RSS 2.0 Email us: webmaster@mahder.com

Ethiopia: Mahder.com -Ultimate Ethiopian News and Information Portal

Saturday
Nov 22nd
Home arrow News arrow መሠረቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሁንታ ነው
መሠረቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሁንታ ነው Print E-mail
Thursday, 12 June 2008

‹‹ለመልካም አስተዳደር መሠረቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሁንታ ነው፡፡››

 

ክቡር ኢንጅነር ኃይሉ ሻውል

      ክቡር ኢንጅነር ኃይሉ ሻውል የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዚዳንት የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድ በኩል በመልካም አስተዳደር እጦት እየተበደለ በሌላ አቅጣጫ ደግሞ በኑሮ ውድነት ምክንያት በሕይወት ለመኖር ከማይችልበት ደረጃ መድረሱን አስረድተው አያይዘውም በአስተዳደሩ ያልተመቸውና ችግር የተበተበው ሕዝብ ለተለያዩ አደጋዎች የተጋለጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

     

ገስስ

ፕሬዚዳንቱ ይህን የተናገሩት በሕክምናና በሥራ ምክንያት በውጭ አገር ለዘጠኝ ወራት ቆይተው ወደ አገራቸው ከተመለሱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአገር ውስጥ ለግል፣ ለመንግሥትና ለዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ጋዜጠኞች ግንቦት 28 ቀን 2000 ዓ.ም በቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ጽ/ቤት ውስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡

      በዚሁ መግለጫቸው ክቡር ኢንጅነር ኃይሉ ሻውል የአገሪቱን ችግሮች ለመፍታትና የሕዝቡ መንፈስ ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ እንዳይመራ ለማድረግ በክብ ጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጦ በመወያየት መፍትሔ ማምጣት እንደሚያስፈልገው አበክረው ካስገነዘቡ በኋላ አያይዘው በተናገሩት ቃል ‹‹ለአገር የሚበጅ ሥራ ለመሥራት መልካም አስተዳደር ያስፈልጋል፡፡ ለመልካም አስተዳደር መሠረቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሁንታ ነው፡፡ ስለሆነም ከሁሉም በቅድሚያ የኢትዮጵያን ሕዝብ ፍላጎት ማጤን ያስፈልጋል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጐት ደግሞ በኢትዮጵያ ምድር የዴሞክራሲ መብቶች ፍትሕና እኩልነት ከሁሉ በፊት ሰፍነው ማየት ነው፡፡›› ብለዋል፡፡

      በመቀጠልም ‹‹ከጥቃቅን የአስተዳደራዊ ሥራ ጀምሮ የዴሞክራሲ ሥርዓት ዋስትናው በገዢው ፓርቲ የሚነገሩ ቃላት እንዳልሆኑ ሁላችንም በተግባር ያየነው ጉዳይ ነው፣ ዴሞክራሲ ከተመቻቹና ከጠንካራ ሕዝባዊ ድርጅቶች ሕልውና ጋር የተሳሰረ ነው፡፡ ጠንካራ የሠራተኛ ማኅበር የመምህራን ማኅበር የነዋሪዎች ማኅበራት እና የመሳሰሉት እጅግ አስፈላጊ ናቸው፡፡›› በማለት ከገለፁ በኋላ አያይዘው ባሰሙት ቃል እነዚህ ሁኔታዎች እንዲኖሩ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ቆርጦ የተነሳ መንግሥት መኖር የግድ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

      ባሁኑ ወቅት ግን ችግራችንና የበለጠ የሚያሳስበን ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ መሠረት የሚሆኑትን ሕዝባዊ ድርጅቶች ማጣታችን ብቻ ሳይሆን ለምንግዜውም እንዳይኖሩ ደብዛቸው የሚጠፋበት ሁኔታ እየተመቻቸ መሆኑን የተናገሩት ክቡር ኢንጅነር ኃይሉ ሻውል በመቀጠል ‹‹ለዚህ ነው ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የዴሞክራሲ ሥርዓት በአስተማማኝ ሁኔታ በአገራችን ሊኖር የሚችልበትን መሠረት የሚሆኑ ጥያቄዎች ያቀረበው፤ ዛሬም ለሁላችን የሚጠቅም ሥራ እንዲጀመር መጠየቅ ግዴታችን ነው፡፡›› በማለት ገልፀዋል፡፡

