RSS 2.0 Email us: webmaster@mahder.com

Ethiopia: Mahder.com -Ultimate Ethiopian News and Information Portal

Sunday
Aug 01st
Home arrow News arrow መቶ ሺዎቻችንን አሰልፉን!! ይቻላል!!
መቶ ሺዎቻችንን አሰልፉን!! ይቻላል!! Print E-mail
Tuesday, 10 February 2009

ከዘመድ አገኘሁ

February 10, 2009

ከሀገር ውጭ በአለም ዙሪያ የተበተናችሁ ምሁራንና ሊቃውንቶች፤ መቶ ሺዎች በአንድነት የፍትህ የዲሞክራሲና የጋራ ጥቅምን የሚያስተጋባ ድምጽ እንድናሰማ፤ ከአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ እንቅስቃሲ ለቀረበው ጥሪ፣ አቅማችሁንና እውቀታችሁን፤ አስተባብራችሁ የህዝባዊ አርነት ትግራይ የፖለቲካ ስልት አማካሪዎችን ከንቱ የመከፋፈል ጥበብን፣ እንድናሸንፍ መቶ ሺዎቻችንን እየመራችሁ፤ የአንድነት ሀይላችንን ተገንዝበን፣ ለጋራ ጥቅማችን እንድንተባበር፣ ግንባር ቀደሙን ሚና የመጫወት ሃላፌነት የኢትዮጵያ ህዝብ አደራ እለባችሁ።

 

 

ለሀገሩ ለሚቆረቆር ሲኦል በሆነቺው ሀገራችን ውስጥ የሚኖሩ ልሂቃን፤ የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ጥቅም ለሆነው ዲሞክራሲያዊ ስራት መፈጠር በጠሩት ሰላማዊ ሰልፍ፤ ሚሊዮኖችን በማሰለፍ ጥራት ባለው ሀሳብና በፖለቲካ እውቀት ምጥቀት፤ የወያኔን ደጋፊዎችን እንኳን ከጎናቸው በማሰልፍ፤ ላእላይ አስተሳሰብ እንዳላቸው፣ ሱናሚ በመባል በሚታወቀው ህዝባዊ ስልፍ ለአእለም አረጋግጠዋል።

ታዲያ የህዝባዊ ወያነ አርነት ትግራይ ጥቂት የድርጅቱ ባለቤቶች ግድያና እስራት፤ ማዋከብና ማሰፈራራት፤ በሌለበት ምድር ከሀገር ውጭ ያሉ ኢትዮጵያኖችን ጥራት ባለው አስተሳሰብ በመምራት፤ የጋራ ጥቅማችን ለሆነው ዲሞክራሲያዊ ስራት፣ ሀገሩ እንዳይገባ ከመረጠውና ከትከለከለው ኢትዮጵያዊ ጀምሮ፤ በሀገሩ ንብረት ለማደራጀት በመወሰኑ በጉቦና በከፋፍለህ ግዛው ፖለቲካ ተጠልፎ ህሊናው እስከሚሰቃየው ኢትዮጵያዊ ድረስ፤ በማሰባሰብ ትንሹን ሱናሚ አሜሪካን ዋና ከተማ እንድናደርግ ከአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ እንቅስቃሲ ለቀረበው ጥሪ አቅማችሁን እውቀታችሁን አስተባብራችሁ የአስተሳሰብ የበላይነት እንዳላችሁ የማሳየት ከፍተኛ አደራ አለባችሁ።

በታሪክ እንደተረጋገጠው የተለያዩ ሐይማኖት የሚገኝበት ሀገር፤ በተለያዩ ጎሳዎች ስብጥር የተፈጠረ ሀገር፤ የተለያዩ ቛንቛዎችን የሚያስተናግድ ሀገር፤ በጥቅሉ የታላቅነት ምልክት ሆኖ ሳለ፤ የህዝባዊ ወያን አርነት ትግራይ የድርጅቱ ቡርዡዋ ባለቤቶች ግን አንዱን የበላይ ሌላውን የበታች፤ አንዱን ምርጥ ሌላውን ምራጭ በማለት፤ ከፋፍሎ ለመግዛት ያረጀ የፖለቲካ ስልት ሲጫወቱ፤ ኢትዮጵያኖች የአንድ ሀገር ልጆች ተብለንና ሆነን፤ ለዘመናት እንዳልኖርን ሁሉ አንድ መሆን አለብን እያልን ስንጮህ አንድ ሆነን ሳለ፤ ለምንስ ባዓይናችሁ አትሰሙም፤ለምንስ ባጆሮአችሁ አታዩም ሲሉን በጆሮአችን ለማየትና በዓይናችን ለመስማት ጥረት ስናደርግ፣ እየሞተ ያለውን ፍልስፍናቸውን እንደገና እንዲያንሰራራ ደም እንደመስጠት ነው የሚቆጠረው።

