RSS 2.0 Email us: webmaster@mahder.com

Ethiopia: Mahder.com -Ultimate Ethiopian News and Information Portal

Saturday
Nov 22nd
Home arrow News arrow ሰዎች በራኃብ ሞቱ
ሰዎች በራኃብ ሞቱ Print E-mail
Sunday, 01 June 2008

     በሰሜን ጐንደር ዞን በአምባ ጊዮርጊስ ወረዳ በገደብዬ ውስጥ ሶስት ሰዎች ለቀናት በራኃብ ሲሠቃዩ ቆይተው ሰሞኑን ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ውስጥ አዋቂ ምንàች ከስፍራው በስልክ ገልጸዋል፡፡

     በዚህም መሰረት 1. አለፈ ፋንታ ወርቅ ደም ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ የነበሩ 2. በላይነሽ ተገኝ የደሮሃ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነዋሪ የነበሩና 3. እማሆይ ፋንታነሽ የተባሉ የገደብዬ ከተማ ነዋሪ የነበሩ መሞታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

     እንደ ውስጥ አዋቂ ምንàቹ አገላለፅ በገደብዬና በአካቢባዋ በሚገኙ አሥር ቀበሌ ገበሬ ማህበራት ውስጥ ባሁኑ ወቅት ሕዝቡ በከፍተኛ ደረጃ የተራበ ሲሆን በአገዛዙ ባለሥልጣናት አንዳችም እርዳታ አንዳልተደረገለት ታውቋል፡፡

 

     አንዳንድ በገደብዬና በአካባቢዋ ተዘዋውረው የተመለከቱ የዓይን ምሥክሮች በሰጡት አስተያየት ሥርዓተ አገሃዛዝ ተገቢውን እርዳታ ካላደረገላቸው የገደብዬና የአካባቢዋ ነዋሪዎች ባጭር ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ በሞት ሊጠቁ እንደሚችሉ ተንብየዋል፡፡

     ይህ በአንዲህ እንዳለ በደቡብ ኢትዮጵያ በጎፋ ልዩ ዞን በደምባ ጎፋ ወረዳ በሎጤ ዛጳ ሴሎና ሎጤ ቶጃ ሰጴ ቀበሌዎች መካከል በተፈጠረ የድንበር ግጭት ሳቢያ 68 ሰዎች በከበባ ተይዘው ሰሞኑን መታሰራቸውን ከሳውላ የደረሱን የመረጃ ምንàች አመለከቱ፡፡

     እንደ መረጃ ምንàች አገላለፅ ሰዎቹ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለ 15 ቀናት ከታሰሩ በኋላ በመጨረሻ ወደ ፍርድ ቤት ቀርበው ከመካከላቸው አሥራ አንዱ ወደ ወህኒ ቤት ሲላኩ የተቀሩት እንዲለቀቁ መደረጋቸው ታውቋል፡፡

   

      ወደ ወህኒ ቤት ከተላኩት መካከል አቶ ሸለመው ፈላ የደምባ ጎፋ ወረዳ  የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ይገኙበታል፡፡

   

      በሌላም በኩል በዚሁ በጎፋ ልዩ ዞን በደምባ ጎፋ በያላ ቀበሌና በዛላ ወረዳ በባዬዚማ ቀበሌ ውስጥ ለራኃብተኛ የቅንጅት ለአነድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቱ አባላት እንዲሁም ለፓርቲው ደጋፊዎች ምንም ዓይነት የእህል እርደታ እንዳይሰጣቸው በግለፅ መታወጁን ከሥፍራው በስልክ የደረሱን መረጃዎች አመለከቱ፡፡

    

     በዙሁ የክልከላ አፈፃፀም ሒደት በተለይ ዓለማየሁ የተባለ የያላ ቀበሌ የወያኔ የማስታወቂያ ጉዳይ ኃላፊ "ለቅንጅቶች እህል ቅንጅት ይስጣቸው! አኛ አንስጣቸውም!" በማለት በስብሰባ ላይ መናገሩ ምንàች ከስፍራው ጠቁመዋል፡፡






Reddit!Del.icio.us!Facebook!Slashdot!Netscape!Technorati!StumbleUpon!Newsvine!Furl!Yahoo!Ma.gnolia!Free social bookmarking plugins and extensions for Joomla! websites! title=
Comments (0)Add Comment

Write comment
quote
bold
italicize
underline
strike
url
image
quote
quote
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley

security code
Write the displayed characters


busy
 


Quick Jump

Ethio Date & Time

ዛሬ ቀኑ:

Calendar Converter




Daylight Saving