RSS 2.0 Email us: webmaster@mahder.com

Ethiopia: Mahder.com -Ultimate Ethiopian News and Information Portal

Saturday
Nov 22nd
Home arrow News arrow አሉባልታ ቢደጋገም የይዘት ለውጥ አያመጣም
አሉባልታ ቢደጋገም የይዘት ለውጥ አያመጣም Print E-mail
Sunday, 20 April 2008
አንዳንድ አቅመ ቢስ የግል ህትመቶች ሀገር ቤት ውስጥ ከአንጀኞች ድርጎ እየተጣለላቸው ቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፖርቲን በማውገዝ ተግባር ላይ ተሰማርተዋል፡፡" በጌታዋ የተማመነች በግ.........." እንዲሉ ማስተባበያ ብንፅፍላቸው ለማውጣትም ፈቃደኝነት ሳያሳዩ ቀርተዋል፡፡ ሰንደቅ ተብዬ ጋዜጣ ካሰፈረው አሉባልታ በውስን እርከን በቅደም ተከተል ቀንጭቤ መልስ አለኝ፡፡ ሰለዚህ አንዳንድ የአንጀኞች አጋር ግለሰቦች ከአፍራሽ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ አሊያም የዋሆች ከብዥታ ጉም እንዲላቀቁ መጣጥñ ፋይዳ የሚኖረው ይሆናል ፡፡መረጃ ነውና እነሆ!

              አሉባልታ ቢደጋገም የይዘት ለውጥ አያመጣም፣

ከታዴዎስ ታንቱ ፣

 

  

     

     በሰንደቅ ጋዜጣ የካቲት 26 ቀን 2ዐዐዐ ዓ/ም ታዲያ ታፔላው ሐውልት ይሆን? በሚል ጥያቄያዊ ርዕስ ሥር ተሰማ ዘርጋው ከተባሉ ግለሰብ የቀረበ መጣጥፍ ቢጤ አንብቤአለሁ፡፡ ግለሰቡ በአጻጻፋቸው ለአሉባልታ የምሥክር ወረቀት የታጠቁ ይመስላሉ፡፡ ጽሑፋቸው በዐረፍተ ነገር ደረጃ ብቻ ሳይሆን በሐረግ እርከን እንኳን የአሉባልታ ይዘት ሰንቆ ተደራጅቷል፡፡ በአሉባልታቸው መነሻ አንቀጽ አንድ ላይ መግቢያ ሲከፍቱ ያስቀመጡትን በቅድሚያ ቀንጭበናል፡፡ እንዲህ ይነበባል፡፡

            ህዝባዊ ዓላማ አንግቤ ተነስቻለሁ የሚል ግለሰብ ወይም ቡድን በስም   ማጥፋትና በኘሮፖጋንዳ ሽፋን የትም ሊደርስ አይችልም፡፡ በዚህ ታሪካዊ ህዝብ መካከል ሆኖ መልክን እየለዋወጡ አይደረስብንም በማለት የትም ማምለጥ አይቻልም፡፡

   ፀሐፊው የሚናገሩትን በውል ለማወቃቸው ጥርጣሬ አለኝ፡፡ ካወቁ ይህን ሰፊ

ፅንሰ-ሐሳብ ያመቀ አባባል  መግቢያ ለማድረግ ለምን ፈለጉ? ምን ማለታቸው ይሆን? ስም አጥፊው ማነው? የማንስ ስም ጠፋ?የኘሮፖጋንዳ ሽፋን የተሰጠውስ በማን ላይ ነው?    

