|
በሰሜን ጎንደር ሕዝቡ በረኃብ መጠቃቱ ተገለጠ |
|
|
|
Thursday, 17 July 2008 |
|
በሰሜን ጎንደር ዞን በዳባት በወገራና በጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች ውስጥ ሕዝቡ በከፍተኛ ደረጃ በረኃብ መጠቃቱን የውስጥ ዐዋቂ ምንጮች ሰሞኑን ከሥፍራው አመለከቱ፡፡
እንደ የውስጥ ዐዋቂ ምንጮች አገላለፅ በወገራ ወረዳ ቤተሰቦቻቸው በረኃብ ሲያልቁ ላለማየት የቆረጡ አባወራዎች ለአያሌ ዓመታት የኖሩበትን ቀዬ ለቅቀው በመሰደድ ላይ የሚገኙ ሲሆን በዳባት ወረዳ በጨርብሣ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ ደግሞ የሥርዓተ አገዛዙ አካላት በምግብ ለሥራ መርሐ-ግብር ሁለት ወር ሙሉ አሰርተው በነፍስ ወከፍ 1ዐ ኪሎ ግራም ጤፍና 1 ሊትር ዘይት ብቻ በመስጠታቸው ሕዝቡ ቅሬታውን በመግለፅ ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡
እንዲሁም በጎንደር ዙሪያ ረኃብ በማየሉ ሕዝቡ በአብያተ ክርስቲያንና በመስጊዶች በመሰብሰብ ክርስቲያኑ ህብረተሰብ ብር 15.ዐዐዐ /አሥራ አምስት ሺህ/ ሙስሊሙ ደግሞ ብር 3ዐ.ዐዐዐ /ሰላሳ ሺህ/ አዋጥቶ በነዋሪዎች መካከል በኑሮ ደረጃቸው እጅግ ችግርተኛ ለሆኑ እርዳታ ለማድረግ የራሱን ኮሚቴ በማቋቋም በእንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝ ከጎንደር ከተማ ምንጮች አክለው ገልጠዋል፡፡
|