RSS 2.0 Email us: webmaster@mahder.com

Ethiopia: Mahder.com -Ultimate Ethiopian News and Information Portal

Tuesday
Jan 06th
Home arrow News arrow በመኢአድ አባላት ላይ አፍናው ቀጥሎል
በመኢአድ አባላት ላይ አፍናው ቀጥሎል Print E-mail
Monday, 06 October 2008

የመኢአድ አባላት ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወደ

ወህኒ መውረዳቸው ተገለጠ፡፡

    በሰሜን ጎንደር ዞን በጭልጋ ወረዳ በጨንድባ ንዑስ ከተማ ውስጥ ነዋሪ የነበሩ ዘጠኝ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት አባላት ከግንቦት ወር 2ዐዐዐ ዓ.ም አንሥቶ ለወራት በወረዳው ዋና ከተማ በአይከል ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ሲማቅቁ ቆይተው ባሁኑ ወቅት ያለ ፍ/ቤት ትዕዛዝ ወደ ወህኒ ቤት መውረዳቸው ተገለጠ፡፡

 

    በፖሊስ ጣቢያ ታስረው በነበሩበት ወቅት የደረሰባቸውን በደል ለበላይ አካል አመልክተው አንዳችም ውሣኔ ሳያገኙ የቀሩት እነዚህ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት አባላት "1. ዋኘው ታደሰ 2. መኳንንት ስንሻው 3. አለህኝ መኳንንት 4. ከፈለ ታደገ 5. ደምስ የኋላ 6. ከላጅ ጀግኔ 7. ተፈራ ዓለሙ 8. ሠጠኝ ታደገና 9. እንዳለ ታደገ የተባሉ መሆናቸውንም ምንጮች አክለው ገልፀዋል፡፡

    አባላቱ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ባልያዙ የፖሊስ አባላት ከየመኖሪያ ቤታቸው ተለቅመው የታሠሩ ሲሆን በግልፅ ጭብጥ የተደራጀ የክስ ቻርጅ ያልደረሳቸው መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል፡፡

    ባሁኑ ወቅት የአባላቱ ቤተሰቦች በከፍተኛ ችግር ላይ የወደቁ ሲሆን ልጆቻቸውም ትምህርታቸውን ተረጋግተው ለመከታተል እንዳልቻሉ ታውቋል፡፡

ሁለት የመኢአድ አባላት ቤታቸውን ተቀምተው

ቤተሰቦቻቸው መበተናቸው ተገለጠ፡

    አቶ ገነት አበሻ በመተከል ዞን በፖዌ ልዩ ወረዳ በመንደር 4. ውስጥ ነዋሪና አቶ ባትሪ ዱኔሮ በልዩ ወረዳው በቀጣና 1. በመንደር 5. ይኖሩ የነበሩ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት አባላት ለዓመታት የኖሩበትን የግል መኖሪያ ቤታቸውን በአገዛዙ ሹማምንት ተቀምተው ለወራት ሲንከራተቱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ ቤተሰቦቻቸው መበተናቸውን ምንጮች አመለከቱ፡፡

    እንደ ምንጮቹ አገላለፅ ባሁኑ ወቅት የአባላቱ ቤተሰቦች ተበትነው በከፍተኛ ችግር ላይ የሚገኙ ሲሆን ለአካለ መጠን ያደረሱ ልጆቻቸውም በአካባቢያቸው በሚገኙ ክፍት የሥራ ቦታዎች ተቀጥረው እንዳይሠሩ ማዕቀብ እንደተደረገባቸው ምንጮች አክለው አስረድተዋል፡፡

    የአካባቢው የሥርዓተ አገዛዙ ሹማምንት በሟቾቹ የመኢአድ አባላት ቤተሰቦች ላይ የደረሰባቸውን በደል በማስመልከት ሰብዓዊ እርዳታ እንዲደረግላቸው ለቀረበላቸው ጥያቄ "ቅንጅት ሲነግሥ ይበላሉ፡፡ ቅንጅት ያብላቸው" በማለት የስላቅ መልስ መስጠታቸውንም ምንጮች ገልፀዋል፡፡

    የሟቾቹ አባላት መኖሪያ ቤቶች ለሥርዓቱ ታማኞች መስጠታቸውንም ከአካባቢው የዓይን ምስክሮች ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

በሣውላ  የመኢአድ ጉባዔን ለማሰናከል የተደረገው ሙከራ ከሸፈ፡፡

    በደቡብ ኢትዮጵያ በጎፋ ልዩ ዞን በሣውላ ከተማ የልዩ ዞኑን ዓመታዊ መደበኛ የመኢአድ ጉባዔ ለማሰናከል በአገዛዙ ሹማምንት የተደረገው ሙከራ በአባላቱ ቁርጠኝነት መስከረም 11 ቀን 2ዐዐ1ዓ.ም ከሸፈ፡፡

    በዕለቱ አቶ ከሣሁን ካሤ በሣውላ ከተማ የዮጫ ክፍለ ከተማ ሰብሣቢ ካይሻ ከለቻ የተባለ ፖሊስና ሁለት የአካባቢ ታጣቂዎችን አስከትለው ወደ ጉባዔተኞች ዘንድ በመሄድ ጉባዔው ሕገ ወጥ መሆኑን በመናገር ለማስፈራራት ሞክረዋል፡፡

    ሆኖም ጉባዔተኞቹ መኢአድ ራሱ ሕገ ወጥነትን የሚዋጋ ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ መሆኑን በማረጋገጥ ማስፈራሪያውን ውድቅ አድርገዋል፡፡

    ጉባዔው በዕለቱ የቀድሞ ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ስሙን ወደ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መለወጡን በሙሉ ድምፅ ተቀብሏል፡፡

    በዚህ ጉባዔ ላይ ከጎፋ ልዩ ዞን 12 ወረዳዎች የተወከሉ 12ዐ ጉባዔተኞች ተሳትፈዋል፡፡

በደባርቅ ሁለት የመኢአድ አባላት መታሠራቸው ተሰማ፡፡

    በሰሜን ጎንደር ዞን በደባቅር ወረዳ ውስጥ ሁለት የመኢአድ አባላት ከመስከረም 14 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም አንስቶ በእሥር ላይ እንደሚገኙ ተሰማ፡፡

    ቄስ መሐበ ታደሰ እንዲሁም ዲያቆን ይርጋ ታከለ የተባሉ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት አባላት ተይዘው የታሠሩት ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በፖሊስ አስገደጅነት ሲሆን የተሠሩበትም ምክንያት ያልተገለፀ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

    ባሁኑ ወቅት የደባርቅ ወረዳ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ኮሚቴ አባላት በየዕለቱ በገዥው ፓርቲ ታጣቂዎች የማስፈራራትና የማዋከብ ሁኔታ እየተፈፀመባቸው መሆኑ ተውቋል፡፡






Reddit!Del.icio.us!Facebook!Slashdot!Netscape!Technorati!StumbleUpon!Newsvine!Furl!Yahoo!Ma.gnolia!Free social bookmarking plugins and extensions for Joomla! websites! title=
Comments (0)Add Comment

Write comment
quote
bold
italicize
underline
strike
url
image
quote
quote
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley

security code
Write the displayed characters


busy
 

Useful Resources


Other top stories


Quick Jump

Ethio Date & Time

ዛሬ ቀኑ:

Calendar Converter




Daylight Saving