RSS 2.0 Email us: webmaster@mahder.com

Ethiopia: Mahder.com -Ultimate Ethiopian News and Information Portal

Thursday
Aug 28th
Home arrow News arrow የቅንጅት አባላት በእሥር ቤት ውስጥ መሞታቸው ተገለጠ
የቅንጅት አባላት በእሥር ቤት ውስጥ መሞታቸው ተገለጠ Print E-mail
Monday, 07 July 2008

ሶስት የቅንጅት አባላት በእሥር ቤት ውስጥ

መሞታቸው ተገለጠ፡፡

     በአዊ ዞን ውስጥ ነዋሪ የነበሩ ሶስት የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ አባላት በከፍተኛ ድብደባ እንዲሁም በመጥፎ አያያዝ በልዩ ልዩ እሥር ቤቶች ውስጥ መሞታቸውን የመረጃ ምንጮች ሰሞኑን ገለጡ፡፡

     እንደ ምንጮቹ አገላለፅ በዚህ ሁኔታ ለሞት የተዳረጉት የመቶ አለቃ አርጋታ ጎበናና አቶ ስሜነህ ዓለሙ የፓርቲው የወረዳ ኮሚቴዎች ሰብሳቢዎች የነበሩ ሲሆኑ እንዲሁም አቶ ፀጋዬ አየለ የተባሉ አባል መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

     በተጨማሪም ጥላሁን አየሌው የተባሉ የወረዳ ኮሚቴ ሰብሳቢ በወያኔ እጅ ከወደቁበት ቀን አንሥቶ የት እንደ ደረሱ የማይታወቅ ሲሆን እንዲሁም ከበበው አያሌው ሌላው የቅንጅት ፓርቲ አባል ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በስደት እንዲኖሩ መገደዳቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

     በተመሣሣይ መልኩ በዚህ ዞን ውስጥ ብዙ ንፁሃን ዜጎች በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ በድብደባ አካለ ጎደሎ ሊሆኑ እንደቻሉ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡

     ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚሁ በአዊ ዞን በዳንግላ፤ በቲሊላ፤ በአንጅባራና በአንካሻ ወረዳዎች ውስጥ የትምህርት ፖሊሲን በመቃወም ሰልፍ ከወጡ ተማሪዎች መካከል ብዙዎች ተይዘው የታሰሩ ሲሆን አበባው ዕርቅይሁን የተባሉ መምህር ደግሞ ክፉኛ ተደብድበው ሆስፒታል ገብተው መሞታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

     በዚሁ ሕዝቡም ጭምር በተሳተፈበት ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ብዙ ሰዎች የተደበደቡ ሲሆን መንገዶች ተዘግተው የትራፊክ እንቅስቃሴም ታውኮ እንደነበር ተውቋል፡፡






Reddit!Del.icio.us!Facebook!Slashdot!Netscape!Technorati!StumbleUpon!Newsvine!Furl!Yahoo!Ma.gnolia!Free social bookmarking plugins and extensions for Joomla! websites! title=
Comments (0)Add Comment

Write comment
quote
bold
italicize
underline
strike
url
image
quote
quote
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley

security code
Write the displayed characters


busy
 


Other top stories


Quick Jump

Ethio Date & Time

ዛሬ ቀኑ:

Calendar Converter




Daylight Saving