RSS 2.0 Email us: webmaster@mahder.com

Ethiopia: Mahder.com -Ultimate Ethiopian News and Information Portal

Saturday
Nov 22nd
Home arrow News arrow ሶስት የቅንጅት አባላት በሰርቪያ ውስጥ መታሰራቸው ተገለጠ
ሶስት የቅንጅት አባላት በሰርቪያ ውስጥ መታሰራቸው ተገለጠ Print E-mail
Thursday, 17 July 2008
 

     ለአትሌቲክስ ውድድር ተመልምለው ውጭ ሀገር ሲደርሱ ከጨካኙ የወያኔ መንግስት አፈንግጠው የፖለቲካ ጥገኝነት የጠየቁት ሶስት የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ አባላት በሰርቪያ ቤልግሬድ ውስጥ ከጥር ወር 2000 ዓ.ም አንሥቶ በእስር ላይ እንደሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ሰሞኑን ገለጡ፡፡

    

እንደ ቤተሰቦቻቸው አባባል አትሌቶቹ ተይዘው ሊታሰሩ የበቁት "በኢትዮጵያ ምንም የፖለቲካ ችግር የለም!" በሚሉ ፖሊሶች ሲሆን ይዘው ለፖሊሶች የሰጧቸው ደግሞ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሠራተኞች መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

     በአሁኑ ወቅት በዚህ ሁኔታ በእስር ላይ የሚገኙት፡- 1.ታአምራት ተስፋዬ     2. ብርሃኑ ዮሀንስ 3.አንዲት ስሟ ለጊዜው የማይታወቅ ሴት ሲሆን ተገቢውን ሕክምና መከልከላቸውንም ለማወቅ ተችሏል፡፡

     የአትሌቶቹ ቤተሰቦች በአሁኑ ወቅት በአትሌቶች ላይ የከፋ ችግር ሊደርስባቸው እንደሚችል በጣም የሰጉ መሆናቸውን ገልፀው ዓለም አቀፍ ስብዓዊ መብት ተከራካሪዎች፣ ሰላም ወዳዶችና ዴሞክራቲክ ኃይሎች አትሌቶቹ በአስቸኳይ በነጻ እንዲለቀቁ አስፈላጊውን ግፊት ሁሉ እንዲያደርጉ በአጽንኦት ጠይቀዋል፡፡






Reddit!Del.icio.us!Facebook!Slashdot!Netscape!Technorati!StumbleUpon!Newsvine!Furl!Yahoo!Ma.gnolia!Free social bookmarking plugins and extensions for Joomla! websites! title=
Comments (0)Add Comment

Write comment
quote
bold
italicize
underline
strike
url
image
quote
quote
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley

security code
Write the displayed characters


busy
 


Quick Jump

Ethio Date & Time

ዛሬ ቀኑ:

Calendar Converter




Daylight Saving