|
Wednesday, 10 September 2008 |
|
ምን ያደርጋል ቢነገር
የሚያውቁሽ ሁሉ ከዱሽ
በአንድነት በጀግንነት የተከበርሽ
ዛሪም ገናንነት ያአልተለየሽ
መታወቂያ መለያ ሆኖ ረሀብሽ
የእድሚ ባለጸጋ መባል ለመከበር
እድሚሽ ሲቆተር ሲነገር
መታወቂያሽ ታሪክሽ ነበር
እንደ ቀድሞ ዛሪም ከአለም ቀደምሽ
የረሀብ የድህነት ታሪክሽ
ሊቀር ነው ውርስ ለልጆችሽ
አጋለቱሽ እንጂ ለምዝበራ ለብዝነዛ
የስነ ጽሁፍ የፍልስፍና ታርዛ
ማንነትሽን ለማጥፋት ደብዛ
ታሪክሽን ቀይረው በዋዛ በፈዛዛ
አሳልፈው ለባእድ ሰቱሽ
በሀዘን በዋይታ ተቆራመድሽ
ጥቁሩም ነጭም አንድ ሆኑብሽ
እማማ እናቲ እናት አለም
ሰምቻለሁ ከሩቅ ሀገር ሁሉንም
የሀዘናችን ማብቂያ ቀኑም
የናትና የሀገር ትርጉም
ለኒ አንድ ናቸው ሁለቱም
ሀገሪን ሳስታውስ እናቲንም
መነታተል መለያየት አልችልም
ይመልከትሽ መዳህኔለም
የደጋጎቹ ጸሎት ይተብቅሽ
የሽዋ ጸሀይ ታብራልሽ
እመብርሀን በቃልኪዳኑዋ ትይሽ
ይገባሸል እና ላአስብሽ
እሱዋ ናትና ዋስ ተበቃሽ
የሀዘን ዳር ታድርግልሽ
ቀና ብለን እንድንሂ ልጆችሽ
ደርሶ ልመና ጸሎትሽ
ሁሉም ባገር ነውና የሚያምረው
የስደት እንግልት መከራው
አልቆአል ቀርቦአል መችረሽው
እማማ እናቲ ምን ልበልሽ
ኅይለማርያም ይውረድ በላይሽ
በሀዘን አነባለሁ ሳስብሽ
እየታየኝ መከራ ስቃይሽ
በቢትሽ አድገው ገደሉሽ
ብድርሽ ይሂ ሆነ ውለታሽ
አንቺን ማናደድ መስሎአቸው
ባንቺ እንግልት መደሰታቸው
መጥፊያቸው ነውና ታገሸቸው
ተሰብስበን ልንገባ ሀገራችን
የዘር ልዩነት ቀርቶልን
እማምላክ ወላዲቶዋ ሰምታን
እማማ እናቲን የድሮዋን
በበደልናት ሁሉ ይቅር ብለን
እጁዋን ዘርግታ ልትይዘን
ፈታሪን አመስግነን ተደስተን
እንደልማዱዋ ልትይዘን ልትችለን
ልመና ምጽዋቱን ትተን
ልንበላ ልንኖር ነው ተቻችለን
ወንድወሰን
COVENTERY
England
|