| የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ጉባዔ ተጠናቀቀ |
|
|
| Monday, 23 June 2008 | |
|
በክቡር ኢንጅነር ኃይሉ ሻውል ንግግር ተከፍቶ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ማምሻውን የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቅቋል፡፡
ጉባዔው
በዚህ መግለጫው ፓርቲው የቅንጅትን ስምና የምርጫ ምልክት ለማስመለስ በፍርድ ቤት የጀመረውን ክስ በመቀጠል ውጤት እንደተገኘ
ሥራ አስፈጻሚው ለበታች አካላትና አባላት ስያሜውንና ምልክቱን እንዲያሳውቅ ውክልና በመስጠት፣ አያይዞም ‹‹የፓርቲው የማደራጀት
አቅምና የገንዘብ ሁኔታ እንደ ፈቀደ የፓርቲው ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶችን እስከ ወረዳ ድረስ በቅደም ተከተል ማቋቋሙ በትጋት
እንዲቀጥል ሆኖ የፓርቲውን መዋቅርና እንቅስቃሴ በሕዝብ መካከል እንዲሠርፅ በማድረግ ረገድ በየደረጃው የምንገኘው የፓርቲው
አካላትና አመራሮችም የተጠየቀውን መስዋዕትነት ለመክፈል መዘጋጀታችንን እናረጋግጣለን፡፡›› ብሏል፡፡
በመቀጠልም
ጉባዔው በአቋም መግለጫው ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ለአገራችን አዲስ ባህል መሆኑን ገልጾ ይህን አዲስ ባህል በአገራችን ለማስፈን
‹‹.....በትጋት ለመሥራት ቃል እንገባለን፡፡›› ብሏል፡፡
ከጉባኤው
ፍጻሜ በኋላ በፓርቲው ጽ/ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ በሥራ አስፈጻሚ አባላት በጉባኤው ሂደትና በፓርቲው አጠቃላይ እንቅስቃሴ ላይ
ለአገር ውስጥና ለዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች ተሰጥቷል፡፡ በጋዜጣዊ መግለጫውም ላይ አቶ አባይነህ ብርሃኑ የሰሜን ኢትዮጵያ ቀጣና ኃላፊ፣ አቶ ወንድወሰን ተሾመ ዋና ፀሐፊ፣ ወ/ሪት መሶበወርቅ ቅጣው የሕዝብ ግንኙነት ኰሚቴ ኃላፊ፣ ወ/ሮ ዓለማየሁ ሞገድ የሴቶች ጉዳይ ኰሚቴ ኃላፊ፣ አቶ ማሙሸት አማረ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ፣ አቶ ጌታቸው አበበ የምርጫ ቋሚ ኰሚቴ እና አቶ በለጠ ገብሬ የሰሜን ወሎ ዞን ኃላፊ መሆናቸው ታውቋል፡፡
ኢንጅነር ኃይሉ ሻውል የፓርቲውን የሥራ አስፈጻሚ ኰሚቴ አባላት አስተዋወቁ Comments (0)
![]() Write comment
|