RSS 2.0 Email us: webmaster@mahder.com

Ethiopia: Mahder.com -Ultimate Ethiopian News and Information Portal

Thursday
Aug 21st
Home arrow News arrow የእነ ስየ አብርሃ በምስጢር ሊካሄድ የታሰበዉ ቴሌ ኮንፈረንስ
የእነ ስየ አብርሃ በምስጢር ሊካሄድ የታሰበዉ ቴሌ ኮንፈረንስ Print E-mail
Tuesday, 24 June 2008

   

እርማት!

   በእነ መኮንን ዘለለዉ የተዘጋጀዉ እነ ስየ አብርሃና ገብሩ አስራትን ያስተናገደ በምስጢር ሊካሄድ የታሰበዉ ቴሌ ኮንፈረንስ በአገር ወዳዱ ኢትዮጵያዊ አቶ “ሽሻይ ዛና” የተባለዉ በስሕተት ስለሆነ “አቶ ሽሻይ ዑቕባዝጊ (በትግራይ ዉስጥ በሽሬ አወራጃ የአድያቦ ተወላጅ) ተብሎ ይነበብ። “አቶ ሽሻይ ዑቕባዘጊ” የነ “መብራህቱ አርዓዶም” ወዳጅ ናቸዉ። ሽሻይ ዛና እና ሽሻይ ዑቕባዝጊ የተላያዩ ግለሰቦች ናቸዉ።  ስሕተቱ የኔ የጸሃፊዉ ስለሆነ ይቅርታ።

     ጌታቸዉ ረዳ       

 

   የTAND አመራር “መኮነን ዘለለዉ” እና ጓደኞቹ  ያዘጋጀዉ የስየና የገብሩ አስራት  የክብር አንግዳነት የቴሌ- ኮንፈረነስ ዉይይት ተቃዎሞ ገጥሞት ከ45 ደቂቃ ባልረዘመ ጊዜ ዉስጥ ተበተነ!          

                     ከጌታቸዉ ረዳ

      (ሳን ሆዘ ካሊፎርኒያ)

    Monday, June 23, 2008 

 

          

     ድሮ የህወሓት ታጋይ በየነበረዉ “መኮነን ዘለለዉ” ፡ በአሁኑ ወቅት የTAND የአመራር አባል በሆነዉ  ግለሰብ “ሰብሳቢነት” የተካሄደዉ ከ20 (ሃያ) የማይበልጡ የትግራይ ተወላጆች  በሚስጢር ተዘጋጀዉ “የቴሌ-ኮንፈረንስ” ዕሁድ በፈረንጆች አቆጣጠር በJune 22, 2008 ስየ አብራሃ፡ ገብሩ አስራት፤አረጋዊ በርሄንና ምናልባሽም በ”ለምለም” ስም የቀረበች (አረጋሸ አዳነች -ነች የሚሏት በጠርጣሬ) የክብር እንግዶች ሆነዉ ለማካሄድ በተጠሩበት ኮንፈረንስ ከ45 ደቂቃ በማይበልጥ ዉይይት በሗላ እነ ስየ አብራሃንና እነ ገብሩ አስራትን ለመቃወም መምስጢር ወደ ኮንፈረንሱ በገቡት ኢትዮጵያዊ መንፈስ ባነገቡ ግለሰቦች  ጠንካራ ተቃዉሞ ገጥሞት ተሰብሳቢዎቹ ወደ ግል አስነዋሪና ብልግና ወደ ተሞላበት የእርስ በርስ ተራ ስድብ ዉስጥ በመግባታቸዉ እንዲወያዩባቸዉ ለዉይይት የቀረቡት 4 አጀንዳዎች ሳይደመጡ ኮንፈረነሱ ተቋርጦ እንዲዘጋ ተገዷል።

 

የኮንፈረንሱ አዘጋጆች አንዲወያዩባቸዉ ያቀረቡዋቸዉ 4 አጀንዳዎች ባጭሩ የሚከተሉት ናቸዉ።

 1-የትግሉ ዉጤት። ይላል፤ ስለ (ኤርትራዊዉ ወያነ ትግራይ TPLF) ማለቱ ነዉ።

2- የህዝቡስ ትግል በምን መልኩ ይቀጥል?

