RSS 2.0 Email us: webmaster@mahder.com

Ethiopia: Mahder.com -Ultimate Ethiopian News and Information Portal

Thursday
Aug 21st
Home arrow News arrow በመላው ኢትዮጵያ የግምባታ ሥራ ተቋረጠ
በመላው ኢትዮጵያ የግምባታ ሥራ ተቋረጠ Print E-mail
Monday, 07 July 2008

     ወያኔ የሥልጣን ዕድሜውን ለማቆት ለዓመታት ዐቢይ የፕሮጋንዳ መነሻ አድርጎ ይጠቀምበት የነበረው የግምባታ ሥራ ከሰኔ ወር 2000 ዓ.ም አንስቶ ተቋረጠ፡፡

     የግንባታ ሥራ እንቅስቃሴ የተቋረጠው የስሚንቶ ዋጋ ከመጠን በላይ በመናሩ ምክንያት መሆኑ የታወቀ ሲሆን ወያኔ ግን በዚህ ጉዳይ ላይ መግለጫ ከመስጠት ተቆጥቧል፡፡

 

     ባሁኑ ወቀት አንድ መቶ ኪሎግራም ስሚንቶ ከብር 380 እስከ 400.00 የሚሸጥ ሲሆን በዚህም ዋጋ በተፈለገው መጠን ማግኘት እንደማይቻል ለማወቅ ተችሏል፡፡

ወያኔ ላለፉተ አሥራ ሰባት ዓመታት በአዲስ አበባና በክፍላተ -ሀገር የኢትዮጵያን ሕዝብ መሬት ለዘሮቹና ለአሽከሮቹ በማከፋፈል ፎቆችን ሲያሰራ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

      በሌላም በኩል የጋዜጠኝነት ሙያን ሥነ ምግባር ጨርሶ በመተው በኢትዮጵያ  ሕዝብ ዘንድ ክፉኛ ለተጠላው ለወያኔ አገዛዝ በመሣሪያት ከመዝለቅ ያለፈ አንዳችም ዓላማ የሌላቸው ጋዜጠኛ ተብዬ የሥርዓተ - አገዛዙ ፕሮፓጋንዲስቶች ባሁኑ ወቀት ስለ ምግብ ዕህል በመገናኛ ብዙሃን መዘገብ ትተዋል፡፡

     ፕሮፓጋንዲስቶቹ ስለዚህ ጉዳይ መዘገቡን ሊተው የቻለው በየዕለቱ እያሻቀበ ስለሚሄደው ስለምግብ ዕህል ዋጋ ለመዋሸት ፈጽሞ የማይመች በመሆኑ እንዲህ ዓይነት ዘገባ ከመዘገብ እንዲቆጠቡ ከጌቶቻቸው በደረሳቸው ትዕዛዝ ምክንያት መሆኑን የውስጥ ዐዋቂ ምንጮች ተናግረዋል፡፡

      የችጋር መልዕክተኛ የሆነው ወያኔ በ1983 ዓ.ም እየግተለተለ አዲስ አበባ ሲገባ በብር 180.00 ይሸጥ የነበረው አንድ መቶ ኪሎ ግራም ነጭ ጤፍ ባኑ ወቀት በብር 1200.00 የሚሸጥ ሲሆን ዛሬ እስከ ብር 400.00 ድረስ የሚያወጣው አንድ መቶ ኪሎ ግራም ሲሚንቶ ደግሞ በዚያን ጊዜ በብር 38.00 ይሸጥ እንደነበር ይታወሳል፡፡






Reddit!Del.icio.us!Facebook!Slashdot!Netscape!Technorati!StumbleUpon!Newsvine!Furl!Yahoo!Ma.gnolia!Free social bookmarking plugins and extensions for Joomla! websites! title=
Comments (0)Add Comment

Write comment
quote
bold
italicize
underline
strike
url
image
quote
quote
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley

security code
Write the displayed characters


busy
 


Other top stories


Quick Jump

Ethio Date & Time

ዛሬ ቀኑ:

Calendar Converter




Daylight Saving