RSS 2.0 Email us: webmaster@mahder.com

Ethiopia: Mahder.com -Ultimate Ethiopian News and Information Portal

Wednesday
Jan 07th
Home arrow News arrow መንግስት የመኢአድን የጎዳና ላይ ቅስቀሳ አገደ-ድብደባ ፈፀመ
መንግስት የመኢአድን የጎዳና ላይ ቅስቀሳ አገደ-ድብደባ ፈፀመ Print E-mail
Sunday, 30 November 2008

መንግስት የመኢአድን የጎዳና ላይ ቅስቀሳ አገደ

በአባሎቹም ላይ እስራትና ድብደባ ፈፀመ፡፡

     መኢአድ በአዲስ አበባ በምሥራቅና በምዕራብ ቀጣናዎች እያካሄደ ባለው የጎዳና ላይ ቅስቀሳው ቅዳሜ ህዳር 20, 2001 ዓ.ም በሁለቱም መኪኖቹ ያሉት አባላቱና መኪኖቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሲሆን በቂርቆስ ፖሊስ ጣቢያ የታሰሩት የአንደኛው መኪና ቀስቃሾቹም ድብደባ የደረሰባቸው መሆኑን ከሥፍራው የደረሱ የፓርቲው አባላት ገልፀዋል፡፡

 

     የምስራቅ አዲስ አበባ ቀጠና ቀስቃሾች  ከጽ/ቤቱ ተነስተው በስታዲየም እየቀሰቀሱ ወደ ቂርቆስ አካባቢ በመንቀሳቀስ ላይ እንዳሉ ለገሃር አካባቢ በፖሊስ ተይዘው ወደ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዋል፡፡

     በራሪ ወረቀቶቹን የበተኑና የተቀበሉ ሰዎችም ከጉምሩክ በወጡ የፌደራል ፖሊስ ድብደባ እንደደረሰባቸውና አንዳንዶቹም አካላዊ ጉዳት እንደደረሰባቸው አካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞች ወዲያውኑ ወደ ፓርቲው ጽ/ቤት በመደወል ገልፀዋል፡፡ በቂርቆስ ፖሊስ ጣቢያ የታሰሩትን የመኢአድ ቀስቃሾች በመኪና ለይ የሰቀሉትን አረንÕዴ ቢጫ ቀይ ቀለም ያለውን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ፖሊሶች የህ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አይደለም ብለው አስወርደው የተቀበልዋቸው ሲሆን አረንÕዴ ቢጫ ቀይ ቀለም ያለው በእጅ ላይ የሚደረግ ባንዲራቸውንም እያስወለቁ የቀሙዋቸው መሆኑን ታሳሪዎቹ ከስፍራው ገልጸዋል፡፡ በአካባቢው የነበረው ህዝብ ፖሊስ ጣቢያውን ከቦ በማስቸገሩ የመኢአድ ባነሮችና መፈክሮችን ፖሊስ  ከመኪናው ላይ ያነሱት መሆኑ ታውsል፡፡ ከቦ በመጠባበቅ ላይ የሚገኘውንም ህዝብ በፖሊስ ተባረዋል፡፡   

     ወደ ምዕራብ አዲስ አበባ ቀጠና የተንቀሳቀሰው መኪና ጉዞውን ወደ ኢዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ለማድረግ እንደተነሳ ብዙም ሳይሄድ ፒያሳ አካባቢ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ሊውል ችሏል፡፡

     ህዳር 18 ቀን 2001 ዓ.ም ቅስቀሳው በተጀመረ ወቅት የፖሊስ ሠራዊት በድምጽ መቀስቀስ አትችሉም ወረቀት በመበተንና በሙዚቃ ግን ይቻላል ሲል፣በህዳር 19 ቀን 2001 ዓ.ም ደግሞ የቴዲን ዘፈን ማሰማት አትችሉም ወረቀት መበተን ግን ፈቅደንላቸኋል ብለው ለተወሠነ ሰዓት የፓርቲውን አባሎች በቁጥጥር ስር አውለው መልቀቃቸው ይታወሳል፡፡ ህዳር 20 ቀን 2001 ዓ.ም ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ቅስቀሳውን ማቆም አለባችሁ በማለት የመኢአድ አባሎች ከነመኪናቸው ታስረዋል፡፡

     በውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም በነገሩ ጣልቃ በመግባት ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተሉት ሲሆን በሁኔታውም ማዘናቸውን ገልፀዋል፡፡ ከውጪ የሚገኙ የፓርቲ ደጋፊዎች የፖሊስ ኮሚሽን ባልደረባ ኢንስፔክተር  ዘላለም ስለጉዳዩ ተጠይቀው ማንንም አላሰርንም ብለዋል፡፡






Reddit!Del.icio.us!Facebook!Slashdot!Netscape!Technorati!StumbleUpon!Newsvine!Furl!Yahoo!Ma.gnolia!Free social bookmarking plugins and extensions for Joomla! websites! title=
Comments (0)Add Comment

Write comment
quote
bold
italicize
underline
strike
url
image
quote
quote
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley

security code
Write the displayed characters


busy
 

Useful Resources


Other top stories


Quick Jump

Ethio Date & Time

ዛሬ ቀኑ:

Calendar Converter




Daylight Saving