RSS 2.0 Email us: webmaster@mahder.com

Ethiopia: Mahder.com -Ultimate Ethiopian News and Information Portal

Tuesday
Jan 06th
Home arrow News arrow ቅንጅትና አንድነት ለይቅል - የብርቱካን ጉብኝት
ቅንጅትና አንድነት ለይቅል - የብርቱካን ጉብኝት Print E-mail
Monday, 10 November 2008

በህዝብ ስቃይና ሞት መነገድ ይቁም!!!

ከነባር የቅንጅት ደጋፊዎችና አገር ወዳድ እትዮጵያዉያን ለንደን

    ቅንጅትን በመበተን ያሴሩ ያስተባበሩና ያበሩ ግለሰቦች እየተጓደኑ የተለያዩ አዳዲስ የፖለቲካ ድርጅቶች እንዳቋቋሙ ዉሎ ያደረ ጉዳይ ነዉ። ከነዚህ መካከል በወ/ት ብርቱካን ሚዴክሳ የሚመራዉ የአንድነት ፓርቲ "ቅንጅት አንድነት ሆኖአል አንድነት ቅንጅት ነዉ" በሚል መቀስቀስሻ የቅንጅትን ጫማ ለማጥለቅና ለመራመድ ሲሞክር ጫማዉ ሰፍቶበት አካሀዱ እየተዉረገረገ መሆኑ ግልፅ ሆኖ መጥቷል።

 

    በእንግሊዝ አገር ይህን የማስመሰል አካሀድ በማራመድ ቀደም ሲል ዶ/ር ብርሃኑ ነጋን በመጋበዝ ግንቦት 7ትን በቅንጅት የድጋፍ ወንበር በማስቀመጥ አሁን ደግሞ ወ/ት ብርቱካንን በመጋበዝ እዚያዉ የቅንጅት የድጋፍ ወንበር ላይ በማቆም በእንግሊዝና በሌላዉ የአዉሮፓ አገሮች የሚገኙትን የቅንጅት ደጋፊዎች በአስመሳይ አካሄድ ወደ ግንቦት 7 እና ወደ አንድነት ፓርቲ ለማዞር ሲዉተረተሩ እያየናቸዉ ነዉ። ይህ በእንግሊዝ አገር እራሱን "የቅንጅት ድጋፍ" እያለ የሚጠራ የቤተሰቦችና የጓደኞች ቡድን ቀደም ሲል "አለም አቀፍ አመራር" ብሎ ራሱን ይጠራ የነበረዉን ቡድን ባቀናጁ ግለሰቦች የሚመራ በብሪታኒያና በመላዉ አዉሮፓ ያለዉን የቅንጅት ድጋፍ በመበተን በመሳሪያነት ያገለገለ ቡድን ነዉ። አሁን ደግሞ በአስመሳይ የፖለቲካ ድጋፍን በዉርስ ለማዞር የማዉገርገርና የማወናበድ አካሄዱን ቀጥሎበታል። እነኝህ ድርጅቶች ለኢትዮጵያ ህዝብ ሊአቀርቡ የሚችሉት የፖለቲካ አማራጭ ካላቸዉ "ግንቦት 7" ሆነ "አንድነት" በራሳቸዉ ስም በራሳቸዉ ትክለሃሳብ ድጋፍ ለማግኘት መሞከር እንጂ ትናንት ረግጠዉ የወጡትን ቅንጅት "መንፈስ" እየተንተራሱ እራስን ማቅናት የማይቻል መሆኑን ከወዲሁ ሊገነዘቡት ይገባል።

