|
ለአፍሪካ ህብረት መስራቾች -ወንድወሰን ሰብስቤ |
|
|
|
Wednesday, 15 October 2008 |
|
ለአፍሪካ ህብረት መስራቾች
እኛ አናውቃችሁም እናንተም አታውቁን
እናንተ እሩህ ሩሆች ተነሱ አድኑን
በስም በዝናችሁ ዛሪ ያወቅናችሁ
ለአፍሪካ አህጉር መብራት ነበራችሁ
ህዝባችሁ ያነባል ሌት ተቀን ይደማል
ፈጣሪም እረስቶአል ያፍሪካን ምስል
እረሀብ ጦርነት ጭራሽ አጥቁሮናል
ለዚህ ለጥቁር ህዝብ ተቆርቁሪ ጠፍቱአል
መቃብር ከፍታችሁ ተነሱ አጽናኑን
ደርሰንላችሖል አይዞአችሁ በሉን
የሞታችሁ ሁሉ እረብድግ በሉ
አፍሪካ ነዳለች ተቃጠለች አሉ
ልጆቹዋም በረሀብ በባሩድ ተበሉ
የ ኦ.ኤ.ዩ መስራች ዛሬ የታላችሁ
ፍቅር ከተስፋ ጋር የተላበሳችሁ
አፍሪካን አድኑዋት አንድ ሆኖ ልባችሁ
ለጥቁር ተሙዋጋች እናንት ነበራችሁ
አፍሪካ አዳራሽ አቱዋል አሉ መላ
በ ተ.መ.ድ መመሪያ አፍሪካ ተብላላ
መንፈሳችሁ ይምጣ በአዳራሹ ይሙላ
ፈረሰ ታአሪኩ ቃልኪዳን መሀላ
ሰባዊነት ጠፍቶ ሁሉም ተጨካክኑዋል
በአፍሪካ አዳራሽ መመካከር ቀርቱዋል
ሁሉም ተናንቆ መዘላለፍ ሆኑዋል
ጡንቻ መተያያ ሆኑዋል አዳራሹ
ያራዊት ስብሰባ ሆኑዋል ባመሻሹ
በ.ተ.መ.ድ መመሪያ መጉዋዝ ተጀምሩዋል
በራስ መተማመን አዳራሹ ረስቱዋል
የአፍሪካውያን እድል በነጭ ተወስኑዋል
በንክዋሜንኩሩማ በፓትሪ ሉሙምባ
ቀ.ኅ.ሥ ሴንጎር በሀቢብ ቡርጊባ
ለአፍሪካ ተሙዋጋች ፈጥረው ነበር አንባ
ጆሞኬኒያታ ገማል አብድል ናስር
ፊሌክስ ሁፌት ጉዋኜ ያኔ የነበር ፍቅር
ዙሪያውን አጥረውት በአንድነት አጥር
አጥር ማገር ፈርሶ አፍሪካ ፈራርሳ
ያፍሪካውያን ኑሮ ሆኑዋል በዳሰሳ
ቀስቅስልን አምላክ ይነሱ የሞቱ
እስቲ ተነሱና አፍሪካን መስርቱ
ያአፍሪካ ልጆች በመቅሰፍት ተመቱ
እረሀብ ጦርነት በርክቱዋል ስደቱ
ለዚህ ለከርታታ ለጥቁር ህዝባችሁ
ከአፓርታይድ ግዛት ነጻ ያወጣችሁ
የአፍሪካን አንድነት የመሰረታችሁ
በአንድነት ተነሱ እስቲ እንያችሁ
አፍሪካ በጎሳ በመንደር ከልሉዋል
በመሪዎች ጡንቻ አፍሪካ ተረግጡዋል
የኛነታቸውን ፍጹም ጠርጥረናል
ፈጥሮ የነበረው አምላክም እረሳን
ደጉ ቀን ቅረበን ክፉ ቀን እራቀን
ወንድወሰን ሰብስቤ
COVENTERY
|