RSS 2.0 Email us: webmaster@mahder.com

Ethiopia: Mahder.com -Ultimate Ethiopian News and Information Portal

Saturday
Nov 22nd
Home arrow News arrow "አስተባባሪ፡ ኮሚቴ"ነኝ በሚለው ቡድን ላይ የተሰጠ መግለጫ
"አስተባባሪ፡ ኮሚቴ"ነኝ በሚለው ቡድን ላይ የተሰጠ መግለጫ Print E-mail
Monday, 05 May 2008

  PDF Version
በብሪታንያ፡ የቅንጅት: ድጋፍ፡ "አስተባባሪ፡ ኮሚቴ"፡ ነኝ፡ በሚለው፡ ቡድን፡ ላይ፡ የተሰጠ፡ መግለጫ።

ለንደን፡ ሚያዝያ፡ 27/ 2000 ዓመተ፡ ምህረት። (May5th 2008)

እኛ፡ በብሪታንያ፡ የምንገኝ፡ የቅንጅት፡ ደጋፊዎች፡የድጋፍ:ድርጅቱ፡ ከልክ፡ ባለፈ፡ መዳከሙ፡ አሳስቦን፡ በጉዳዩ፡ ላይ፡ ቅንጅትን:የደገፉ:ሁሉን:ለማወያየት፡ በድረ-ገጾችና፡ በዘመናዊው፡መልእክት፡ ማሰራጫ፡ (e-mail) በቅርቡ፡ ጥሪ፡

ማስተላለፋችን፡ይታወቃል።ይህ፡ጥሪያችን፡በይፋ፡ከተላለፈ፡ሦስት፡ቀን፡በህዋላ፡እራሱን፡"አስተባባሪ፡ኮሚቴ"፡እያለ፡የሚጠራው፡ቡድን፡ደጋፊዉን፡ለመከፋፈል፡በማቀድ፡በዚያው፡ቀን፡ሌላ፡ስብሰባ፡በመጥራት፡የማፍረስና፡የማደናቀፍ፡እርምጃ፡መውሰዱን፡ደርሰንበታል።

        

"አስተባባሪ፡ኮሚቴው"፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡በአገራችን፡ወቅታዊ፡ሁኔታ፤በተለይም፡በቅንጅት፡ሥራ፡አስፈጻሚ፡አካልና፡በላእላይ፡ምክር፡ቤቱ፡የተከሰቱትን፡ችግሮች፡በሚመለከት፡ደጋፊዎችን፡ሰብስቦ፡አንድም፡ውይይት፡አለማካሄዱ፡ድክመት፡ብቻ፡ሳይሆን፡ሆን፡ተብሎ፡የተሠራ፣የአባላቱን፡የመወያየትና፡ችግሩን፡የመፍታት፡ፍላጎቱን፡አስሮ፡የያዘ፡ደባ፡ነው።አሁን፡ከሁለት፡አመት፡በኋላ፡የቅንጅትን፡ችግርና፡"የአስተባባሪ፡ኮሚቴውን"፡አሠራር፡በሚመለከት፡የደጋፊዎች፡ውይይት፡ለማካሄድ፡ችግሩ፡ጉዳያችን፡ነው፡የሚሉ፡ደጋፊዎችን፡ለማሰባሰብ: ግንቦት፡3ቀን፡ 2000ዓመተ፡ ምህረት፡(May11) ከቀኑ፡ስምንት፡ተኩል፡(2:30pm) ፊንችሊ፡በሚገኘው፡የኢትዮጵያውያን፡ማህበረስብ፡ማህበር፡አዳራሽ፡የተጠራዉ:ስብሰባ፡የሚካሄድ:መሆኑን:በድጋሜ:እናስታዉቃለን።የዚህ፡ስብሰባ፡መጠራት፡ያስደነገጠው፡ደበኛ፡"አስተባባሪ፡ኮሚቴ"፡ደጋፊዉን፡ለመከፋፈልና፡ውይይቱ፡የሚያመጣበትን፡መዘዝና፡የሚያወጣውን፡እውነታ፡ለመሸፋፈን፡በዚያው፡ቀንና፡ሰአት፡ስብሰባ፡ጠራ።ይህ፡አካሄድ፡ደጋፊዉን፡በመናቅ፡የተደረገና፡የድጋፍ፡ድርጅቱን፡ለመከፋፈል፡ታስቦና፡ደጋፊዎቹ፡ቀደም፡ብሎ፡ወደተጠራው፡ስብሰባ፡ሲሄዱ፡ከጥቂት:የመከፋፈል፡ተንኮል፡ወጣኞችና፡አስፈጻሚዎች፡ጋር፡ተስባስበው፡የተለመደ፡ተግባራቸውን፡ለመፈፀም፡እንዲያመቻቸው፡የተወሰደ፡እርምጃ፡እንደሆነ፡ሰዉ:እንዲረዳዉ:ያስፈሊጋል።ይህ፡አይነቱን፡ደባ፡በማውጠንጠን፡በተባበሩ፡አዛውንት፡ግለሰቦች፡ላይም፡በጣም፡አዝነናል።ኢትዮጵያና፡ኢትዮጵያዊነትን፡የሚከፋፍልና፡የሚያዳክም፡እንጅ፡የሚያስተባብርና፡የሚያጠናክር፡መጥፋቱ፡በጣም፡ያሳስባል፤ያስቆጫልም።

