| የቅንጅት አመራር የፓርቲውን ስምና አርማ በተመለከተ |
|
|
| Tuesday, 06 May 2008 | |
|
የቅንጅት አመራር የፓርቲውን ስምና አርማ በተመለከተ የምርጫ ቦርድን እየከሰሰ ነው! የገዥው ፓርቲ የቅንጅት መሪዎችን አፍሶ ለሥር ከዳረገ በኋላ የድርጅቱን መጠሪያ ስምና አርማ ምርጫ ቦርድ ለግለስቦች አሳልፎ መስጠቱ አስቂኝና አስገራሚ ሆኖ ከርሟል። ድርጊቱ በማናቸውም መለኪያ ሕገወጥ ከመሆኑም በላይ የሕዝብ ንብረት በጠራራ ፀሐይ እንደመዝረፍ የሚቆጠር ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ለቅንጅት መሠረታዊ ዓላማዎች ህልውናና አጠቃላይ ይዘት ስሙንና ዓርማውን ጨምሮ አቅፎ የተቀበለውና ይኅንኑም የሚንከባከበውና በዓይነ ቁራኛ እንደሚጠብቀው የሚያጠራጥር አይደለም። በ1997 ምርጫ የቅንጅት አሽናፊነት እንደተረጋገጠ የወያኔ መንግሥት ቅንጅትን ለማጥፋት ያልፈነቀለው ድንጋይና ያልጠነሰሰው ሴራ አልነበረም። የፓርቲውን አመራር በጠቅላላው ከማሠር አልፎም የድርጅቱን ሕልውና ፈጽሞ ለማጥፋት ካልሆነም በእጅ አዙር ለመቆጣጠር ያላሰለሰ ጥረት አድርጓል። እርሱ ማፍረስ ሲያቅተውም ሌሎች እኩይ ተግባር ያላቸውን ግለሰቦች ፓርቲው ውስጥ ሠርገው እንዲገቡ በማድረግ አፍራሽ ተልኳቸውን ሲያካሂዱ ቆይተው እነሆ አሁን ፓርቲ መሥርተናል በማለት ከቅንጅት እራሳቸውን አግልለዋል። ምንም እንኳን በወያኔ አገዛዝ ፍትሕ ይገኛል ብለን ባናምንም ባሉት መሥመሮች ሄደን በመጨረሻ ለሕዝብ ውሳኔ ማቅረቡ ተገቢ ሆኗል። አቶ አባይነህ ብርህኑ የቅንጅት ማእከላዊ ኮሚቴ አባልና የፓርቲው ፕሬዘዳንት ተወካይ ለሀራምቤ መጽሄት በሠጡት ቃለ ምልልስ በትክክል እንዳስቀመጡት ፓርቲው በቅድሚያ ሕጋዊ መብቱን በሀገሪቱ ፍርድ ቤቶች ተጠቅሞ እንድሚያስከብር፤ ካልሆነም ለሀገሪቱ ም/ቤት ጉዳዩን አቅርቦ እንደሚያስወስን፤ በዚህም መፍትሄ ካልተገኘ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁኔታውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። በዚህ ሁሉ ጥረት የፓርቲያችን ሕጋዊ መብት የማይከበር ከሆነ የፓርቲው መለያ ስምና ምሥል ባለቤት ለሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጉዳዮን አቅርበን እናስወስናለን ብለዋል:: በክሱ ዝርዝር ማመልከቻ እንደተገለጸውና በምርጫ 97 የዓለም ሕዝብ እንደሚመሰክረው በኢንጂነር ሀይሉ ሻውል የሚመራው ቅንጅት በዚሁ ስምና ዓርማ ተወዳድሮ ማሽነፉ የአደባባይ ሚስጥር ነው። ቀድሞውንም የምርጫ ቦርድ ለገዥው ወገን ጥቅም ሲባል የተፈጠረ ለመሆኑ ባለፉት ተከታታይ ምርጫዎች በገሀድ የታየና የሚታወቅ ጉዳይ ነው። ድርጊቱ ሆነ ተብሎ የቅንጀትን ሕልውና ለማጥፋት ከሚደረጉ በርካታ እርምጃዎች አንደኛው መሆኑ ቢታወቅም፤ ይኅንን አምባገነናዊና መስሪ ተግባር የሀግሪቱ ህግ እስከሚያራምድ ድረስ ገፍቶ የመጨረሻ ፍርዱን ከሕዝብ መሻቱ አስፈላጊና ተገቢ እርምጃ ነው እንላላን። ለዚህም መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም የቅንጅት አባሎችና ደጋፊዎች በያሉበት ድጋፋቸውን እንዲገልፁ ጥረያችንን እናስተላልፋለን። በዚህ አጋጣሚም በፓርቲው አመራር ላይ የደረስውን ጊዜአዊ ችግር በመጠቀም ከምርጫ ቦርድ ጋር በመተባበር የፓርቲውን ስምና ሎጎ እንደቅርጫ የተክፋፈሉት ግለስቦችም ሆኑ ድርጅቶች ይኅንኑ ለፓርቲው ፕሬዘዳንት ተወካይ በአስቸኳይ እንዲያስረክቡ በቅንጅት አባላትና ደጋፊዎች ስም እንጠይቃለን። የክሱን ሂደትና ውጤት እየተከታተልን የምናቀርብ መሆኑን እየገለጽን ለፍርድ ቤት የቀረበውን ዝርዝር ማመልከቻ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ...... ገጽ 1 ገጽ 2 ገጽ 3 ገጽ 4
Comments (0)
![]() Write comment
|