ ሞፈርና ቀንብር ተሽክሞ በከፈለው የግብር ገንዝብ ያስትማረን አባት ጧሪ አጥቶ በየመስጊዱ በየ ቤተ ክርስቲያኑ ተረፍርፎ  ምነው አምላክ ሞቴን ብታሳምረው እያለ አንባውን ሲያፍስ፣ በአንቀልባዋ እኛን አዝላ በጭንቅላቷ ውሀ የሞላበት ማስሮተሽክማ ያሳደገች አናት፣ ትምሀቱን ጨርሶ ስራ በማጣት አደገኛ ቦዝኔ በመባል በየአስር ቤቱ የሚንገላታው ትንሹ ወንድማቸን፣ ከእናቷ ጉያ መለየት የማይገባት ትንሿ አህታችን የመኖር ዘዴ መንገዱ ጠፍቷት ጊዜ ላመጣቸው ሀብታሞች እርቃነ ስጋዋን ስትደንስ ታድራለች። በህዝባቸን ላይ የሚሰራውን ግፍና በደል እያወቅነው በቸልታ የምንመለከተው አስክ መቼ ድረስ ነው? መለስ መዋሸት ስለማይታክተው ኤኮኖሚያቸን በስመንት አጅ አድጓል፣ በተለይም ወደ አሜሪካ ያምንልከው እቃ ከቀረጥ ነጻ ስልሆነ ትርፋቸን አጅግ ክፍ ያለ ነው፣ ቢልም ተጠቃሚው መለስና ግብረ አበሮቹ ሲሆኑ ህዝቡ በስሙ ተነገደበት ኣንጂ ያገኘው ጥቅም የለም፣፣

መለስ የአሜሪካ ታማኝ አገልጋይ በመሆኑ ዘመናዊ  የሆኑ የጦር መሳሪያዎች ስለአገኘ ጦርነት ለመክፈት ምክንያት እየፈለገ ነው፣ በሌላ በኩል ህዝባችን በአገሩ ባይተዋር፣ የበላተኝ ተመልካች፣ በሁለተኛ ደረጃ የሚተዳደር ዜጋ፣ እንደ ቅኝ ተገዥ ሰርቶ አፍርቶ ለበላተኛ ማቅረብ ከተገደደ፣ አገልጋይ ሆኖ የሚኖረው አስክ መቼ ድርስ ነው?  አኛ የጠር መሳሪያ የለንም አያስፈልገንም። መለስ ራሱ ፈሪ ሆኖ እኛንም ፈሪ አድርጎ አስቀረን፣ ጎበዝ ቢሆን ኖሮ ለአስራ ሰባት አመታት እንደ አይጥ ተደብቆ ባልኖረ ነበር፣ በምርጫው ምክንያት ሁለት መቶ ወጣቶች ስለገደለብን የዚያ ፍራቻ ስነ ልቦናችን ወስጥ ተቀምጦ የበለጠ ፈሪዎች ስለአደረገን እኛ እሱን፣ አሱ እኛን፣ በመፈራራት አይጥና ድመት ሆነን ኖረናል፣ በዚህ አይነት ለመኖር ስለማንችል አሁን እኛ መለስን ከሥልጣን ማስወገድ ይገባናል። መለስ ከጥይት የበለጠ የሚፈራው ሰላማዊ ሰልፍን ስለሆነ ይህንን በያዝነው 2000 ዓ.ም  ማድረግ ሲገባን የሚያስፈልገን  አንድ ጠንካራ መሪና ወኔ ያለው ህዝብ ነው፣ የኬንያ ህዝብ በአንድ ሺህ ህይወት በድምጹ ያሸነፈውን መብት ለማስከበር ከቻለ ፣ እኛ ካስፈለገ አስር ሺህ ህይወት ለመሰዋት መዘጋጀት አለብን፣ ይህንን ለማድረግ ካልቻልን ፈሪዎች መሆናችንን ለኢትዮጵያ ህዝብ በይፋ ገልጸን ምርጫውን ራሱ እንዲወስን እናድርግ፣ፈሪዎች ሆነን ከመኖር እየታገልን ብንሞት ይሽለናል! የኢትዮጵያ አምላክ ብርታቱንና ድፍረቱን ይስጠን፣፣   ፍራንክፉርት መጋቢት 30 / 2000  09.03.2008






Reddit!Del.icio.us!Facebook!Slashdot!Netscape!Technorati!StumbleUpon!Newsvine!Furl!Yahoo!Ma.gnolia!Free social bookmarking plugins and extensions for Joomla! websites! title=
Comments (0)Add Comment

Write comment
quote
bold
italicize
underline
strike
url
image
quote
quote
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley

security code
Write the displayed characters


busy
 


Quick Jump

Ethio Date & Time

ዛሬ ቀኑ:

Calendar Converter




Daylight Saving