3-በትግሉ ዉስጥ፤ የናንተስ ተራ ምን መሆን አለበት

4-ከኢትዮጵያ ታጋዮች ጋርስ በምን መልኩ ብንተባበር ይሻላል?

 የሚሉ ናቸዉ።

 

     ከተሰብሳቢዎቹ መሃል (X) ኢድዩ ነበር አሕአፓ ታጋዮችና  እንኳ ቢኖርባቸዉም፤ ከአንድ  የኢዲዩ ታጋይ በስተቀር እነሱም በአንጃዉ በነስየ አብራሃና በነገብሩ አሰራት አፍቀሬነት ዉስጥ ስለተሰባሰቡ፤የትግራይ “ሕዝብ” ትግል እያሉ የሚጠሩት አጀንዳ ያኮላሹትንና ብዙ ብሔራዊ ወንጀሎችንና የሕዝብ ድምጽ በጠመንጃ ስያፍኑ የነበሩ እነ ስየና እነ ገብሩን መቃወም ቀርቶ የተቃወሙትን ሁሉ በተራ ስድብ ለማስቆም ሞክረዋል።

 

        የኮንፈረንሱ የክብር እንግዶች ተብለዉ፤ (በመኮነን ዘለለዉ አጠራር “ዓበይቲ ሰባት” (ታላላቅ ሰዎች) ዛሬ ሥልጣን ዉስጥ የሌሉ ሦስቱም የወየኔ አመራሮች በተገለጹት አጀንዳዎች ላይ “ነካ- ነካ” እያደረጉ አስተያየታቸዉን ከሰጡ በሗላ፤ በአንድ የኢድዩ ነባር ታጋይ የነበረ ተቃዎሞ ደረሳቸዉ። “ወንድሞቻችን ጥርግርግ አድርጋችሁ በየምክንያቱ ፈጃችሗቸዉ!”፤ “ሕዝባችን ምትሉትን ሕዝብ “ባፍ ጢሙ” ደፋችሁት!” “አገራችን ሸጣችሗት!” “ለኢትዮጵያ ባንዴራ ክብር የማትሰጡ ወራዶች!” ፡”ነብሰበሎች!” “ወደባችን ዘጋችሁት!” “ምኒሊክ ኤርትራን ለጣልያን ሸጠ፤እያላችሁ ስትዋሹን፡ዛሬ ኤርትራን ማን አንደሸጠ አስመሰከራችሁ! ትግራይ ሕዝብ በናንተ ተዋርዷል! እኛ የትግራይ ሰዎች ታሪክና አገር “ሻጭ፤ቸርቻሪ” እየተባልን በናንተ ታሪካችንንና ክብራችን ተዋርዷል!” አሁን እናንተ ስለ ዲሞክራሲ አዚህ የምትዘላብዱት ሰዉ ያምነናል ብላችሁ ነዉ?!” ከቶ እናተ ምን በደላችሁ! ይህ ሁሉ ክብር ለአገር ሻጮች እየሰጡ የሚያዋርዱን አነኚህ እዚህ አናነተን የጋበዙ የታሪክ “እባሶች-ጥራጊዎች” (አብረዉ ከናንተ ጋር ድሮ በትግሉ ወቅት ህዝብ ሲበድሉ የነበሩ) ናቸዉ አንጂ እንናተ ማ ምን ታረጉ?!” እናንተ እዚህ ሳይሆን ስለ አገር “ክህደታችሁ” እስር ዉስጥ ነበር መግባት የሚገባችሁ!!!