      ክቡር ኢንጅነር ኃይሉ ሻውል በመቀጠል ደግሞ ዴሞክራሲ በአገራችን እንዲሰፍን ዛሬም የፍትሕ አካላት በእውነትና በእኩልነት ሕዝብን እንዲያገለግሉ፤ ዛሬም የፖሊስና የደኅንነት ተቋማት ነፃ የሕዝብ አገልጋይ እንዲሆኑ፤ ዛሬም መገናኛ ብዙኃን የሙያው ሥነ ምግባር በሚፈቅደው በነፃነት እንዲሠሩ፤ ዛሬም የሕዝቡ የመናገር፤ የመጻፍ፤ የመሰብሰብ፤ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግና የመሳሰሉት መብቶቹ ይከበሩለት ዘንድ በአፅንኦት ጠይቀው አያይዘውም በእነዚህ ሕዝባዊ ጥያቄዎች ምክንያት ሁሉንም እንግልቶች ለመቀበል መገደዳቸውን አውስተዋል፡፡

      ‹‹ገዢና ተገዢ ተፋጠውና እልህ ተያይዘው፤ በልማት ጐዳና ለመራመድ በፍፁም አይቻልም፡፡›› ያሉት ክቡር ኢንጅነር ኃይሉ ሻውል በመቀጠል ደግሞ ድህነትን ለማሸነፍ በጋራ ተሰልፈን እጅ ለእጅ ተያይዘን በሕግና በሕዝብ የበላይነት ላይ ተማምነን ወደ ልማት ሥራችን መሰማራት አስፈላጊ መሆኑን አበክረው አስገንዝበዋል፡፡

      በዚሁ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ስለቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ስያሜ እንዲሁም ስለምርጫ ምልክቱ የባለቤትነት መብት፤ ከፓርቲው አፈንግጠው ወጥተው የራሳቸውን ፓርቲ በማቋቋም ሂደት ላይ ከሚገኙ የቀድሞ አመራር አባላት ጋር ቅንጅት ወደፊት ስለሚኖረው ግንኙት፤ በቅርቡ ስለሚካሄደው የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ፤ ከቅንጅት ተለይተው ወጥተው በውጭ አገር ሆነው ሌላ የትግል ስልት መምረጣቸውን ስለሚናገሩ ሰዎችና ስለተዛማጅ ጉዳዮች ተጠይቀው ክቡር ኢንጅነር ኃይሉ ሻውል ሰፊ ገለጻና ማብራሪያ አሰምተዋል፡፡

      በተዛመደ መልኩ ፓርቲውን ለማዳን ስለተከናወኑት ተግባራት እንዲሁም የክቡር ኢንጅነር ኃይሉ ሻውልን የአመራር ብቃት በማስመልከት አቶ አባይነህ ብርሃኑ የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የሥራ አስፈጻሚ አባል አጭር ገለጻ ያደረጉ ሲሆን በተያያዙ አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ ደግሞ ወ/ሪት መሶበወርቅ ቅጣው የፓርቲው የላዕላይ ምክር ቤት አባል በበኩላቸው ማብራሪያዎችን ሰጥተዋል፡፡

      በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የላዕላይ ምክር ቤት አባላትና ጥሪ የተደገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡






Reddit!Del.icio.us!Facebook!Slashdot!Netscape!Technorati!StumbleUpon!Newsvine!Furl!Yahoo!Ma.gnolia!Free social bookmarking plugins and extensions for Joomla! websites! title=
Comments (0)Add Comment

Write comment
quote
bold
italicize
underline
strike
url
image
quote
quote
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley

security code
Write the displayed characters


busy
 


Quick Jump

Ethio Date & Time

ዛሬ ቀኑ:

Calendar Converter




Daylight Saving