|
Thursday, 15 May 2008 |
|
ለጭቁኖች ብለህ ብረት ያነሳኸው
ሽፍታና ቀማኛን ስርዓት ያስያዝከው
በእኩልነት ፍትህ ሁሉን አንድ ያደረከው
ብልህና ጀግናው ና የኛ መይሳው
ያቆምክልን ጎጆ በደም በአጥንትህ
ሲፈራርስ ዛሬ በምርጫ ልጅ ልጆች - በባላንጋሮችህ
ምን ይሰማህ ይሆን
ምንስ ትለን ይሆን
ስታይ ልጆችህን
ቆመን ስናይ ፈዘን?
ልብ! አል ባ ዎ ች ሆነን!?
ጎንደርም ዝም አለ
መሬቱን ንብረቱን ልጆቹን ሲቀማ
ወሎም ግራ ገባው
አካሉን አፍርሰው ሲያወጡት ለቅርጫ
ጎጃምና ሸዋም ቆመዋል ደንብረው
ያልጠበቁት ሆኖ የሚያደርጉት አተው
ከኣርሲ ወለጋ
ባሌ ጋምጎፋ
ከኢሊባቡር ሐረር
ሁሉም ዝም ብለዋል ያሉ በሩቅ በቅርብ
አማራ ቅርጫ ወቶ ለትግራይ ለሱዳን
ለስጦታ ሲቀርብ
ሰማህ ወይ
መይሳው?
ገብተው ሲነጣጥሉት ቁዋራን ከሁመራ
ፋሲካ ሆነ አሉ በግብፅ ከተማ
ሚኒሊክ ጌታቸው
ዋሽንግተን ዲሲ ሜይ 6, 2008
|