RSS 2.0 Email us: webmaster@mahder.com

Ethiopia: Mahder.com -Ultimate Ethiopian News and Information Portal

Saturday
Nov 22nd
Home arrow News arrow ከታዲዎስ ታንቱ - የመዲናችን ዕንባ
ከታዲዎስ ታንቱ - የመዲናችን ዕንባ Print E-mail
Saturday, 19 April 2008

 

   የመዲናችን ነዋሪ ሕዝብ አንዳችም ብሩህ ነገር በቅርብ ርቀት አያይም፡፡ ሕይወቱ ድቅድቅ ባለ ጨለማ ተውጧል፡፡ በሞትና በሕይወት መካከል ያለውን ልዩነት በልዩነት ለይቶ ለማስቀመጥ እንኳን መለኪያ አጥቷል፡፡፡ በቃላት ሊገለፅ ከሚቻለው በላይ ችግሮችን ለማስተናገድ ተገድዷል፡፡

 

   አቅርቦት ወደ አልቦ እርከን እየወረደ ይገኛል፡፡ ፍላጉት በጣም ተንጠራርቷል፡፡ የ"ገዢዎቻችን" የኢኮኖሚ ቀመር ከድህነት ቅነሳ በተቃራኒ መርህ ግቡን አግኝቷል፡፡ ብሶት የወለዳቸው ብሶተኛ ትግሬዎች በአሥራ ሰባተኛው ዓመት የዘውድ በዓላቸው ዋዜማ ላይ የሰማኒያ ሚሊዮን ሕዝብን ሆድ አስብሰዋል፡፡

    በአዲስ አበባ ከተማ የውኃ አጥረት ችግር አሻቅቧል፡፡ ጎሕ ሲቀድድ ፍለጋው ይቀጥላል፡፡ ማለዳ መነሳት የግድ ሆኗል፡፡ ጀሪካን፣ባልዲ፣እንሥራና ገምቦ ተሸክመው የሚርመሰመሱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን የትም ማየት ይቻላል፡፡ መኪኖችም በተመሳሳይ መልኩ ይንቀሳቀሳሉ፡፡ በየአቅጣጫው ይባዝናሉ፡፡ የሀገራችን ዋና ከተማ፣የአፍሪቃ ሕብረት፣የብዙ ዲኘሎማቶችና የአያሌ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች መቀመጫ በሆነችው በአዲስ አበባ ክተማ የውኃ እጥረት ችግር ዐቢይ የመወያያ ርዕስ ሆኗል፡፡ የዓባይ ጌታ በውኃ ጥም ደርቋል፡፡ የኦሞ፣የገናሌ፣ የዋቢ ሸበሌ፣የብላቴና የመሰል ወንዞች ባለቤት ውኃ አጥቷል፡፡

    በ"ገዢዎቻችን" ለችግሩ ሰበቦች ተቀርፀዋል፡፡ ቀዳሚው ሰበብ የሕዝብ ቁጥር መጨመር መሆኑ ተመልክቷል፡፡ በፍፁም ግን አያሳምነንም፡፡ እንዴት ሊሆን ይችላል? ራሱን መንግሥት አድርጎ ያስቀመጠው የትግሬዎች ቡድን ሕዝብን በደሙ ነፍስ ይገዛል እንዴ? በዕቅድና በመርሐ-ግብር ማስተዳደር እንዳለበት ይገባናል፡፡ ከዕቅድ ውስጥ ደግሞ የሕዝብ ቁጥር ትንበያ ይካተታል፡፡ ዓመታዊ የሕዝብ ፍልሰት ይታሰባል፡፡ ምን ያህል ይወልዳል? ምን ያህልስ ይሞታል? ተመሳሳይ ሌሎች ጥያቄዎችም ይነሳሉ፡፡ የወያኔ ቡድን ሹማምንት ከእነርሱ በላይ ብልጥ ያለ አይመስላቸውም፡፡ ለሰንካላ ዕቅዳቸው የሕዝብ ብዛትን በሰበብነት አንቀበልም፡፡ ዘረኝነት የወለደው ችግር ነው፡፡ ያለ ችሎታ በዘር ኮታ የተቀመጡ ሹማምንት በራሳቸው የችግሩ አካል ናቸው፡፡ ሰበብ አያስፈልግም፡፡

አገዛዙ ሲወገድ ብቻ ችግሩ ይወገዳል፡፡ የአዲስ አበባ ሕዝብ ይህን ጠንቅቆ ያውቀዋል፡፡

   " ገዢዎቻችን" የግንባታ ተግባራዊ እንቅስቃሴን በሰበብነት ያስቀምጣሉ፡፡ ሁለተኛው ምክንያታቸው ይህ ነው፡፡ ህብረተሰቡ ግን ምክንያታቸውን ውድቅ አድርጓል፡፡ ሥራ በዕቅድ መሆን እንዳለበት ህብረተሰቡ የግንዛቤ ችግር የለበትምና፡፡ ትግሬዎች ማንንም ለማሞኘት አይችሉም፡፡ የግንባታ ዘርፍ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች የውኃ ፍጆታ መጠን ከዕቅድ ውስጥ የማይገባበት ምን ምክንያት አለ? ትግሬዎች ራሳቸውን በመንግሥትነት እርከን አስቀምጠው ይህን በምክንያትነት ማቅረብ አልነበረባቸውም፡፡ ዕቅዶች በየፈርጁ ብዙ ነገሮችን ሊያካትቱ ይገባል፡፡ ውኃ ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም መሠረታዊ አገልግሎቶች በዕቅዶች ውስጥ ማስገባት የመንግሥት ግዴታ መሆኑን "ገዢዎቻችን" ያጣሉ ብለን አንገምትም፡፡ ሰለሆነም የአዲስ አበባ ሕዝብ በውኃ እንዲያልቅ የግንባታ እንቅስቃሴ ሰበብ ሊሆን ከቶም አይገባም፡፡ ይህ የሕዝብ አስተያየት ነው! ትክክል!

