|
ኢንጅነር ኃይሉ የቅንጅት ኮሚቴ ሰብሳቢዎችን አነጋገሩ፣ |
|
|
|
Sunday, 13 April 2008 |
|
ከታዲዎስ ታንቱ ኢንጅነር ኃይሉ ሻውል የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፖርቲ ኘሬዝዳንት የጎፋ ልዩ ዞን የቅንጅት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትንና የዞኑን የሰባት ወረዳ የፖርቲው ኮሚቴ ሰብሳቢዎችን ከዋሸንግተን ዲሲ መጋቢት 28 ቀን 2ዐዐዐ ዓ/ም በስልክ አነጋገሩ፡፡ ኘሬዝዳንቱ በዚሁ ዕለት ከዞኑ የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፖርቲ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ሰፊ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ ለቀረበላቸው ልዩ ልዩ ጥቄዎችም በማብራራት መልስ እንደሰጡ ከሥፍራው ከደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡
በመቀጠልም ኘሬዝዳንቱ በዞኑ ውስጥ ለሚገኙ ለደምባ ጎፋ፤ለሣውላ ከንቲባ፣ ለአይዳ፣ ለበስኬቶ ፣ ለመሎ ኮዛ፣ለዑባ ጥንስስና ለዛላ ወረዳዎች የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፖርቲ ኮሚቴ ሰብሰሳቢዎች የፖርቲውን የወቅቱን እንቅስቃሴ እንዲሁም በቅርቡ የሚካሄደውን ጠቅላላ ጉባዔ በማስመልከት ገለጻ ያደረጉላቸው ሲሆን ከገለጻው በኋላ ለተነሱ ልዩ ልዩ ጥያቄዎችም በማብራራት ተገቢውን መልስ ሰጥተዋል፡፡ ኘሬዝዳንቱ ከጎፋ ልዩ ዞን የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፖርቲ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች ጋር ሊወያዩ የቻሉት እነሱ ራሳቸው ያቀረቡትን ጥያቄ መሠረት በማድረግ የፖርቲው ጽ/ቤት የግንኙነት ኘሮግራሙን በማመቻቸቱ መሆኑን የመረጃ ምንጮች አክለው ገልፀዋል፡፡ የጎፋ ልዩ ዞን የልዩ ልዩ ወረዳዎች የኮሚቴ ሰብሳቢዎች በኘሬዝዳንቱ ገለጻና ማብራሪያ ፖርቲው ሰለሚገኝበት ሁኔታ ተገቢውን ግንዛቤ በመጨበጣቸው በአሁኑ ወቅት ለማንኛውም ዓይነት ከፋፋይ እንደማይንበረከኩ ገልጸው በተረጋጋ ስሜት የጉባዔውን ቀን በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውንም ለቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ጽ/ቤት በስልክ አረጋግጠዋል፡፡
|