RSS 2.0 Email us: webmaster@mahder.com

Ethiopia: Mahder.com -Ultimate Ethiopian News and Information Portal

Thursday
Aug 28th
Home arrow News arrow ለክቡር እንጅነር ኃይሉ ሻውልየድጋፍ መልዕክት እየጎረፈ ..
ለክቡር እንጅነር ኃይሉ ሻውልየድጋፍ መልዕክት እየጎረፈ .. Print E-mail
Sunday, 08 June 2008

ከታዲዎሰ ታንቱ

 

አባላትና እንግዶች በክንዋኔ ሰሌዳ ከተመለከተው ጊዜ በአንድ ሰዓት ቀድመዋል፡፡ ድንኳኑ ጢም ብሏል፡፡ ለመቀመጫ መቀመጫ አልተገኘም፡፡ ከፊሉ ቆሞዋል፡፡ አንዳንዱ ሰዓት ያያል፡፡ የተቀረው የያዘውን የክንዋኔ ሰሌዳ ይመለከተዋል፡፡ በሕሊናው ከህሊናው ጋር የሚነጋገርም ይስተዋላል፡፡ በሐሳብ ተመስጧል፡፡ አንዳንዱ ይኮሳተራል፡፡ ሌላው ይፈግጋል፡፡ አንዳንዱ ቆፍጠን ይልና በራሱ ውሳኔ ደግሞ ወደ ነበረበት ይመለሳል፡፡ ሁሉም በየፊናው የዕለቱን ሥነ ሥርዓት አስመልክቶ የራሱን ሒሳብ ይሰራል፡፡ በሕሊናው ያሰላል፡፡ ጥያቄ ይጠይቃል፡፡ ራሱን ይጠይቃል፡፡ ለምን ዘገዩ? አልቦ መልስ ያገኛል፡፡ በክንዋኔ ሰሌዳ ላይ ከተመለከተው የሰዐት ገደብ ደቂቃዎች አልፈዋል፡፡ አሁንም አልመጡም! አልመጡም! አሁንም አልመጡም! ግን ይመጣሉ፡፡ ጉጉት ሲበዛ ጊዜ ይረዝማል፡፡ አሁንም ግን አልደረሱም፡፡ ጊዜው ደግሞ እንዴት ይሮጣል? ለ 1ዐ 25 ጉዳይ ሆኗል፡፡ በድንገት ግን ድንገተኛ እንቅስቃሴ ታየ፡፡ የላዕላይ ምክር ቤት አባላት እንቅስቃሴ መሆኑን አንጣ፡፡ አዎን! ፈጠን ብለው ወደ በሩ አመሩ:: በድንኳን ውስጥ ያለው ሰው በሙሉ ይንሾካሾክ ገባ፡፡ መጡ እንዴ? አዎ መጡ! የት አሉ? አኚውና መጡ! አዎን አውነትም እኚውና መጥተዋል

 

አሁን አንደ ኢትዮጰያ የሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ ልክ ለ 1ዐ 2ዐ ጉዳይ ይነበባል፡፡ ከች አሉ! ከዘጠኝ ወራት በፊት የረገጡትን የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲን ቅጥር ግቢ ደግመኛ ሊረግጡት በቁ፡፡ የመልካም ጤንነት ገጽታ ይታይባቸዋል ፡፡ ፈገግታ ከፊታቸው ይነበባል፡፡ እልልታው ቀለጠ፣ ኃይሉ ኃይላችን ነው! ኃይሉ ኃይላችን ነው!  አሁንም ቀጥሏል፡፡ ኃይሉ ኃይላችን ነው! ክቡር ኢንጅነር ኃይሉ ሻውል ቀስ ብለው ወደ ፊት ያመራሉ፡፡ ክብርት ባለቤታቸው ወይዘሮ አልማዝ ዘውዴ አብሮአቸው ይገኛሉ፡፡ እልልታው ቀልጧል፡፡ የጭብጨባው ቃና ከፍ ብሏል፡፡ በመካከሉ መፈክር ጣልቃ ይገባል፡፡ ኃይሉ ኃይላችን ነው!