   በመሠረቱ ዛሬ በአዲስ አበባ ውስጥ ግንባታዎችን የሚያካሔዱት ትግሬዎችና ጥቂት ለእነሱ በሎሌነት ያደሩ ብቻ መሆናቸውን የማያውቅ የለም፡፡ በግንባታዎች ሰበብ በጀግኖቹ ቀደምት ኢትጵያውያን ደምና አጥንት ተጠብቆ የኖረው መሬታችንም ከባንዳነት ያለፈ ታሪክ በሌላቸው ወገኖች ተቸብችቦ ሲያልቅ እያየን ነው፡፡ በቁማችን ሞተንና በሞታችን ቆመን ይህን አሳዛኝ ትርዒት ማየት ግድ ሆኖብናል፡፡ ትግሬዎች ደግሞ ይህን ደካማ ጎናችንን ጠንቅቀው ሰለሚያውቁ " እናንተ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ፎቆችን እየገነባን በመሆኑ የውኃ እጥረት የሚጠበቅ ነው!" ይሉናል፡፡ ይህ ትልቅ ድፍረት መሆኑን አንጣ፡፡ "ገዢዎቻችን"  ለሕዝብ ያላቸውንም ንቀት ፍንትው አድርጎ ያሳየናል፡፡ይህን ማን ሊክድ ይችላል?

   ይህ በእንዲህ እንዳለ የመብራት መቋረጥ የአዲስ አበባን ሕዝብ በጣም አስመርሯል፡፡ መብራት በመዲናችን ቢያንስ በሳምንት ለሁለት ቀናት ይቋረጣል፡፡ ምክንያቱ ምን እንደሆነ አይታወቅም፡፡ አንዳንዴም በአንዳንድ ቀበሌዎች መብራት ለሃያ አራት ሰዓታት ሲጠፋ ይስተዋላል፡፡ በዚህ ምክንያት የኮምፒውተርና የኢሜል አገልግሎት መስጫ ድርጅቶች በጣም ተማርረዋል፡፡ መዝናኛ ቤቶችም ቡናና ሻይ መሸጥ አልቻሉም፡፡ሰው ናቂው የትግሬዎች አገዛዝ ለችግሩ በመፍትሔ እርከን ያስቀመጠው አንዳችም አማራጭ የለም፡፡ እርግጥ ነው፡፡ የፈረቃ መርሐ ግብር ቀርጾዋል፡፡ ይህ ግን መፍትሄ አይደለም፡፡

   በሌላም በኩል የቅቤ ዋጋ በጣም ንሯል፡፡ በዚህም መሠረት ባለፈው ጥር ወር በብር 48.ዐዐ ይሸጥ የነበረው አንድ ኪሎ ቅቤ በአሁኑ ወቅት በብር 85.ዐዐ ሲሸጥ ይስተዋላል፡፡ የዋጋ ጭማሪው አሁንም ቀጥሏል፡፡ የጤፍና ጥራጥሬ ዋጋም እንደ ተሰቀለ ቀርቷል፡፡ በቅርብ ርቀት የሚታይ አንዳችም ብሩህ ተስፋ የለም፡፡ በፍፁም!

    በተዛመደ መልኩ የሞዴስ የዋጋ ንረት ሴት ተማሪዎችን ከትምህርት ቤት እያስቀረ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተለይም በዝቅተኛ ኑሮ ሥር የወደቁ ሴት ተማሪዎች ንፅሕናቸውን ለመቆጣጠር እንደተቸገሩ ተነግሯል፡፡ በአሁኑ ወቅት የትግሬዎች አገዛዝ በሞዴስና በተያያዙ በሴቶች ንፅሕና መጠበቂያ ዕቃዎች ላይ ቫት 15 በመቶ እንዲሁም የገቢ ቀረጥ 27 በመቶ ሰለሚያስከፍል የዋጋ ንረት ሊባባስ እንደቻለ ሙያዊ ነቃሽ ተመዝግቧል፡፡ በዚህ ምክንያት ደኃ ሴት ተማሪዎች የወር ወጋቸው እስኪነጥፍ ለሶስት አንዳንዴም ለአራት ቀናት ከትምህርት ቤት እንደሚቀሩ ታውቋል፡፡ ሴቶች በበኩላቸው የመፍትሔ ሐሳብ አስቀምጠዋል፡፡ የቫትና የገቢ ግብር እንዲነሳ ጠይቀዋል፡፡፡ ያም ሆነ ይህ የመዲናችንን ዕንባ አልታበሰም፡፡ ዋይታው ቀጥሏል፡፡ ችግሮች በየፈርጁ ተባስሰዋል፡፡ ትናንት ከዛሬ ተሽሏል፡፡

  






Reddit!Del.icio.us!Facebook!Slashdot!Netscape!Technorati!StumbleUpon!Newsvine!Furl!Yahoo!Ma.gnolia!Free social bookmarking plugins and extensions for Joomla! websites! title=
Comments (0)Add Comment

Write comment
quote
bold
italicize
underline
strike
url
image
quote
quote
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley

security code
Write the displayed characters


busy
 


Quick Jump

Ethio Date & Time

ዛሬ ቀኑ:

Calendar Converter




Daylight Saving