|
አባቷ የቅንጅት አባል በመሆናቸው እርዳታ ተከለከለች |
|
|
|
Thursday, 17 July 2008 |
|
በደቡብ ኢትዮጵያ በጎፋ ልዩ ዞን በደምባ ጎፋ ወረዳ በያላ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ ነዋሪ የሆነች ብርቱካን ብርሃኑ የተባለች አንዲት መናገርና መስማት የተሳናት ሴት አባቷ አቶ ብርሃኑ ኃይሌ የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ አባል በመሆናቸው ብቻ ሰብዓዊ እርዳታ መከልከሏን የዓይን ምስክሮች ሰሞኑን ገለጡ፡፡
እንደ የዓይን ምስክሮች አገላፅ ብርቱካን ብርሃኑ ማንነቱ በውል በማይታወቅ ሰው ተደፍራ የወለደችው የስምንት ወር ህፃን ያላት ሲሆን አባቷ ልጃቸው እርዳታ እንዲሰጣት አቶ ዘነበ ዘዋን የያላ ቀበሌ ሊቀመንበርን ደጋግመው ቢጠይቋቸውም ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በተያያዘ መልኩ ወይዘሮ ደስአለኝ ቱቶ የቀበሌው ሥራ አስኪያጅ ለዚህች ምስኪን ሴትና ለስምንት ወር ሕፃን ልጇ እርዳታ መከልከሉን በመደገፋቸው የአካባቢያቸው ነዋሪ ሴቶች በከፍተኛ ንቀትና ትዝብት እንዳዮዋቸው ከቦታው የደረሱን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡
ባሁኑ ወቅት እናትና ልጅ በከፍተኛ ችግር ላይ የሚገኙ መሆናቸውን አስረድተው በሰብዓዊነት አቋም ማንም ሰው እርዳታ ሊያደርጉላቸው እንደሚገባ የዓይን ምስክሮች አክለው ተናግረዋል፡፡
|