|
ለፕሮፊሰር አስራት ወልደየስ - ለፕሮፊሰር አስራት ወልደየስ |
|
|
|
Tuesday, 18 November 2008 |
|
ለፕሮፊሰር አስራት ወልደየስ
80ኛ አመት ልደት መታሰቢያ
አሥፍራትን ከፍለናል ለኢትዮጵያ እዳ
ምድሪቱን እንዲለቅ አድርባዮ ባንዳ
አሥራት ተከፍሎላት ካልዳነች እማማ
ዘንድሮ ማብቂያው ነው ስልጥእኑን ይቀማ
ለክልል አይደለም አስራት የከፈልነው
ለመንደር አይደለም አሥራት የከፈልነው
ለመጭው ትውልድም ለኢትዩጵያዊውነው
ጀግናው አዛውንቱ አምርረው አለቀሱ
አላግባብ ከፈልነው አሥራትን መልሱ
ችቦውን አብሩለት ስሙን አወድሱ
ሰውን ያሳዘነው በባንዳ መርከሱ
ሙሾው ወረደ አሉ በለገሀር ሜዳ
ኬትም ተለቃቅሞ የመጣው ከሜዳ
ተጨንቁዋል ተጠቡዋል ባንዳ አቱዋል ቀዳዳ
አንበሳውን ገለው አንበሶች ተነሱ
ጠላትን ሊያጠፉ በክርን ሊደቁሱ
የማይጨው ያድዋው ጀግኖቹ ተረሱ
ሰዎች ባአንድነት አስራት አስራት በሉ
የሱን ፈለግ ይዘው ህጻናቱ ሁሉ
አንድት አንድነት አንድነት እያሉ
በጠላት ጆሮ ላይ ሁሌ ያዜማሉ
ፈጣሪ ያውቅሀል ልብህን በእውነት
ለሞት የዳረገህ የፍቅር ቅንነት
ይመስክር ውስጣችን አይደለም በአንደበት
ይሄ ነው አላማው ያበቃው ለሞት
እውነት ይዞ ሄዱዋል ሀኪሙ አስራት
እነሱ ቢገሉህ አንተ አልሞትክላቸው
እስር ቤት በኩራት ተቀመትክላቸው
በሞያህ ምስጉን ነህ አለም ያደነቀህ
ምስጋና ሰምተናል ፈረንጅን ፈውሰህ
ምናለ ድትሄድ እኛንም አድነህ
አንተ ጠፍተህብን በሽታው ጎዳን
አንተን የሚመስል ማንስ ያድነን
አቀበት ቁልቁለት ውጣን ወረድን
አንተ የሄድክበት መንገዱ ጠፋን
እምነት ከስራ ጋር እግዜር የቸረህ
እውነትን በስራ ላገር ያሳየህ
ስመ ጥሩ አርበኛ ሙሁር አንተ ነህ
ይነገር ይታወቅ ይነበብ ስራህ
የሀገር ፍቅር ስሜት ለሞት አበቃህ
ወንድወሰን ሰብስቤ
2008 DES COVENTRY
|