     የረቡዕ ፀሐፊ ማንን ዒላማ አድርገው እንደጻñም አያውቁም፡፡ ለመጻፍ ያህል መጻፍ በኛ አተያይ ሥራ ፈትነት ነው፡፡ የአሉባልታ ድሪቶ ለሀገርና ለሕዝብ ምንም አይፈይድም አንድ ህትመት ግልፅ መልዕክት ማስተላለፍ ይጠበቅበታል፡፡ መልኩን የለዋወጠው ማነው? መልክ መለዋወጥስ በራሱ ምን ማለት ነው ?ፀሐፊው ሰለ ታፔላው ጥያቄ አቀረቡ ፡፡ ወዲያው ደግሞ ሰለ ስም ማጥፋትና ኘርፖጋንዳ ጠቀሱ፡፡ በመቀጠል ሰለመልክ መለዋወጥ ይነግሩናል፡፡ ሕዝቡ ታሪካዊ መሆኑንም እገረ መንገዳቸውን አንስተዋል፡፡ በተዘበራረቀ ጭብጥ አሉባልታቸውን እየደረቱ ወረዱ፡፡ ለመሆኑ ፀሐፊው ጤነኛ ናቸው? የአሉባልታ ሱስ የተጠናወታቸው እኚህ የረቡዕ ፀሐፊ በመጠቀል ደግሞ፣

             የቅንጅት ሶስት ተጠሪ ወይም እንደራሴ አቶ አባይነህ ብርሃኑ ሰለሰርተፊኬቱ ጉዳይ ማስተባበያውን ቢሰጡ ኖሮ ሃላፊነታቸውን እንደተወጡ በቆጠርኩ ነበር፡፡ መጀመሪያ ነገር ቅንጅት ሶስት በተከፋፈለው ፖርቲ ውስጥ አናሳ ቡድን መሆኑ እየታወቀ ራሱን የዲሞክራሲ ዋልታና ማገር አድራጊና ፈጣሪ ታማኝ አድርጎ ሲመጻደቅ ሌላውን የማሰብ የመወሰንና የመምራት መብት ኃላፊነትና ግዴታ እንደሌለው አድርጎ መቁጠሩ አስገራሚ አይደለም፡፡ 

    በመሰረቱ ቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፖርቲ በኢንጅነር ኃይሉ ሻውል የሚመራውና መስከረም 14 ቀን 1998 ዓ/ም ውህደት የፈጸመው ነው፡፡ ይህን ደጋግመን ተናግረናል፡፡ ሰለዚህ ቅንጅት አንድ ነው፡፡ አሁንም የምንለው ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡ በግልጽ ቋንቋ ተናግረዋል፡፡ ሁለት ቅንጅት የለም፡፡ በሶስት ረድፍ የሚመደብ ክፍፍልም ሊኖር አይችልም፡፡ ፀሐፊው እንደ ሰው የሚያስቡ ከሆነ የምንናገረው ሊገባቸው እንደሚችል ይታመናል፡፡ ቅንጅት አንድ ነው፡፡

    የአሉባልታ ሕመም መጥፎ ደዌ ነው፡፡ በእኛ በኩል ፈውስ እንዲያገኙ ብዙ ጥረት አድርገናል፡፡ በሚመለከተን ሁሉ ተገቢውን ወቅታዊ መረጃ ደጋግመን ሰጥተናል፡፡ በኢንጂነር ኃይሉ ሻውል የሚመራው ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፖርቲ አናሳ ቡድን አይደለም፡፡ ለመሆኑ አናሳ ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ፀሐፊው በውል ያውቁ ይሆን?አንድ ፖርቲ በምሉዕ ቅርፁና ይዘቱ እንዳለ እንዴት አናሳ ሊባል ይችላል? ፀሐፊው ቢያንስ እንዴት የመጠነኛ ግንዛቤ ደኃ ይሆናሉ? አያ ፀሐፊ ማነው አናሳ መሆናችንን የነገረዎት?በደመ-ነፍስ ምስክርነት አለ እንዴ? መረጃ በዕውነት ላይ የተመሰረተ መሆን ይኖርበታል፡፡

