|
Wednesday, 04 February 2009 |
|
እንቆቅልሽ
ሀገር እሳት ወልዳ
ሆነና በሜዳ
ትንከራተታለች ሆነና እንግዳ
ጳጳሱ ሲቆጡ ሼሁ ማዘናቸው
ምን ይሁን ሚስጥሩ ሰዎች ከገባችሁ
ቁልቁለት ሲወርዱ አንድ መሆናቸው
ሀገር ወገን ገለው መተሳሰባቸው
ገና መች ተያዘ የሚጠብቃችው
የመኒም አይሄዱም አድዋም አይወጡም
አንድ ሆነ እርምጃቸው አይቀዳደሙም
ተያይዞ ገደል የገባ ሰው የለም
ይጀመር በነሱ ሽልማት ይሸለም
እንቆቅልሽ ፍቱ ሃይማኖት ያላችሁ
ቁልቁለት ሳትወርዱአፋፍ ላይ ቆማችሁ
ዳዊት ቁራኑንም ባለበት ይዛችሁ
ያስተሳስራችሁ አጥንቱ ደማችሁ
እንቆቅልሽ ፍቱ ሀገሬ ያላችሁ
ሼሁና ጳጳሱ ምን አግናኛቸው
ቁልቁለት ለመውረድ መደጋገፋችው
ደጋፊዎቻቸው ለምን ለቀቁዋቸው
ሽቅቡን ሲወርዱ ቁሙ ያላሉዋቸው
እንቆቅልሽ ሁነ ሰዎች ጠይቁዋቸው
ተው የሚል ሰው ጠፍቶ
ሰው እርስቱን ትቶ
አለሁኝ ይለዋል ሰው ቆሞ ሞቶ
ሽልማት በውድቀት ሆነና ዘንድሮ
ማሽነፍ ተቻለ ቁልቁል ተወዳድሮ
ደጋፊዎቻቸው ይያዙ ከበሮ
ይዘምሩላቸው ቁልቁልቅት ሲወርዱ
ሰው ካወቀባቸው ካልቀረ ማበዱ
ተከትለዋችው ቁልቁለት ይውረዱ
ሺ አመት ያንግስህ ብለው ማለታቸው
የስው ህይወት መጥፋት ያላሳሰባቸው
ካህናት ሊቃውንት የፈረዱባቸው
ምን ቢጠሉዋቸው ነው ቁልቁል የነዱአቸው
ያጠፋ ሲወቀስ አይቼ ባገሬ
የሰራም ሲወደስ አይቼ ባገሬ
ገዳይ የወደሳል ተቀይሮ ዛሬ
ጳጳሱ አጥፍቶ አበጀህ ካላቸሁ
ካህኑ አጥፍቶ ሹመት ከሰጣችሁ
የተንዥረገገው ደሙ ይክሰሳችሁ
አሁንም ደም ይፍሰስ ብለው ከተነሱ
ንጹህ ደም አይፈስም ይጀመር ከነሱ
እስላም ክርስቲያኑ ባንድ ላይ ቆማችሁ
ያባቶቻችሁን ቃልኪዳን ይዛችሁ
የውያኔን ሴራ ውዲያ ሰባብራችሁ
ኢትዩጲያን አድኑ አንድ ሆኖ ልባችሁ
yemrhane2009-02-03
ወንድወሰን ሰብስቤ england2009-02-03
|