     በማለት አቶ ሽሻይ “አቶ ሽሻይ ዑቕባዝጊ (በትግራይ ዉስጥ በሽሬ አወራጃ የአድያቦ ተወላጅ) የተባለ ድሮ የኢድሕ ታጋይ የነበረ ኢትየጵያዉ ትግራይ ሰዉ እነኚህ “መደመጥ የለባቸዉም” “ድምጻቸዉ ልሰማ አልሻም፡ ሕዝብና አገር የሸጡ የበደሉ ናቸዉ፡ ኮነፈረንሱን ዝጉት! አሁኑኑ!!!! በማለት ከፍተኛ ተቃዎሞ (ፕሮተስት) በማድረጉ፤በመጨረሻ ለረጅም ጊዜ የስድብ እንካ ስላንትያ ፍጥጫዉ በመግባት ንትርኩ “ድሮ በወያኔና በኢድዩ ታጋዮች መሃል ወደ ነበርዉ ስድብና የመናናቅ ፍጥጫ “ቴንሽን” ዉስጥ ስለተለወጠ ኮንፈረንሱ እንዲዘጋ ተገደደ።

 

      አቶ “አቶ ሽሻይ ዑቕባዝጊ” ስየ አብራሃንና ገብሩ አስራትን ስለ የባሕር ወደባችን ማጣት ምክንያት እንሱ መሆናቸዉና ተጠያቂ መሆናቸዉንና እነደዙሁም አሁንም ኤርትራ የኢትዮጵያ ኮሎኒ ነበረች የሚለዉን እምነታቸዉ መተዋቹንና አለመተዋቸዉን፤ ከተዉትስ  ባሕሩና ህዘቡ ከኛ ጋር ያስነጠቁን ጥቅማችንና ቤተሰባዊነታችን አንዱ አንዱን ሳይበድል “ያበላሻችሁትን በምን መንገድ ይካስ ትላላችሁ?” ብሎ ከወጣራቸዉ በሗላ “ከአመጓሾቻቸዉ አንዱ ፤ግንፍል ብሎ አቶ “አቶ ሽሻይ ዑቕባዝጊ” በተራ የአረብኛ ቋንቋ በስድብ ሲዘልፏቸዉ፤ አንዳነዶቹም  “በዚህ ኮንፈረነስ አልተጋበዝክም “እረፍ” ስለ ኤርትራና ስለ ወደብ እንድንወያይ እዚህ አልመጣንም!” ሲለዉ፡- አቶ “ሺሻይ ዛና” የዋያኔ ጉድ ወደ መዘክዘኩ አልህ እና ስድብ ዉስጥ ሲገባ “እነ ስየ፡ እነ ለምለም (አረጋሽ አዳነ ነች በ”ለምለም” ስም ስትጮህ የነበረችዉ ይላሉ አንዳነድ ታዛቢዎች አንደገለጸት) አነ ገብሩ አስራት”  “እነደነገጠች አይጥ ዉልቅ፡ዉልቅ” ብለዉ ከቴሌ ኮንፈረንሱ ተሰናበቱ።

 

በምስጢር በጛደንነትና በዘመድ አዝማድ በጎጥ ስብስብ እየተጠራሩ እነ ስየና እና እነ ገብሩ ኢትየጵያን ወደ ዲሞክራሲና ወደ ነጻነት ይመሯታል ብለዉ ለነኚህ ክብር ሰጥተዉ አሁንም በበሰበሰዉ ጎዳና ለመጓዝ የሚጥሩ ሰዎች አገሪቷን አንደገና ወደ ሌላ ጠማማና እልክ ሽኩቻ ዉስጥ ወደ ሚያስገባ ሁኔታ እየፈጠሩ መሆናቸዉን ካሁኑኑ ቢገነዘቡት መልካም ነዉ እንላለን። ከዚህ ዉስጥ ለዉስጥ (ስለ እኛ ስለ ትግራይ ሕዘብ) ባምቻና በጋብቻ፤በጓደኝነት እተጠራሩ ተንኮል የተሞላበት ስብስብ የሚያደረጉ ኮንፈረንሶች ከቀጠሉ ፤የሰብሳቢዎቹ ማንነትና “ጉድ” ይፋ በማዉጣት ማንነታቸዉን ለማጋለጥ የምንገደድ መሆናችነን ካሁኑኑ ለመግለጽ እንወዳልን። በሕዝብ ስም እየተሰበሰቡ፤ ከ እነ ስየና ከ እነ ገብሩ፤ ከእ