 

በቅርብ ርቀት ሁለት ሕፃናት ቆመዋል፡፡ ወንድና ሴት ሕፃናት ናቸው፡፡ ዕቅፍ አበባ ይዘዋል፡፡ ብዙም አልቆዩም፡፡ ወዲያው ወደ ፊት ራመድ አሉ፡፡ ሁለቱ ቡቃያዎች! ብዙም አልቆዩም፡፡ ለክቡር  ኢንጅነር ኃይሉና ለክብርት ባለቤተቸው እቅፍ አበባ አበረከቱ፡፡  ረጅም ጭብጨባ! እልልታውም ተከታተለ፡፡ አሁን ከቡር ኢንጄነር ኃይሉና ባለቤታቸው የተዘጋጀላቸውን ሥፍራ ይዘዋል፡፡ ጭብጨባው ግን ቀጥሏል፡፡ ቸብ! ቸብ! ቸብ! ቸብ! አሁንም ቀጥሏል፡፡ ቸብ! ቸብ! ቸብ! ቸብ! ረጅምና ተከታታይ ጭብጨባ! አንድ ጊዜ!  ፀጥታ!

 

ክቡር እንጄነር ኃይሉ ሻወል በዚህ ደማቅ የአቀባበል ሥነ ሥርዓት ላይ ለቅንጅት ለአንድነተና ለዴሞከራሲ ፓርቲ አባላት፤ ደጋፊዎች እንዲሁም ጥሪ ለተደረገላቸው እንግዶች የዓላማ ፅናታቸውንና ቁርጠኛ አቋማቸውን የሚያረጋግጥ ንግግር አሰምተዋል፡፡ ንግግራቸውን ቃል በቃል ቀርፀነዋል፡፡እነሆ!

 

እኔ እዚህ ልናገር የምፈልገው ብዙ ነገር ሊኖር አይገባም፡፡ ቅንጅት የኢትዮጵያ ሕዝብ ፓረቲ አንደሆነ ሁላችንም የምናውቀው ነው፡፡ ሊያፈርሱት የሞከሩት ሁሉ የሚያውቁት ነው፡፡ ሕዝብን ደፍሮ የሕዝብን ድርጅት ለማፍረስ መሞከር ግብዝነት ይመስለኛል እኔ፡፡ ለወደፊት ግን ማንኛችንም አኩራፊም ሆነ ሌላ ሳይኖር አብረን እንድንሄድ እጠይቃለሁ፡፡(ጭብጨባ) ግን አንድ ፓርቲ፤ፓርቲ ሊሆንና ውጤታማ ሊሆን የሚችለው ውሰጡ ሲፀዳ ብቻ ነው፡፡ (ረጅም ጭብጨባ)

 

እዚህ ቤት ዕውነትንና አንድነተን ኢትዮጵያዊነተንና ዴሞክራሲን የሚፈልግ የዕውነት ቤት ይሄ ነውና፤ እንኝህን ጉዳዮች ለማሳደግ፤ለማስከበር ለኢትዮጵያም ሕዝብ ወደ ፊት መመሪያ ለማድረግ የሚፈልግ ሁሉ አንዲመጡ እጠይቃለሁ፡፡ (ጭብጨባ ቸብ! ቸብ! ቸብ! ቸብ!) ግን ለሌላ መልዕክተኛ ሆኖ መምጣቱ እንደማያዋጣ የለፈው ያስተማረን ይመስለኛል፡፡

 

     እዚህ ፓርቲ ውስጥ ሕዝብን የማይወድ ቦታ የለውም ፡፡ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የማይቆም ቢቀር ይሻላል፡፡ ለአንድነት የማይቆም ለዘረኝነት የሚሔድ ቦታ የለውም፡፡ (ጭበጨባ) ይህች ሀገር አንድነት ከሌላት ሀገር አይደለችም፡፡ ባጭር ጊዜ ትሞታለች፡፡ ይህ ሕዝብ እርስ በርስ ተፋቅሮ በዕኩልነት ካልሄደ የትም የሚያደርሰን እንደሌለ እዚህ ውስጥ የማያውቅ ያለ አይመስለኝም፡፡ ይህን ያላመነ ዛሬ አይመጣም፡፡ አልመጣምም፡፡

 ቅድም እንዳልሁት አንድነትን፤ ፍቅርን ኢትዮጵያዊነትን የሚፈልግ ግን ይህች ፓርቲ የሱ ፓርቲ ልትሆን ይገባል፡፡

 

