RSS 2.0 Email us: webmaster@mahder.com

Ethiopia: Mahder.com -Ultimate Ethiopian News and Information Portal

Saturday
Nov 22nd
Home arrow News arrow አንድ የቅንጅት አባል ፍትሕ ማጣታቸውን ገለጡ
አንድ የቅንጅት አባል ፍትሕ ማጣታቸውን ገለጡ Print E-mail
Sunday, 10 August 2008

     አቶ እሸቱ ከበደ ሸንቁጥ የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ አባል ንብረታቸውን በሥርዓተ-አገዛዙ ካድሬዎችና በግብረ አበሮቻቸው ተዘርፈው እስከ ዛሬ በሕግ አግባብ ተገቢውን ፍትሕ ያላገኙ መሆናቸውን ሰሞኑን ገለጡ፡፡

 

 

     ቀደም ሲል በአርሲ ዞን በደዴታ ወረዳ በዴራ ከተማ በዐ1 ቀበሌ ነዋሪ የነበሩትና ባሁኑ ጊዜ ተባርረው በአዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙት አቶ እሸቱ ንብረታቸውን የተዘረፉት ሚያዝያ 4 ቀን 1998ዓ.ም ከሌሊቱ በ8 ሰዓት ላይ እንደነበር አስረድተው ከዚያን ጊዜ አንስቶ ለሥርዓተ-አገዛዙ የሕግ አካላት በተከታታይ ቢያመለክቱም ለጉዳያቸው ትኩረት የሚሰጥ አካል ማጣታቸውን በምሬት ተናግረዋል፡፡

     በነበሩበት በዴራ ከተማ አራት ጊዜ ታሥረው የተፈቱ ከመሆናቸውም በላይ በቀን ሁለት ጊዜ ወደ ተዘጋጀላቸው ሥፍራ እየቀረቡ እንዲፈርሙ ይገደዱ እንደነበር የተናገሩት አቶ እሸቱ ቤተሰባቸውም ተበትኖ በከፍተኛ ችግር ላይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

     በጠቅላላው ከብር አሥር ሺህ በላይ ዋጋ የሚያወጣ ንብረት የተዘረፉ መሆናቸውን የገለፁት አቶ እሸቱ በመጨረሻም የሰብዓዊ መበቶች ድርጅቶችና የሚመለከታቸው አካላት በግፍ የተዘረፈው ንብረታቸው እንዲመለስላቸው የበኩላቸውን ግፊት ሁሉ እንዲያደርጉ አበክረው ጠይቀዋል፡፡






Reddit!Del.icio.us!Facebook!Slashdot!Netscape!Technorati!StumbleUpon!Newsvine!Furl!Yahoo!Ma.gnolia!Free social bookmarking plugins and extensions for Joomla! websites! title=
Comments (0)Add Comment

Write comment
quote
bold
italicize
underline
strike
url
image
quote
quote
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley

security code
Write the displayed characters


busy
 


Quick Jump

Ethio Date & Time

ዛሬ ቀኑ:

Calendar Converter




Daylight Saving