                     

በአመራሩ፡አካባቢ፡የተሰበሰበው፡አድመኛ፡ቡድን፡ቀደም፡ሲል፡በደጋፊዎች፡የተመረጠውን፡አመራር፡በየሰበቡ፡እየገፉ፡ድርጅቱን፡ለመቆጣጠር፡ጥረት፡ማድረጉ፡የሚታወስና፡የማይታበል፡ሀቅ፡ነው።በደጋፊዎች፡ከተመረጠው፡ስብስብ፡የተወሰኑት፡ክፍል፡ከስብሰባ፡ውጭ፡እየተስማሙና፡እየተፈራረሙ፡የማይፈልጉትን፡ተመራጭ፡የማስወጣት፡የአድማ፡ሥራ፡አሁንም፡እንደቀጠሉበት፡ነው።በቅርቡ፡ሊቀንበሩንና፡ፀሐፊውን፡ጊዜአችሁ፡አልቋል፡ብለው፡ሃላፊነታቸውን፡በአድማ፡መንጠቅ፡አሁንም፡በመታየት፡ያለ፡ጉዳይ፡ነው:መግለጫም፡ወጥቶበታል፡፡"የአስተባባሪ፡ኮሚቴው"አድመኛ፡አካል፡ይህንን፡የጊዜአችሁ፡አልቋል፡ደባ፡ሲፈጽም፡የራሱስ፡ጊዜ:ማለቁን፡ዘንግቶት፡ሳይሆን፡እያወቀ፡ደጋፊዎችን፡በመናቅ፣ማን፡ይጠይቀኛል፡ከሚል፡ "የልብ፡እብጠት"፡በመነሳት፡መሆኑ፡ግልፅ፡ነው።

                

"የአስተባባሪ፡ኮሚቴዉ"፡የፋይናንስ፡አያያዝ፡ብዙ፡ጥያቄ፡ያለበት፡መሆኑን፡ደጋፊዎች፡እንዲያውቁ፡ያስፈልጋል።የቅንጅት፡አመራር፡እሥር፡ቤት፡በነበረበት፡ጊዜ፡ወደ፡አገር፡የሚላከው፡ገንዘብ:በሚስጥር፡መሆን፡አለበት፡በሚል:ከለላ፡ከአሜሪካኑ፡"አለም፡አቀፍ፡አመራር":በመጣ፡መመሪያ፡ከ15ሺህ፡ፓውንድ፡በላይ፡ወጪ:ሆኖአል።በጊዜው፡የነበሩት፡ሰዎች፡ጉዳዩን፡ለማጣራት፡ሞክረው፡ምንም፡የሚያስተማምን፡ነገር፡አልተገኘም።አሁን፡ግን፡አመራሩ፡ከእሥር፡ቤት፡ወጥቶ፡በነፃ፡መንቀሳቀስ፡ላይ፡ያለ፡ስለሆነ፡የሚያስፈራ፡ነገር፡የለምና፡ለግለሰቦች፡መርጃ፡በድብቅ፡ተሰጠ፡የተባለው፡ገንዘብ፡ሁሉ፡ በሂሳብ፡ሙያተኛ፡ተጣርቶ፡ለደጋፊዎች፡ሪፖርት፡መቅረብ፡አለበት። 

