|
የቅንጅት ፓርቲ ጉባኤ ሪፖርቶችን ሲያዳምጥ ውሏል |
|
|
|
Saturday, 21 June 2008 |
|
የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ጉባኤ ሪፖርቶችን
ሲያዳምጥ ውሏል፡፡
ዛሬ ጧት በክቡር ኢንጅነር ኃይሉ ሻውል የቅንጅት ለአንድነትና
ለዴሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዚዳንት ንግግር በደማቅ ሥነ ሥርዓት የተከፈተው የፓርቲው ጉባኤ ከሰዓት በኋላም በመቀጠል ከዞኖች የቀረቡ
ሪፖርቶችን ሲያዳምጥ ውሏል፡፡
በዚህም መሠረት የከፋ፤ የቦረና፤ የጉጂ፤ የደቡብ ሸዋ፤ የጌዴኦ፤
የሸካ፤ የባሌ፤ የጅማ፤ የምዕራብ ጎጃም፤ የምሥራቅ ሸዋ፤ የሰሜን ሸዋ፤ የሀዊ፤ የምሥራቅ ሐረርጌ፤ የሱማሌ፤ የመተከልና
የሌሎችንም ዞኖች ሪፖርቶች አዳምጧል፡፡
በሪፖርቶቹ መካከል ሞረሽ የኪነት ቡድን ልዩ ልዩ አዝናኝና ቀስቃሽ
ዜማዎችን በማቅረብ ጉባኤተኛውን አዝናንቷል፡፡
በጠዋቱ የጉባኤ መርሐ-ግብር የጎፋ፤ የጋሞ፤ የወላይታ፤ የሲዳማ፤
የአዋሳ፤ የትግራይ፤ የአፋርና የዳውሮ ዞኖች ተወካዮች ሰፊ ሪፖርቶች አቅርበዋል፡፡
በዚህ ጉባኤ ሂደት ከልዩ ልዩ አገሮች ድጋፍ ሰጪዎች የመልካም ምኞት
መግለጫ በማስተላለፍ ላይ የሚገኙ ሲሆን ጉባኤው አሁንም በጉባኤተኞች ንቁ ተሳትፎ ቀጥሏል፡፡
|