RSS 2.0 Email us: webmaster@mahder.com

Ethiopia: Mahder.com -Ultimate Ethiopian News and Information Portal

Sunday
Aug 01st
Home arrow News arrow የኢትዮጵያ ዝምታ -ተስፋዬ ገብረአብን በተመለከተ
የኢትዮጵያ ዝምታ -ተስፋዬ ገብረአብን በተመለከተ Print E-mail
Saturday, 07 February 2009

 

የኢትዮጵያ ዝምታ -ተስፋዬ ገብረአብን በተመለከተ






Reddit!Del.icio.us!Facebook!Slashdot!Netscape!Technorati!StumbleUpon!Newsvine!Furl!Yahoo!Ma.gnolia!Free social bookmarking plugins and extensions for Joomla! websites! title=
Comments (1)Add Comment
...
written by Isaias Afewerki, February 07, 2009
ይህ ግለሰብ ከኤርትራ ክፍለ ሃገር ወደ መሃል አገር መጥተው ኑሯቸውን ከመሰረቱ ቤተሰብ በደብረዘይት ከተማ ተወልዶ አደገ። የትውልድ ሐረጉ በእናቱም በአባቱም ከትግሬ ጎሣ ሲሆን፤ የኢትዮጵያን ሰራዊት ከድቶ ወያኔን በመቀላቀል ከወያኔ ካድሬዎችና ባንዳዎች ጋር አብሮ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ላይ በተካሄደው ሴራ በከፍተኛ ደረጃ ተሳትፏል። ወያኔዎች ተስፋዬ ገብረአብ የሻቢያ ሰላይና የውስጥ አርበኛ ነው በሚል ፊት ስለነሱት በቦሌ በኩል ከአገር ሊወጣ ችሏል። የሚገርመው ካለፈው እኩይ ድርጊቱ የመማር ፍላጎትና ፀፀት አይታይበትም።

እንዲያውም ከጠዋቱ የተጠናወተውን ፀረ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ዘመቻ ለየት ባለ መልኩ ለመቀጠል በልቡ ሲሳብ ይስተዋላል።በፓልቶክ ላይ በተለያዩ ስሞች በመግባት የሻቢያና የወያኔን አርጅቶ ያፈጀና የመከነውን ፕሮፓጋንዳ ከሚያስተጋቡ ግለሰቦች አንዱ ተስፋዬ ገብረአብ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ መረዳት ይቻላል። ሰሞኑን ጓደኞቹ እነ አንዳርጋቸው ፅጌ ከለንደን በብእር ስም በኢንተርኔት ላይ በበተኑት ጽሑፍና በከረንት አፌርስ ፓልቶክ ክፍል፤ ለመጽሐፉ ሽያጭ ከፍተኛ ቅስቀሳ ተደርጓል። በተለያዩ ከተሞችም ያሉ ወኪሎቻቸውን አሰማርተው የየዋሁን ኢትዮጵያዊ ኪሥ በተስፋ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።

ፀረ ኢትዮጵያዊነት የሚያራምዱ ቡድኖችና ግለሰቦች መፅሐፍ ፃፍን በሚል ፈሊጥ እጃቸውን እያፍታቱብን እኛው ላይ የሥነ ልቦና ዘመቻ ከፍተው በሃገራችንና በሕዝባችን ሕልውና ላይ ከሚፈፅሙት ደባ በተጨማሪ ከእኛው በሚገኝ የገንዘብ ፈሰስ የቀሪ ዘመናቸውን ዓለም ናጠው ለማሳለፍ የሚያደርጉትን ከንቱ ጫወታ አንድ ደረጃ ላይ መግታት ያስፈልጋል።

አንዳርጋቸው ፅጌ ወያኔን በእምብርክኩ እየዳኸ ባገለገለበትና አብሮ ሲያፈርስና ሲዘርፍ በነበረበት ዘመን፤''አማራው ከየት ወዴት'' በሚል መጽሃፍ ተብዬው የኢትዮጵያን ታሪክ ወደ መቶ አመት ታሪክነት ሸብሽቦ ከመሳለቁም በላይ አማራው ላይ ሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ በስሜት ተነሳስቶ ጭፍጨፋ እንዲያካሄድ የአቅሙን ያህል ጥሮ እንደነበር ይታውሳል። ተስፋዬ ገብረአብ ደግሞ ከዚህን ቀደም ''በቡርቃ ዝምታ''ኦሮሞውን በአማራው ወገኑ ላይ በጥላቻ ቀስቅሶ በማስነሳት እልቂት እንዲፈጠር የጣረ የወያኔ ካድሬ ነበር።

አሁንም በዚህ ጽሑፉ ኢትዮጵያዊው ኦሮሞ ከቁምነገር ያላስገባውን ''የቡርቃ ዝምታን'' በየምእራፉ ያነሳል። ኢትዮጵያውያን አንብበው የራሳቸውን ግምት እንዲወስዱ፣ መረጃና ትዝብትም እንዲቃረምበት በሚል ሙሉ አስተያየት ከመስጠት በመቆጠብ እነሆ 400 ገጽ ያለውን ጥራዝ አቅርበናል።

http://www.4shared.com/file/84876160/5ad071c3/Tesfaye_GebreAb-Mastawesha1.html

ታዛቢወች

Write comment
quote
bold
italicize
underline
strike
url
image
quote
quote
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley

security code
Write the displayed characters


busy
 

Useful Resources


Other top stories


Quick Jump

Ethio Date & Time

ዛሬ ቀኑ:

Calendar Converter




Daylight Saving