ነ መለስና ወዘተ…..እየተሞዳሞዱ ኮንፈረነስ  ሲያካሂዱ ሌሎች ዜጎችም “እኛም የ ህዝቡ አካል ነንና ሃሳበችን እንስጥ በሚሉት ላይ ተረባርበዉ በቡድን የሚሸርቡና ዲሞክራሲአዊ የንግግርና የፕሮቴስት (የመቃወም)፤የመጮሕ፤ የመሰልፍ፤ስብሰባዉ እንዳይካሄድ የማወክ….ተናጋሪዉ እንዳይደመጥ የማወክ መብቶችን የሚዘጉ ሁሉ፤ ማወቅ ያለበቸዉ፤ ሰዎችን በትእግስት መጠበቅና ማቀዝቀዝ አንጂ “እኛ ብዙ ነን አሱ አንድ ነዉ፤ ተረባርበን አፉን እናስይዘዉ” የሚለዉ ከቶዉንም ለጊዘዉ አንጂ ዘላቂነት አይኖረዉም። እነ ስየንና እነ ገብሩን እንዲመሯችሁ የምታላዝኑ ሁሉ ተቃዋሚዉን አቶ ሽሻይ ዛናን “ ገበሬ ፤ገሪባ ፤የገበሬ ልጅ..የአጎቴ የፊታዉራሪ እገሌ በቅሎ ያዥ የነበርክ… ” የሚሉትን ስድቦች  በመሳደብባችሁ ስልጡን ምሁራኖች መሆናችሁ ለማሳት ገበሬዉንና የገበሬ ልጅ ማንኳሰሳችሁ ለትዝብት ይጥላችሗል።ገበሬዉን የምትንቁ “ከተሜዎችና አራዳዎች” “ምሕረቱን ይስጣችሁ!” እነ ገብሩ እንዲመሯችሁ

ጊዜ ከምታጠፉ በሳዉዲ አረብ እና በግብጽ ምድር ዉስጥ ታስረዉ በሃይማኖታቸዉ ብቻ ተወንጅለዉ 5000 ጅራፍ በቀን 50 ጅራፍ እንዲገረፉና 10 ዓመት ተፈርዶባቸዉ፤ የሚሰቃዩትን 30 የትግራይ ተወላጆች ተሰባስበን እንርዳ ፤ሰላማዊ ሰልፍ አንዉጣ ፤ተቃዎሞ እንጻፍ። ብየ በዌብ ሳይቴ ስላምናችሁ አንዳችሁም አንኳ ለዚህ ቅዱስ ጥሪ አልመለሳችሁልኝም። ወያኔ የናቃቸዉ፤ጊዜ የጣላቸዉ፤ የትግራይ ስደተኞችን ቴሌ ኮንፈረንስ ጠርቶ ከመርዳት ይልቅ፤ ሕዝብን የበደሉ ወያኔዎች አንዲመሯችሁ ለድሆቹ ጊዜ አጥታችሁ በዘመድ አዝማድ በጓደኛነት በምስጢር እየተሰባሰባችሁ በቴሌ- ኮንፈረንስ ለወያኔዎች መማጸናችሁ ሌላዉ አሳዘኙ ገጽታዉ ነወ። “አሁንም ትግሉ በሁሉም ዘርፍ ይቀጥላል”          

      ጌታቸዉ ረዳ

      2000 ዓ/ም

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 






Reddit!Del.icio.us!Facebook!Slashdot!Netscape!Technorati!StumbleUpon!Newsvine!Furl!Yahoo!Ma.gnolia!Free social bookmarking plugins and extensions for Joomla! websites! title=
Comments (0)Add Comment

Write comment
quote
bold
italicize
underline
strike
url
image
quote
quote
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley

security code
Write the displayed characters


busy
 


Other top stories


Quick Jump

Ethio Date & Time

ዛሬ ቀኑ:

Calendar Converter




Daylight Saving