|
ለአቡነ ቲዎፍሎስ መታሰቢያ - ወንድወሰን ሰብስ |
|
|
|
Tuesday, 09 September 2008 |
|
ያችን ቀን ያችን ሰአት
እመብርሃን ብሎ ሲለምናት
ለሀገሩ ዋጋ ሊከፍል ህይወት
ጼጥሮስ ዝም ፅጥ አለ ላፍታ
ፊቱ ድቅን እያለ ሲያመነታ
ሀገሪን ኢትዮጺያን አደራ
ልጆቾዋም ባአንድ ላይ በጋራ
እንዳይነካቸው የከፋ ነገር መራራ
የረመኔዎች ጥሪ ሳይረብሽው
ቀሪውን እስረኛ ባረከው
ሞትን እንደማይፈራ ነግሮቸው
ዳግም በዛች ቤት ላይቆይ
በኩራት የግፍ ፅዋውን ተቀበለ
ጼጥሮስ ቴዎፍሎስን ወልዶ ሆነ መንታ
እመብርሀን አንቺ እርጂኝ
ከፍርሃት ማእበል አውጭኝ
እንዳአባ ኤፍሪም በሰረገላ አጋልቢኝ
በእምነት በማተቢ አፅኒኝ
ክህደት ፍርሃትን አታሳይኝ
ውዳሴ ማርያምን ደግሜ
ወጥቼ ወርጄ ነበር ደክሜ
እኔም እንደ ጌታዬ ይፍሰስ ደሜ
አልሄድም እናቴን አስቀይሜ
ውዳሴሽን ይዠአለሁና ተከተይኝ
የአለም ክብረ ነዋይ ሳያጎጎኝ
የኢትዮጵያን ጥፋት ሳያሳየኝ
እንደ ሰማእታቱ በሆንኩኝ
የወገኖቼን ስደት መከራ
ለመጭው ትውልድ የሚያበራ
ጀግና አንበሳ አስቀራ
የኢትዮጵያን ላት አሳፍረህ
አምላኬ እመብረሃንን ብለህ
ከአረመኔዎች እጅ ታደጋት
ጭሆት ልቅሶዋን ተመልከት
ኢትዮጲያን ሃገሪን ከልላት
እመብረሃን እናታለም እማማን አደራ
ህዝቦቹዋን ታደጊ ከክፉ መከራ
ኢትዮጲያውያንን ብለሽ
ፀሎት ልመናቸውን ሰምተሽ
ታደጊያቸው እባክሽ
ያስራት በኩራት ልጆችሽ
እንባቸውን አብሺ በልጅሽ
ላንቺ ልባቸው አይሰንፍም
አንቺን ብለው አያፍሩም
መከራቸው በዝቶአልና እመብርሃን
የግፍ የበደል ዘመንን
በቃችሁ በይ እመብርሃን
መከራው ችግሩ በዝቶአልና
የሃገሪቱን በሽታ እረሃብ ገበና
እመብርሃን አንቺ ከልሊና
ባንቺ የታመነ ሰው አይወድቅምና
እኔም በባለጊዜዎች ተይዤአለሁና
ሀገሪን ኢትዮጺያን አደራ
ልጆቾዋም ባአንድ ላይ በጋራ
እንዳይነካቸው የከፋ ነገር መራራ
የረመኔዎች ጥሪ ሳይረብሽው
ቀሪውን እስረኛ ባረከው
ሞትን እንደማይፈራ ነግሮቸው
ዳግም በዛች ቤት ላይቆይ
በኩራት የግፍ ፅዋውን ተቀበለ
ወንድወሰን ሰብስ
COVENTRY
|