   እንደ ትናንቱ ሁሉ ዛሬም የኢትዮጵያ ሕዝብ ከእኛ ጋር በተግባር ተሰልፏል፡፡ የቅንጅት ዓላማ የሕዝብ ነው ፡፡ ሕዝብ ይህን ጠንቅቆ ያውቀዋል፡፡ ማንም ሊነግረው አይገባም፡፡ ከሕዝባችን ጋር ሆነን ዴሞክራሲን በዚህች ሀገር ዕውን ለማድረግ በዓላማ ፅናትና በቁርጠኝነት በመንቀሳቀስ ላይ ነን፡፡ የህትመት አሉባልታ የወረቀት ነብር ነው፡፡ የሌሎችን የማሰብ የመወሰንና የመምራት መብትም እናከበራለን፡፡ በዚህም መሠረት ጥቂት የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፖርቲ፣አፈንጋጮች በመረጡት መስመር ነጉደዋል፡፡ አዲስ ፖርቲ ለማቋቋም ማመልከቻ ለሚመለከተው አካል ገቢ አድርገዋል፡፡ አንዱ መሪ ሌላው ተመሪ በመሆን ይንቀሳቀሱሉ፡፡ እኛ የራሳችንን ቅዱስ ዓላማ ከማራመድ በስተቀር የሌሎችን መብት ፈጽሞ አልነካንም፡፡ ፀሐፊው ለአሉባልታቸው ማሟያ የሐሰት ነዶ ያስራሉ፡፡ ከኋላቸው ሆኖ ወረቀት እንዲያዥጎረጉሩ የሚገፋፋቸው አንጃው ነው፡፡ ግን ቢያስቡበት መልካም ነው፡፡ ከአሉባልታ ማትረፍ አይቻልም፡፡ ሰለሆነም ከመነሻው መክሰራቸውን ሊረዱ ይገባል፡፡ የሰንደቅ የረቡዕ ፀሐፊ አያይዘው ደግሞ እንዲህ ይላሉ፡፡

              ...............የመኢአድ ስም የተጻፈበት ትልቅ ማስታወቂያ /ታፔላ/ በጽ/ቤቱ በራፍ መቆሙና አሁንም ድረስ መታየቱ ገሃድ ነው፡፡ ቅንጅት መስከረም 14 ቀን 1998 ዓ/ም ውህደቱን ከፈጸመ እስከ አሁን ሁለት ዓመት ተኩል ሆኖታል፡፡ አመራሮቹ ከተፈቱ ደግሞ ከ8 ወር በላይ ቢሆናቸውም አሁንም በቅንጅት ስም የሚምሉና የሚገዘቱ ግለሰቦች እስከ አሁን ድረስ ታፔላውን አላነሱትም፡፡ ታዲያ ታፔላው ሐውልት ነው?

     ተራ ወሬ ለሕዝብ አንዳችም አይፈይድም፡፡ ፀሐፊው ምን መረጃ ለመስጠት ፈልገዋል? ሕዝብ የሚያውቁውን መልሶ ለሕዝብ መንገር ሥራ ፈትነት ነው፡፡

