RSS 2.0 Email us: webmaster@mahder.com

Ethiopia: Mahder.com -Ultimate Ethiopian News and Information Portal

Tuesday
Jul 08th
Home arrow News arrow ተማሪው በወያኔ ታጣቂዎች ተገደለ - ታዲዎስ ታንቱ
ተማሪው በወያኔ ታጣቂዎች ተገደለ - ታዲዎስ ታንቱ Print E-mail
Friday, 16 May 2008
በደቡብ ጎንደር በፋርጣ ወረዳ በቁሃላ ገበሬ ማህበር ውስጥ ምሥጋናው ጌጤ ዘለለው የተባለ አሥራ ዘጠኝ ዓመት ዕድሜ የነበረው የስምንተኛ ክፍል ተማሪ በወያኔ ቅጥረኛ ፖሊሶችና በአካባቢው ታጣቂዎች በከፍተኛ ደረጃ ድብደባ ተፈጽሞበት ሚያዝያ 13 ቀን 2ዐዐዐ ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን በሥፍራው የነበሩ የዓይን ምስክሮች አረጋግጠዋል፡  

    የዓይን ምሥክሮች ወጣቱ ተደብድቦ የተገለደበት ምክንያት ሰሞኑን ወያኔ ባካሔደው የአካባቢና የማሟያ ለተባለው ማስመሰያ ምርጫ" የአካባቢው ነዋሪዎች እንዳይወጡ እየተዘዋወረ ቅስቀሳ አድርጓል" በማለት መሆኑንም አክለው ገልፀዋል፡፡

    የሟች ምሥጋናው ጌጤ ዘለለው አስክሬን ቤተሰቦቹ የትምህርት ቤት ጓደኞቹና የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት በአቱዕ ባዕታ ቤተ ክርስቲያን ሚያዝያ 14 ቀን 2ዐዐዐ ዓ/ም መቀበሩንም ከሥፍራው ከደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡

    ተማሪ ምሥጋናው ጌጤ ዘለለው በተገደለበት ዕለት በርካታ ወጣቶች በፖሊሶች የተደበደቡ ሲሆን ከመካከላቸው ፀጋዬ ቢሆነኝና ማሩዬ መልኬ የተባሉ ሁለት ወጣቶች እግራቸውን ተሰብረው ከቦታ ወደ ቦታ የሚንቀሳቀሱት ታዝለው መሆኑንም የመረጃ ምንጮቻችን አክለው አስረድተዋል፡፡






Reddit!Del.icio.us!Facebook!Slashdot!Netscape!Technorati!StumbleUpon!Newsvine!Furl!Yahoo!Ma.gnolia!Free social bookmarking plugins and extensions for Joomla! websites! title=
Comments (0)Add Comment

Write comment
quote
bold
italicize
underline
strike
url
image
quote
quote
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley

security code
Write the displayed characters


busy
 


Other top stories


Quick Jump

Ethio Date & Time

ዛሬ ቀኑ:

Calendar Converter




Daylight Saving