እኔ ውጭ ሆኜ ምንም አልሰጋሁም፡፡ ሰው እኮ የሚለኝ ፓርቲው ፈረሰ፤በዚያ ወጣ፤ እንዲህ ሆነ፤ ሲሉኝ  የትግል ጓዶች ስላሉኝ ምነም አልጠረጠርሁም፡፡ ምክንያቱም ይሄ ቤት የአንድ ግለሰብ ቤት አይደለም፡፡ (ሞቅ ያለ ጭብጨባ) ይሄ ቤት የሁሉም የፓርቲው አባላት ቤት ነው፡፡ ይሄ ፓርቲ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው፡፡ ለዚያ የሚታገል ሰው እንዳለ እርግጠኛ ስለነበርሁ ምንም ቅር አላለኝም፡፡ (ጭብጨባ) ስቆይም ለመዝናናት አንዳልሆነ ሳይገባችሁ አይቀርም፡፡ ብዙ ችግሮች ተፈጥረው ነበር፡፡ እነኛን ችግሮች መወጣቱ አሁን ለምንያያዘው ትግል አስፈላጊ በመሆኑ ነው፡፡ ዋናውን ትግል የምንታገለው ግን እዚህ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሕዝብ ውስጥ ነው፡፡ ከኛ ጋር ቆሞ የታገለው እንጂ እኛ እከሌ እከሌ ብለን ጠርተነው አይደለም፡፡ የፓርቲ አባል ያልነበሩ መስዋዕት ሆነዋል፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያዊ ካለ ማንም ኢተዮጵያዊ መጥቶ ከኛ ጋር ቢቆም ደስታውን አልችለውም፡፡ ነገር ግን እነኚህ ጓደኞቼ በየከፍለሀገሩ ዞረው ሕዝቡን አበረታትተው ፖርቲውን ከፍተኛ ጅምር እንዲያሳይ አድርገዋል፡፡ በጣም አመሰገናቸዋለሁ(ጭብጨባ) ለወደፊቱ ጠቅላላ ጉባኤው ተጠርቶ ከዚህ በፊት የደረሱት ችግሮች እንዳይደገሙ ማረሚያ እንዲደረግ፤ ሁለተኛ አመራር የሚመረጠው በግለሰቦች ሳይሆን በጠቅላላ ጉባኤው ስለሆነ አመራሩን እንደገና እንዲመርጡ ፤ሶስተኛ የፓርቲውን ፕሮግራም ማሻሻል ካስፈለገው ያንን ማሻሻል እንዲሰሩ ይጠራል፡፡ በዚያ ላይ ዝርዝር ሁኔታዎችን እናቀርባለን፡፡ እናንተም ብዙዎቻችሁ እዚህ ጋ ተገኝታችሁ አብራችሁ እንደምትሳተፉት ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ አመሰግናለሁ! ቸብ! ቸብ! ቸብ! ቸብ! (ረጅም ጭበጨባ)

 

የሰዎች አሰተያየት

 

ለእንጅነር ኃይሉ ሻውል የተደረገላቸው አቀባበል በጣም ድነቅ ነው፡፡ በጋራ ተሰብስበናል፡፡ በሰላም ስለመጡልን ደስታችንን እየገለፅን ነው፡፡ ደስ ብሎናል!

አለማየሁ ሞገድ  

 

ኢንጅነር በመምጣታቸው ደስ ብሎናል ፡፡ የቅንጅት ቤተሰብ አባላት እንደገና ተሰበሰቡ፡፡ ሞቅ ደመቅ ያለ አቀባበል በማየቴ ረክቻለሁ፡፡

                                                      ወርቁ ከበደ

ከጠበቅነው በላይ ደስ ብሎኛል፡፡

                        ሚሊዮን ተሾመ

እጅግ በጣም ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል፡፡

                        መንበረ ቀጸላ

የዛሬው የአቀባበል ስነሰርዓት ግንቦት 97ን የሚያስታውሰኝ ነው፡፡ የዛሬው የስብሰባው ስሜት በትግሉ በይበልጥ አንድንተጋ ያደርገናል፡፡ በርትተን እንታገላለን፡፡ ሁሉም ዜጋ ለነፃነቱ በርትቶ ይታገል፡፡

                        እሸቱ ወልደፃድቅ

በጣም ደስ ብሎኛል ፡፡ ሁሉም እንቅስቃሴ ተስፋ ሰጭ ነው፡፡

                        ጌታቸው አበበ

 

 