   በሕዝብ ቤት በራፍ ላይ የተሰቀለውን ታፔላ አዲስ ግኘት አድርገው በህትመት ያውጃሉ እንዴ? ታፔላው እንደ ተሰቀለ የጥምረቱ ተልዕኮ ተሳክቷል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ውህደቱ ተካሂዷል፡፡ ታፔላው በፖርቲው ራዕይ፣ዓላማና ተልዕኮው ላይ ያመጣው አንዳችም አሉታዊ ተጽእኖ አልነበረም፡፡ ግልፅ ነው! የወሬ ዐመል ያለበት ምንጊዜም ለወሬ ሟች ይሆናል፡፡ የምንፈልገው ለሕዝብ ተገቢውን መረጃ የሚመግብ ህትመት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡ በአሉባልታ ሀገር አይገነባም፡፡ ፀሐፊው አለማወቃቸው አክለው ሲገልፁ ደግሞ "....ታፔላው ሐውልት ነው?" ብለዋል፡፡ እንዴ! ምን ማለታቸው ነው?ሐውልት ይፈርስ የለ እንዴ? የጋራ መታሰቢያ ያልሆኑ ሐውልቶች ሁሉ እንዲፈርሱ የግድ ነው፡፡ ሐውልትኮ ሰለተፈለገ ብቻ አይታነፅም፡፡ ሐውልት ትውልድን ወክሎ ይታነጻል፡፡ ሐውልት ይናገራል"፡፡ ሐውልት ይመሰክራል፡፡ፀሐፊው ይህን ማወቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ፀሐፊው በታፔላውና በሐውልት መካከል ያለውን ልዩነት ካላወቁ ልናስረዳቸው ዝግጁ ነን ! ይህን ሊያውቁት ይገባል፡፡ አሉባልታ የአሉባልተኛውን ልክ ይናገራል፡፡ የህትመት ውጤቶች ደግሞ ሕዝብን የሚያቀራርቡ፣ አንድነትን የሚያጎለብቱ፣መተሳሰብንና መከባበርን የሚያበረታቱ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ የረቡዕ የሰንደቅ ፀሐፊ ብዕር ከወረቀት ከማዋሐዳቸው በፊት ደጋግመው ማሰብ እንደነበረባቸው ይሰማናል፡፡ ታፔላን ትልቅ የሀገር አጀንዳ አድርጎ ማውራት በእኛ አተያይ ዝቅ ያለ ስብዕናን ያመለክታል፡፡ ንትርክ አያስፈልግም፡፡ ከአሉባልታ ምን ለማትረፍ እንደታሰበ የሚያውቁት ፀሐፊው ራሳቸው ብቻ መሆናቸውን አንዘንጋ፡፡

     ፀሐፊው በጽሑፋቸው መደምደሚያ ላይ ደግሞ "ቅንጅት አሁንም ሽፋን ነው፡፡" በማለት ፍርጥም ባለ ቋንቋ አስቀምጠዋል፡፡ ይህ አነጋገር ካለማወቅ ከሠረፀ ወኔ የመነጨ ነው፡፡ እኛ ዕውነተኛ የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፖርቲ ቤተሰብ አባላት በሽፋን የምንጓዝ አይደለንም፡፡ የትግል መርህ አለን፡፡ ራዕያችንና ዓላማችንን ጠንቅቀን እናውቃለን፡፡ ትግላችን ይህን ግñአን ሕዝብ ነጻ ለማውጣት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሕዝቡ ከእኛ ጋር መሆኑን ደግሞ ጠላትም ሆነ ወዳጅ በውል ያውቃል፡፡ በሽፋን አንታገልም፡፡ ፀሐፊው ሥራ ከሌላቸው ቤተ መጻሕፍት ገብተው መፅሐፍ ቢያነቡ ይመረጣል፡፡ የአሉባልታ ቋት የሆነ አእምሮአቸውን የዕውቀት ማህደር ያድርጉት፡፡ አሁንም ደጋግመን ለማስገንዘብ እንወድዳለን፡፡ ከእኛ በላይ ለቅንጅት ለአንድትና ለዴሞክራሲ ፖርቲ ሕልውና የሚቆረቆር ማንም የለም፡፡ ዓላማ በሽፋን እንዴት ግቡን ሊመታ ይችላል? እኛ የቅንጀት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፖርቲ ቤተሰብ አባላት መነሻችንን እናውቃለን፡፡ መድረሻችንም በግልፅ ይታየናል፡፡ በአሉባልታ አንፈታም፡፡ አሉባልታ የአሉባልተኛውን አስተሳሰብ ብቻ ይወክላል፡፡ አሉባልታ ሺህ ጊዜ ቢደጋገም ግን የይዘት ለውጥ እንደማያመጣ ሊታወቅ ይገባል እንላለን!






Reddit!Del.icio.us!Facebook!Slashdot!Netscape!Technorati!StumbleUpon!Newsvine!Furl!Yahoo!Ma.gnolia!Free social bookmarking plugins and extensions for Joomla! websites! title=
Comments (0)Add Comment

Write comment
quote
bold
italicize
underline
strike
url
image
quote
quote
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley

security code
Write the displayed characters


busy
 


Quick Jump

Ethio Date & Time

ዛሬ ቀኑ:

Calendar Converter




Daylight Saving