RSS 2.0 Email us: webmaster@mahder.com

Ethiopia: Mahder.com -Ultimate Ethiopian News and Information Portal

Saturday
Nov 22nd
Home arrow News arrow በአርባ ምንጭ የሁለት ደብሮች አስተዳዳሪ ታሰሩ
በአርባ ምንጭ የሁለት ደብሮች አስተዳዳሪ ታሰሩ Print E-mail
Monday, 04 August 2008

 

በጋሞ ዞን በአርባ ምንጭ ከተማ የመንበረ ቅዱስ ሚካኤልና ገብርኤል ደብሮች አስተዳዳሪ አባ ኃይለሚካኤል ታደሰ በዞኑ ፖሊስ መምሪያ ከሐምሌ 23 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም  አንሥቶ በእሥር ላይ እንደሚገኙ ሰሞኑን ምንጮች ከአርባ ምንጭ አስታውቀዋል፡፡

     አስተዳዳሪው የታሰሩበት ምከንያት ምን እንደሆነ ከአገዛዝ አካላት ያልተገለፀ ሲሆን አንዳንድ የአርባ ምንጭ ነዋሪዎች እኚህ የሐይማኖት አባት በሐዝብ ዘንድ ተወዳጅ በመሆናቸው ብቻ እንዲሁ ሰበብ ተፈልጎ የታሰሩ መሆናቸውን ሲናገሩ መደመጣቸውንም ምንጮች አክለው ገልፀዋል፡፡

     አባ ኃይለሚካኤል በግልፅ ተለይቶ በጭብጥ የተመለከተ የክስ ቻርጅ ባይደርሳቸውም ፍርድ ቤት ቀርበው ወደ ማረፊያ ቤት የተመለሱ መሆናቸውን ምንጮች አስረድተዋል፡፡

     ይህ በእንዲህ እንዳለ በአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪ የሆኑት 1 አብዮት አጌና 2. አንዱዓለም አጌና 3. ባንትይርጉ በገራ 4. ሰሎሞን ተካልኝ 5. ዓለማየሁ ጌታ እንዲሁም 6. ይርጋዓለም ታፈሰ የተባሉ ግለሰቦች ከሐምሌ 21 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም አንሥቶ በእሥር ላይ እንደሚገኙ ምንጮች ከአርባ ምንጭ አመለከቱ፡፡

     እንደ ምንጮቹ አገላለፅ ግለሰቦቹ ተይዘው ሊታሰሩ የበቁት "የከተማውን ሀብረተሰብ ለዐመፅ አነሣሥታችኋል" በሚል ሰበብ ሲሆን ከተሰሩበት ወቅት አንሥቶ አስከካሁን ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውንም ለማወቅ ተችሏል፡፡






Reddit!Del.icio.us!Facebook!Slashdot!Netscape!Technorati!StumbleUpon!Newsvine!Furl!Yahoo!Ma.gnolia!Free social bookmarking plugins and extensions for Joomla! websites! title=
Comments (0)Add Comment

Write comment
quote
bold
italicize
underline
strike
url
image
quote
quote
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley

security code
Write the displayed characters


busy
 


Quick Jump

Ethio Date & Time

ዛሬ ቀኑ:

Calendar Converter




Daylight Saving