RSS 2.0 Email us: webmaster@mahder.com

Ethiopia: Mahder.com -Ultimate Ethiopian News and Information Portal

Saturday
Nov 22nd
Home arrow News arrow አንጀው በአርባ ምንጭ ደመወዝ እከፍላለው እያለ ነው
አንጀው በአርባ ምንጭ ደመወዝ እከፍላለው እያለ ነው Print E-mail
Saturday, 19 April 2008

ከታዲዎስ ታንቱ፣

አንጀኞች በአርባ ምንጭ የቅንጅት

ኮሚቴን አቋም ለማስለወጥ ሞክረው ከሸፈ፡፡

   ከቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፖርቲ አፈንግጠው በአንጀኝነት ከወጡ ጥቂት የፖርቲው የቀድሞው አመራር አባላት የተላኩ ግለሰቦች በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ከተማ የቅንጅት ኮሚቴ አባላትን አሳስተው አቋም ለማስለወጥ በልዩ ልዩ ስልት ያደረጉት ሙከራ ሰሞኑን ከሸፈ፡፡

 

   በዚህ ሒደት አንጀኞቹ ወደ ፊት የእነሱ ፖርቲ ሕጋዊ ሰውነት ሲያገኝ ሁሉም የኮሚቴ አባላት በደመወዝ እንደሚተዳደሩ በመግለፅ ላገUቸው አንዳንድ የኮሚቴ አባላት ባዶ ተስፋ የሰጧቸው ሲሆን፣ በመቀጠልም አሁንም መሪያቸው ኢንጂነር ኃይሉ ሻውል እንደሆኑ አስመስለው በየቦታው በማስወራት ኮሚቴው ወሬአቸውን አምኖ በመቀበል በአስቸኳይ አቋሙን በመለወጥ ከእነሱ ጋር እንዲያብር ብዙ እንደጣሩ የአርባ ምንጭ የመረጃ ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡

   አንጀኞቹ አያይዘው የውጭ ድጋፍ እንዳላቸው ተናግረው የሚያቋቁሙት ፖርቲ የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፖርቲን ዓላማ እንዲሁም ኘሮግራም እንደሚያራምድ በማስረዳት የአንጀኝነት ተልዕኮአቸውን በአስመሳይ ቃላት ሸፋፍነው ድጋፍ ለማግኘት እንደሞከሩ ታውቋል፡፡

   የዞኑ የኮሚቴው አባላት ግን የቀረበላቸውን አሳሳች ተስፋ ውድቅ አድርገው ቅንጅት አንድ መሆኑን ዳግም በማረጋገጥ የአንጃ ተላላኪዎችን አሳፍረው እንደመለሷቸው የመረጃ ምንጮቻችን አመልክተዋል፡፡

  የጋሞ ዞን አሥር ወረዳዎች ሲኖሩት በአሥሩም ወረዳዎች የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፖርቲ ኮሚቴዎች በተግባራዊ እንቅሰቃሴ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡

   ይህ በእንዲህ እንዳለ አቶ ተፈራ ፈለቀ በጎፋ ልዩ ዞን የበስኬት ወረዳ የቅንጅት ለአንድትና ለዴሞክራሲ ፖርቲ ኮሚቴ ሰብሳቢ መኖሪያ ቤት ሚያዝያ 1 ቀን 2ዐዐዐ ዓ/ም ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በፖሊስ ተበረበረ፡፡

   በዚሁ ዕለት ፖሊሶች በቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፖርቲ ጽ/ቤት በር ላይ ይውለበለብ የነበረውን የኢትዮጵያ ባንዲራ አውርደው ይዘው የሔዱ ሲሆን፣ ቀደም ሲልም ተመሳሳይ ድርጊት ፈጽመው እንደነበር ከመረጃ ምንጮች ለማወቅ ተችሏል፡፡ 

      አቶ ተፈራ ፈለቀ ከዚህ ቀደም ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሁለት ጊዜ ተይዘው በጠቅላላው ለሃያ ሶስት ቀናት ታስረው የተለቀቁ መሆናቸው ታውቋል፡፡




Reddit!Del.icio.us!Facebook!Slashdot!Netscape!Technorati!StumbleUpon!Newsvine!Furl!Yahoo!Ma.gnolia!Free social bookmarking plugins and extensions for Joomla! websites! title=
Comments (0)Add Comment

Write comment
quote
bold
italicize
underline
strike
url
image
quote
quote
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley

security code
Write the displayed characters


busy
 


Quick Jump

Ethio Date & Time

ዛሬ ቀኑ:

Calendar Converter




Daylight Saving