ለዘጠኝ ወራት በውጭ ሀገር በሕክምናና በሥራ ምክንያት ቆይተው ግንቦት 23 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም ወደ ሀገራቸው ለተመለሱት ለክቡር ኢንጅነር ኃይሉ ሻውል ለቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዝዳንት የደስታና የመልካም ምኞት መግለጫ ከልዩ ልዩ ዞኖች ወደ ፓርቲው ጽ/ቤት እየጎረፈ ይገኛል፡፡

     በዚህም መሠረት የሰሜን ሸዋ ዞን፤ የደቡብ ጐንደር ዞን፤ የሰሜን ጎንደር ዞን፤ የደቡብ ወሎ ዞን፤የድሬዳዋ ጊዜአዊ አስተዳደር፤ የአዋሳና የአካባቢው ጊዜአዊ አስተባባሪ ኮሚቴ፤ የሲደማ ዞን፤ የጐጂ ዞን፤ የዝዋይ ዞን እንዲሁም የናዝሬትና የአካባቢው ተጠሪ የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ለኢንጅነር ኃይሉ ሻውል የደሰታና የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላልፈዋል፡፡

     የሰሜን ሸዋ ዞን የቅንጅት ለአንድነት ለዴሞክራሲ ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በዚሁ መግለጫው ለክቡር ኤንጅነር ኃይሉ ሻውል ረጅም ዕድሜ ከጤንነት ጋር ተመኝቶ ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ሕልውናውን በአደጋ ላይ የጣሉትን ሰርጎ ገቦች አበጥሮና አንጠርጥሮ በመለየት ሕዝባዊ መሰረቱን ለማጠናከር በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር በበለጠ ተጠናክሮ መሥራት እንደሚጠበቅበት አሳስበዋል፡፡

 

     እንዲሁም የደቡበ ጎንደር ዞን የቅንጅት ለአንድነት ለዴሞክራሲ ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከደብረ ታቦር ባስተላለፈው የድጋፍ መግለጫው ክቡር ኢንጅነር ኃይሉ ሻውል ሕክመናቸውን አጠናቅቀው ወደ የሚወዷት ሀገራቸው ወደ ኢትዮጵያ በመመለሳቸው የተሰማውን ደስታ ገልጾ በማያያዝም "...በቅርብ ቀን ጠቅላላ ጉባዔ ተጠርቶ በቅንጅት ውስጥ የአለው ችግር ተፈትቶ እልባት አንዲያገኝና ለወደፊቱም ድርጅታችን ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክሪሲ ፓርቲ በአዲስ መልክ ተጠናክሮ ሰላማዊ ትግላችን የሚጠናከርበት መንገድ አንዲየቀስልን ስንጠይቅ በታላቅ አክብሮት ነው፡" በሏል፡፡

 

በተዛመደ መልኩ የሰሜን ጎንደር የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ባስተላለፈው መግለጫው ክቡር ኤንጅነር ኃይሉ ሻውል ከአያሌ ወራት የውጭ ሀገር ቆይታ በኋላ በሰላም ወደ ሀገራቸው በመመለሳቸው የተሰማውን ደስታ ገልጾ አያይዞም ጠቅላላ ጉባዔ ተጠርቶ የኢትዮጵያ ሕዝብ የደስታው ተካፋይ እንዲሆን አንዲደረግ አበክሮ ጠይቋል፡፡

 

ሌሎችም የዞን የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ኮሚቴዎች እንዲሁም ተጠሪዎች ለክቡር ኢንጅነር ኃይሉ ሻውል ረጅም ዕድሜን ከጤንነት ጋር ተመኝተው ባጭር ቀናት ውስጥ ጠቀላላ ጉባዔ ተጠርቶ ፓርቲው ዳግም ተጠናክሮ አንዲቀጥል እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡

 






Reddit!Del.icio.us!Facebook!Slashdot!Netscape!Technorati!StumbleUpon!Newsvine!Furl!Yahoo!Ma.gnolia!Free social bookmarking plugins and extensions for Joomla! websites! title=
Comments (0)Add Comment

Write comment
quote
bold
italicize
underline
strike
url
image
quote
quote
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley

security code
Write the displayed characters


busy
 


Other top stories


Quick Jump

Ethio Date & Time

ዛሬ ቀኑ:

Calendar Converter




Daylight Saving