    የኢዮጵያ ህዝብ መምረጥ መቻሉን በ97 ምርጫ አስመስክሮአል። የኢትዮጵያ ዲያስፖራም ቢሆን የህዝብን ጥያቄ የያዙ እንደ ቅንጅት እንደ ህብረት ያሉትን ድርጅቶች ሲአገኝ ለመደገፍ ቀስቃሽና አስተናጋጅ እንደማይፈልግ በተግባር አረጋግጧል። የማስመሰሉ አካሄድ በመጀመሪያ እራስን ከዚያ የተቃዋሚዉን ጎራ በበለጠ ደግሞ አገርን የሚጎዳ ስለሆነ መቆም አለበት። ቅንጅት ለምን እንደተበተነ ለደጋፊዉ ህዝብ መግለጫ ያልሰጡ መሪዎች በምንም ደረጃ የሚአካሂዱት ፖሊቲካ ተአማኒነት ሊኖረው አይችልም። ወ/ት ብርቱካን በቅንጅት ዉስጥ የተሰጣቸዉን ሃላፊነት ሳይወጡ የህዝብን አደራ ረግጠዉ ሌላ ድርጅት መስርተዉ ያንኑ ህዝብ ላንተ ቆመናል ሲሉ በህዝብ ስቃይና ለቅሶ ማፌዝና መቀለድ መሆኑ ተስኖአቸዉ ይሆን? እንመራሃለን ደግፈን ሲሉት የደገፈን ህዝብ፤ መሪዎቼን አላስነካም ቢሎ ደረቱን ለጥዪት በመስጠት አመኔታዉን ያሳየን ህዝብ፤ ስለመረጠ ስለደገፈ ግንባሩን በጥይት ተመቶ በየቦታው የወደቀን ህዝብ፤ በአስርተ ሺዎች ለእስራትና ለድብደባ በተዳረገ ህዝብ መሰዋትነት ላይ እንዴት ይነገዳል ይቀለዳል? ከቤትህ አትዉጣ ሲሉት የተቀበለን፤ የመኪናህን ጥሩንባ አጩህ ሲሉ በአደባባይ ያስተጋባን፤ ከስራህ ቅር፤ ሱቅህን ዝጋ ሲሉት ያለማወላወል የፈጸመ ህዝብ ያሳየዉን ቁርጠኝነት ታሪክ ዘግቦታል። በዚህም የተነሳ በብዙ መቶ ሺዎችህ የሚቆጠሩ በእስር እንደተንገላቱ፤ ከስራቸዉ እንደተፈናቀሉና የመተዳደሪያ ንግዳቸዉን እንደተነጠቁ ይታወቃል።

    ወ/ት ብርቱካን ግን የሙታን ቤተሰብን ሳያጽናኑ፤ በእስራት ለታፈኑት ምንም ድጋፍ ሳያረጉ ከመሰል ጓደኞቻቸዉ ጋር በአሜሪካን ከተማ "ዲያስፖራዉን ለማመስገን" በሚል ስም ያስመረጣቸዉን የደገፋቸዉንና የሞተላቸዉን ህዝብ ትተዉት ወጡ። ከዚያም አልፎ በአሜሪካን ኮንግሬስ ተገኝተዉ በእስር ያለዉ ሰዉ 100 አይሞላም ብለዉ ቃላቸዉን ሰጡ። ይህን እንደተናገሩ አከታትሎ ወያኔ 17800 እስረኞችን በነጻ ለቅቄአለሁ ሲል አስታወቀ። ለህዝብ የቆመ መሪ በመካከሉ ተገኝቶ ከደረሰበት ጉዳት እንዲአገግም ይደግፈዋል እንጅ ከአገር ወጥቶ በጉዳቱና በደረሰበት እመቃ አይሳለቅበትም። ቅንጅት ፓርላማ ለመግባት የህዝብ ድምጽ መከበር አለበት ስላለ አመራሩ ወ/ት ብርቱካንን ጨምሮ በቃሊቲ ከአመት ተኩል በላይ ታሰሩ። ከእስር ከተለቀቁ በኋላ፤ ወ/ት ብርቱካን አካሂዳቸዉን ቀይረዉ ከወያኔ ጋር አብረን እንሰራለን፣ የትግራይ ህዝብን በማስቀየማችን ይቅርታ እንጠይቃለን ሲሉ ሰንብተዋል። አሁን ደግሞ በቅንጅት ስም ተመርጠዉ ፓርላማ በገቡት 2/3 የፓርላማ አባሎችን ይዘው አዲሱ ፓርቲያቸዉን "አንድነትን" በፓርላማ እንዳለ ሆኖ ሲሙ ይያዝልን ብለዉ በጽሁፍ አቅርበዉ ወያኔን ደጅ ጥናት ይዘዋል። ይህንን በማድረጋቸዉ ፓርላማ አንገባም ባሉበት ግዜ ለነሱ ነፃነት የተሰዋዉን የብዙሃኑን ደጋፊ ህይወት ከምንም ሳይኮጥሩ የፓርላም መቀመጫ ለማግኘት እየተራወጡ ነዉ።

