|
በወለጋ ግጭት የተገደሉ ሰዎች ስም በከፊል ታወቀ |
|
|
|
Monday, 07 July 2008 |
|
የወያኔ የጎሣ መርህ አገዛዝ ባመጣው ቀውስ ሣቢያ በምሥራቅ ወለጋ በኦሮሞና በጉሙዝ ብሔረሰቦች መካከል ከግንቦት 8 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም አንሥቶ በተካሔደው ግጭት የተገደሉ ሰዎች ስም ዝርዝር በከፊል ሰሞኑን ታወቀ፡፡
በዚህም መሠረት 1. ኩመራ ዱሬሣ 2. ተስፋዬ ቀነዓ 3. አስማረ ቸኰል 4. ታደሰ ድርብሣ 5. አብዲ መስፍን 6. ተረፈ ነገሪ 7. ከበደ ገለታ 8. ፍቃዱ አልቀባ 9. ፍቃዱ ሳልባና 1ዐ. ተስፋዬ አስረስ 11. ኪዳኑ አስአዛ 12. ፈይሣ ወዳጆ 13. ኢረና ጅልቻ 14. ደረሰ ሺፈራው 15. ለማ ዓሊ 16. ብርሃኑ ዳርጌ 17. ስንታየሁ ምትኩ 18. ሣሙኤል ተመስገን 19. ተመስገን አልፋዳ እንዲሁም ኢፋ አሰፋ በጥይት ተመትተውና በስለት ተቆራርጠው ተገድለዋል፡፡ በተመሣሣይ መልኩ 1. በድሬ ጀማል ጉሬ የተባለች ሴት በግጭቱ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደለች ስትሆን እንዲሁም 2. ቡሻ ዳዋ 3. ዮሐንስ መኰንን 4. ዋቅጋሪ ዴሬሣ 5. ሞይሣ በዳሣ 6. ዋቅሹማ 7. ተስፋዬ መንገሻ 8. ከድር ዩያ፤ 9. ኃይሉ መታፈሪያ 1ዐ. ቦጋለ ዋቅቶሌ 11. ዳባ ገዲና 12. አቡሻ ሰቦቃ 13. ምትኩ ያደታ 14. ፎሎ ቡልቲ 15. ተስፋዬ አዋታ 16. ከበደ ፉፋ 17. ኦባ ኪሴ 18. ኦላኒ 19. ሰሎሞን ዋኛና 2ዐ. ዳንኤል ዳፋ መገደላቸው ታውቃል፡፡ ከእነዚህም በተጨማሪ ከአርቁንቤ፤ ከጉርጊዳና ባሬዳ ቀበሌዋች 1. ናስር ቀነህ 2. ታመነ 3. ጌታሁን እንዳለ 4. ደገፋ ገመዳ 5. ዘለቀ ሆርዶፋ 6. ገዋ 7. አመኑ ኦልዴራ 8. ሁሰን ሰይድ 9. ኢታና ዋቅጅራ 1ዐ. ተስፋዬ ታፈሰ 11. ተረፋ ዋቅቶሌ 12. ግርማ ረጋሣና 13. ጉርሙ ዋቅቶሌ በግጭቱ መካከል በግፍ ተጨፍጭፈው መገደላቸውን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ አንዳንድ ሰዎች የሟቾቹን ቁጥር እስከ አራት መቶ ሲያደርሱ በቅጥፈቱ፤ በመሠሪነቱና በነፍሰ ገዳይነቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ አክ እንትፍ ብሎ የተፋው የወያኔ ቡድን ግን በግጭቱ ከሃያ የበለጠ ሰው እንዳልተገደለ ይናገራል፡፡ ሆኖም በአንድ ቀበሌ ብቻ 9ዐ የሚደርሱ ሰዎች መገደላቸውን መረጃዎች ያመለከቱ ሲሆን በነቀምት ሆስፒታል በሞት አፋፍ የሚገኙ ቁስለኞች እንዲሁም ለከፍተኛ ሕክምና ወደ አዲስ አበባ የመጡ መኖራቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
|