|
ለጀግኖች መታሰቢያ - ወንድወሰን ሰብስቤ |
|
|
|
Monday, 20 October 2008 |
|
ከልብ ለደከሙ ለኢትዮጲያ እማማ
ታሪካቸው ይውጣ ይነገር ይሰማ
እውቁ መሀንዲሱ ሐይለጊዮእጊስ ይስማ
ትምህርት ለሆድ ሆነ ጊዜው ተበላሸ
ጀግኖቹ ሄዱና ሳይነጋልን መሸ
ግራ ተጋብተናል ሀብተወልዶች ይምጡ
በአገር አስተዳደር ዘመኑን በለጡ
ከተማን ቀስቅሱ የቀሩም ይጠሩ
የቁርጥ ቀን ልጆች እንደወጡ ቀሩ
የማይጨው ያአድዋ ጀግኖቹ ተረሱ
ምኒልክ ቲዎድሮስ ዮሀንስ ይነሱ
ምን ይሉን ስንሄድ አረ ወደነሱ
አበበ አረጋይ መስፍን ተምሳስ ደሙ
በጠላት ተወራ ቀስቅሶአቸው ይስሙ
ባልቻ አባመላ ጀግኖቹ ተመሙ
ገበየሁ ነሲቡ ኅይለማሪያም ደስታ
በጀግኖች ልጆቹዋ ጣሊያን ተረታ
ገብረማሪያም ወያ ከፈለው የታለ
ከበደ ፅሐዩ አበብ በቀለ
ታፈሰ ይገዙ ዳምጠው ጫጫ በሉ
ወልደመስቀል ኮስትር ጀግኖቹ የታሉ
ተክሌ በሻህ ሀይሉ ጎበና ይነሳ
የዛ ሁሉ ጀግና ታሪኩ ተረሳ
መኮንን አፈወርቅ ውልዴ አጥናፉ ቀሩ
ጌታቸው ደምሰው አሉላ ድንበሩ
የአግርሪቱን መዥገር ተነሱና አባሩ
ዘራይም ተረሳህ በሮማ ድልህ
በሮማ አደባባይ ታሪክ የሰራህ
አገር ስትታመስ አብዲሳ አላየህ
መሬት ተናገሪ ጀግኖች የበላሽ
ገናናዋ አገር ከአለም የቀደምሽ
አርበኛሽን ጥሪው ይቁም ከፊትሽ
የጥቁሮች እንቁ ዳይመንድ የነበረች
ሆዳሙ በዛባት ኩሩ እንዳልወለደች
ህሊና በስልጣን አለውጥ ያለው
ህሊና በገንዘብ አልሸጥም ያለው
ይነሳ ያ ጀግና ክቡር የሆነ ሰው
ውለታ አልጠበቀም ከሀገሩ ብድር
ህይወቱን የሰጠው ላሁኑዋ ምድር
በመጠጥ አይደለም በፍቅር ስካር
ለካስ ያስገድላል የሀገር ፍቅር
ለካስ ያሰቅላል የሀገር ፍቅር
ስንቱ ሜዳ ቀረ ሳያገኝ ቀብር
እምድር ዝም ብለሻል ተነሽ ተናገሪ
ይህው በቀሉብሽ ሀገር አሳፋሪ
ይብቃን እንነሳ እንቁም ከበር
ፅዋው ሞልቶ ፈሶአል የጀግናው ብድር
ወገን ሰላም ያግኝ ውሎ እንዲያድር
በኢትዮጲያ ጉዳይ ለስር የበቃችሁ
ጠላት ለማንበርከክ በሜዳ የቀራችሁ
ጀግና እንደው ጀግና ነው ታሪክ ያስታውሳችሁ
ወንድወሰን ሰብስቤ
COVENTRY
|