    እኛ በእንግሊዝ አገር የምንገኝ አገር ወዳድና የቀድሞ ቅንጅት ደጋፊዎች፣ አሁንም እንደበፊቱ ደግመን ደጋግመን ወ/ት ብርቱካንና አንድነት ፓርቲያቸዉን እንዲሁም መሰሎቻቸዉን የምንላቸዉ፣ ለመበተን በተባበራችሁበት የቅንጅት ስምና በስሙ በተሰበሰበ ድጋፍና ጥሪት ተመርኩዛችሁ አዲሱን ቤታችሁን ማደራጀት የሞራል ድሽቀት ነዉና ይህን ማወናበድ እንድታቆሙ እንጠይቃለን። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ሁሉ፣ የትናንቱ በህዝብ ስቃይ መቀለድ አልበቃ ብሎ ዛሬም በነዛዉ በተሰዉት የኢትዮጵያ ዉድ ልጆች ስም ከዲያስፖራ ገንዘብ ለመሰብሰብ ወደዚሁ አዉሮፓና አሜሪካ እንዳመራችሁ እዉቅ ነዉ። የሙታን ቤተሰቦች "አባወራችን በቅንጅት ምክንያት ተገደለ/ች ጦማችንን አደርን እርዱን ደግፉን" በሚሉበት በአሁኑ ወቅት የቅንጅትን ለቅንጅት በማድረግ ቤተሰቦቹ እንዲረዱ ማረግ የሞራል ግዴታ ነዉ። ሆኖም ወ/ት ብርቱካንና ፓርቲያቸዉ ከዚህ በፊት በቅንጅት ሰማእታት ስም እየተማጸኑ ባጋበሱት ገንዘብ እስካሁን ምንም እርዳታ  ሳያደርጉ አሁንም በነዛዉ ሰማእታት ስም ለመነገድ መሞከራቸዉ የህሊና ቢስነትና የሞራል ዝቅተኛነት ነዉ እንላለን።

    እኛ በእንግሊዝ አገር የምንገኝ አገር ወዳድና የቀድሞ ቅንጅት ደጋፊዎች፣ አሁንም እንደበፊቱ ደግመን ደጋግመን ወ/ት ብርቱካንና አንድነት ፓርቲያቸዉን እንዲሁም መሰሎቻቸዉን የምንላቸዉ፣ ለተነሳችሁበት አላማ እርግጠኛነትና እምነት ካላችሁ አዲስ ስማችሁን በማንገብ አዲስ አላማችሁን በማዉለብለብ አባልና ድጋፍ መሰብሰብ መብታችሁ ነዉ። ከዚህ ባሻገር ግን ከቅንጅት መቃብር የወጣን ቅንጅት ነን እያላችሁ ለወገኑና ለአገሩ በአንድነት የቆመዉን ህዝብ አትከፋፍሉት። በአሁኑ ሰአት በእንግሊዝ አገርና በአዉሮፓ የሚታየው አካሄድ ከፋፋይና አጥፊ ስለሆነ በአስቸኳይ መቆም አለበት። ካልቆመ እንታገለዋለን በዚህም በተቃዋሚ ጎራ ለሚደርሰዉ ይበልጥ መከፋፈልና መዳከም ሃላፊነቱ ከናንተው ራስ አይወርድም።

በህዝብ ስቃይና ሞት መነገድ ይቁም!!!

ሴረኛነትና የፖሊቲካ ቅጥፈት ይቁም!!!

መከፋፈል መዳከም ነዉ መሰባሰብ መጠናከር ነዉ!!!

ዲሞክራሲ፣ አንድነትና፣ እኩልነትን ላጣመረች ኢትዮጵያ እንታገል!!!

ህዳር 2001

PDF Version






Reddit!Del.icio.us!Facebook!Slashdot!Netscape!Technorati!StumbleUpon!Newsvine!Furl!Yahoo!Ma.gnolia!Free social bookmarking plugins and extensions for Joomla! websites! title=
Comments (0)Add Comment

Write comment
quote
bold
italicize
underline
strike
url
image
quote
quote
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley

security code
Write the displayed characters


busy
 

Useful Resources


Other top stories


Quick Jump

Ethio Date & Time

ዛሬ ቀኑ:

Calendar Converter




Daylight Saving