የሂሳብ፡ማጣራት፡ዓይነቱ፡ቅድመ፡አመታዊ፡ስብሰባ፡ዝግጅት፡ሳይሟላ፣እንዲያውም፡የአመታዊው፡ስብሰባ፡በማህበሩ፡ደንብ፡ከተደነገገው፡ጊዜ፡በላይ፡ብዙ፡ከተላለፈ፡በኋላ፣ሳይቀድሙኝ፡ልቅደም፤ካልሆነም፡ላደናቅፍ፤ከሚል፡እኩይ፡አስተሳሰብ፡በመነሳት፡"ከአስተባባሪ፡ኮሚቴው"፡አንዱ፡ቡድን፡ያልተሟላና፡ደንብ፡የጣሰ፡አመታዊ፡ስብሰባ፡ጠርቷል።አመታዊ፡ስብሰባ፡ ለመጥራት፡በማህበሩ፡ደንብ፡የሚሰጥ፡የጊዜ፡ገደብ፡እንዳለ፡እየታወቀ፣ይህ፡ሥርአት፡አልባ፡"አስተባባሪ፡ኮሚቴ"፡ግን፡የጠራው፡ስብሰባ፡የሕገ፡ደንቡን፡የጥሪ፡የጊዜ፡ገደብ፡ይጥሳል።

ቀደም፡ሲል፡ለግንቦት፡3ቀን፡2000፡ዓመተ፡ምህረት፡(may11)ስብሰባ፡የጠራነው፡ደጋፊዎች፡ግን፡አሁንም፡በድጋሚ፡አደራ፡የምንለው፡በፊንችሊ፡ኮሚኒቲ፡አዳራሽ፡በተጠራው፡ስብሰባ፡ቅንጅትን:የደገፈ:ሁሉ:ተገኝቶ፡በተከሰተው፡ችግርና፡"የአስተባባሪ፡ቡድኑ"፡በሚያውጠነጥነው፡ደባ፡ላይ፡በጥሞና፡ለመወያየትና፡እንዴት፡ወደፊት፡መሄድ፡እንደሚቻል፡ስምምነት፡ላይ፡እንዲደረስ:በድጋሜ:እናሳስባለን።ስለሆነም፡በቅርቡ፡በተበተነው፡"የአስተባባሪ፡ኮሚቴው"ተገንጣይ፡ክፍል፡በጠራው፡ጥሪ፡ሳትወናበዱ፡ደጋፊዎቹ፡በጠሩት:ስብሰባ፡እንድትገኙና፡ችግሩን፡በውይይት፡እንድንፈታ፡ይህን፡መግለጫ፡አውጥተናል።                        

በደባና፡ግልፅነት፡በጎደለው፡ሥራ፡ኢትዮጵያ፡አትድንም።        

በጠባብ፡የቡድን፡አሠራር፡ወያኔ፡አይሸነፍም።

ለአንድ፡አገር፣ለአንድ፡ሕዝብ፣በቁርጠኝነትና፡በህብረት፡እንቁም።  

ኢትዮጵያ፡ለዘላለም፡ትኑር!!!!!

More Info

 CALL FOR A MEETING OF KINIJIT SUPPORTERS IN THE UK






Reddit!Del.icio.us!Facebook!Slashdot!Netscape!Technorati!StumbleUpon!Newsvine!Furl!Yahoo!Ma.gnolia!Free social bookmarking plugins and extensions for Joomla! websites! title=
Comments (0)Add Comment

Write comment
quote
bold
italicize
underline
strike
url
image
quote
quote
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley

security code
Write the displayed characters


busy
 


Quick Jump

Ethio Date & Time

ዛሬ ቀኑ:

Calendar Converter




Daylight Saving