RSS 2.0 Email us: webmaster@mahder.com

Ethiopia: Mahder.com -Ultimate Ethiopian News and Information Portal

Saturday
Nov 22nd
Home arrow News arrow የኘሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የጎሣ ፖርቲ ያጣጥራል፡፡
የኘሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የጎሣ ፖርቲ ያጣጥራል፡፡ Print E-mail
Wednesday, 19 March 2008
ከታዲዎስ ታንቱ፣

    በዓላማ ሳይሆን በዘር ተደራጅቶ ለአሥራ ስድስት ዓመታት በኘሮፈሰር በየነ ጴጥሮስ መሪነት ሲንቀሳቀስ የቆየው 14 ጎሳዎች በአባልነት የሚገኙበት የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ሕብረት በሚል ስያሜ የሚጠራው የጎሳ ፖርቲ በአሁኑ ወቅት ሊሞት እንደሚያጣጥር ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

 

   እንደ ውስጥ አዋቂ ምንጮች አገላለፅ ፖርቲው አሥራ ስድስት ዓመታት ፈጽሞ ጠቅላላ ጉባዔ ያላካሔደ ከመሆኑም በላይ ኘሮፈሰሩ ከፖርቲው ይልቅ ራሳቸውን አገዝፈው ለማሳየት የሚያደርጉት ጥረት ፖርቲውን ለዚህ ውድቀት እንደዳረገው ተመልክቷል፡፡

     በተዛመደ መልኩ ኘሮፈሰሩ የአመራር ችሎታ የሌላቸው ሲሆን፣ለፖርቲያቸው ትኩረት ከመስጠት ይልቅ ለራሳቸው ጎሳ ኑሮ መሻሻል አበክረው ሰለሚጨነቁ ፖርቲው እንደተጎዳ የሚናገሩ ጥቂት አይደሉም፡፡

    በዚህ ምክንያት በአሁኑ ወቅት አንዳንድ የሕብረቱ አባል ጎሳዎች ሕብረቱን ለቅቀው የወጡ ሲሆን ሌሎችም ለመውጣት እየተዘጋጁ መሆናቸውን የመረጃ ምንጮቻችን አክለው አስረድተዋል፡፡

    ኘሮፈሰር በየነ በወያኔ ፖርላማ ጥልቀት በሌላቸው ሐሳቦች የቃላት ጂምናስቲክ በመሥራት የሚታወቁ ሲሆን በቅርቡ ደግሞ ለሥርዐተ አገዛዙ ኘሬዝዳንትነት ተወዳድረው የወደቁ መሆናቸው ይታወሳል፡፡

    ግለሰቡ በ1988 ዓ/ም ተቋቁሞ አንዳች ቁም ነገር ያልሰራውን አማራጭ ኃይሎች የተባለውን ስብስብ ሲመሩ የቆዩ ሲሆን፣ ሰብስቡ በአሁኑ ወቅት ሕልውናው በራሱ ጊዜ በመክሰሙ የምስክር ወረቀቱን ወስደው ለምርጫ ቦርድ መመለሳቸውንም ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ለማወቅ ተችሏል፡፡

    ሰውየው በወያኔ ሹማምንት ተገምግመው በቅርቡ ኘሮፈሰርነት ከማግኘታቸው በፊት በወያኔ የረዳት ኘሮፈሰርነት ማዕረግ ተሰጥቷቸው በጎሳ አገዛዝ መርህ በተቀረፀው የትምህርት ፖሊሲ ሥርዓተ-አገዛዙን ሲያገለግሉ ኖረዋል፡፡    ኤርትራን ከኢትዮጵያ ለማስገንጠልና ኢትዮጵያን የባሕር በር ለማሳጣት በ1983 ዓ/ም በወያኔ የተረቀቀውን ቻርተር ተሽቀዳድመው የፈረሙት እኚህ ግለሰብ የሥርዓተ-አገዛዙ የትምህርት ማኒስቴር ምክትል ሚኒስቴር ሆነው አገዛዙን በታማኝነትና በቅንነት ለዓመታት ማገልገላቸውም ይታወሳል፡፡




Reddit!Del.icio.us!Facebook!Slashdot!Netscape!Technorati!StumbleUpon!Newsvine!Furl!Yahoo!Ma.gnolia!Free social bookmarking plugins and extensions for Joomla! websites! title=
Comments (1)Add Comment
...
written by ethiopian lover, March 21, 2008
I find this article very illogical. Prof. Beyene might have worked to please the current regime, but he is a man who loves his country, unlike the writer of this article, the professor is currently working IN Ethiopia for the betterment of the country, by educating the youth. The education policy might not be that much applauded, but still people are getting education...Please be objective as much as possible when critizing someone.

Write comment
quote
bold
italicize
underline
strike
url
image
quote
quote
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley

security code
Write the displayed characters


busy
 


Quick Jump

Ethio Date & Time

ዛሬ ቀኑ:

Calendar Converter




Daylight Saving