በፖለቲካ ድርጅቶችና በግብረ ሰናይ ማህበራዊ ቡድን፤ እንዲሁም በተናጠል ራስን በመወከል፤ ዕንደ ጽንሰ ሀሳብ አመለካከታችውና የህይወት ፍልስፍናቸው እምነት፤ እንዲሁም የትግል ስልት ምርጫቸው፤ ኢትዮጵያውያን ልሂቃን የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም ለተወሳሰበው ችግራችን ያቅማቸውን በማበርከት የመፍተሄ አካል ለመሆን ደፋ ቀና ሲሉ፣ የወቅቱ ገዢዎች የትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት፣ የድርጅቱ ባለንብረት የሆኑት ጥቂት ግለሰቦች፣ ተቃዋሚዎች ተከፋፈሉ እነሱ አንድ ሆነው ሀገር ሊመሩ ቀርቶ እራሳቸውንም ማደራጀት አልቻሉም እያሉ የሌለ ነገር ሲያስተጋቡ እውነት ከመሰለን የስህተቶችን ሁሉ እናት እየፈጠርን ነው።

ባፍጣጠር ባህሪያቸው ወገንትኛ ወይንም partisan የሆኑትን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ልዩነትን፣ እንደማይገባና ድክመት አድርገው የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በማድረግ፣ ተቃዋሚዎች ብፍጽም አንድ መሆን አይችሉም እያሉ፤ ሊፈጠር ለማይችል ህብረት፣ ገንዘብ፣ ጉልበት፣ በተለይ በፍጹም ተመልሶ የማይገኘውን ግዜ ስናባክን፤ የኢትዮጵያውያንን የመከራ ግዜ በማራዝም፤ በአንጻሩ ለወያኔ ጋንጎች ግን ግዜ እንዲገዙ እድል እየሰጠን ነው።

ዛሪ በሀገራችን ምድር ላይ ቅጥ ባጣ ፍጹም አንባ ገነናዊ የፖለቲካ አገዛዝ፤ ማህበራዊ ህይወት በመዛባቱና ፍትህ በመጥፍቱ እንዲሁም ፀረ አንድነት ሀይሉ የመከፋፈል እቅዱ በመስመሩ በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ህጻናትና በምሊዮኖች የሚቆጠሩ አዛውንት ሃገራቸው ገሀነብ ሆናባችዋለች ነገር ግን ግፍና በደል በበዛ ቁጥር የህዝብ እንቢተኝነት እያደገና እየጎለብተ ነው የመጣው።

ረሀብ ድንቁርና በሽታና ኋላቀርነትን የሚያክሉ ጠላቶች ከዘመን ዘመን እየተሸጋገሩ የአለም ህዝብ የድሃ ምሳሌ ሲያረጉን እነዚሀን የዘመናት ጠላቶች የምንጥልበትን መሳሪያ በአስተማማኝ ሁኔታ ለመፍጠር የሚያበቃንን ዲሞክራሲያዊ ስራት ለመፍጠር የሚደረገው ትግል በመጠኑ ጥራት እያሳየ ምጥቷል።

በተለይ ከሕ ውስጥ የሚወጣው ሚስጥር ከእለት ወደእለት እየጨመረ በመምጣቱ፣ የድርጅቱ የውስጥ ፖሊሲ ሙሉ በሙሉ ጉልበት፤ ሐይል፤ ጭካኔ፤ ከሆነ ዉሎ አእድሯል፣ የሆነ ሆኖ በጣት የሚቆጠሩ የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ድርጅት ብቸኛ ባለቤቶች፣ የማጭበርበር ጥበባቸው በመንጠፉ ደጋፊዎቻቸው እንዃን እራሳቸውን ከወያኔ ሲያገልሉ በብዛት እየታየ ነው።

በጎሳ፤ በሐይማኖት፤ በፍልስፍናና፤ በሌሎችም እጅግ ባጣም ብዙ ጉዳዮች ፍፅሞ ተለያይተን ነገር ግን ዋና ዋና መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ እየተስማማን ማንም ሊቃወመው የማይችል ስምምነት ላይ በመድረሳችን ለእያንድ አንዳችን መብት፤ እኩልነትና፤ ፍትህ፤ ድምፁን የማያሰማ ኢትዮጵያዊ ያለ አይመስልም፤ ነገር ግን በእነዚሁ ጉዳይ ላይ የሊቃውንቶች፤ የምሁሮች፤ እንዲሁም የመሪዎች የአስተሳሰብ ጥራትና የአመራር ብስልት በአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ እንቅስቃሲ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ላይ በምታደርጉት ተሳትፎ የሚፈተንበት ሰአት ነው።

አንድ መቶ ሺዎች ተሰልፈን የአሜሪካንን ፖሊሲ ብናስለውጥ ተጠቃሚዎች ሁልችንም ነን።

የዚህ ሰልፍ ስኬት የትግልችንን መሰረት የመብት የእኩልነትና የፍትህ ጥይቄ እንጂ የአንድ ግሩፕ ወይም ፓርቲ ወይም ጎሳ እንቅስቃሴ አለምሆኑን የምናረጋግጥበትም ሰአት ነው።

ከመብት ከእኩልነትና ፍትህ ጥያቄ በላይ የህዝብ የጋራ ጉዳይ እንደሌለ!!

ከመብት ከእኩልነትና ፍትሕ ጥያቄ በላይ የሐይማኖት ተቛሞች የጋራ ጉዳይ እንደሌለ!!

ከመብት ከእኩልነትና ፍትሕ ጥያቄ በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ጉዳይ እንደሌለ!! ገንዘባቸውንና እውቀታቸውን የሚያፈሱት ሐገር ወዳድ ባለሐብቶች ከሁሉመ ጋር የሚጋሩት ጉዳይ ቢኖር መብት ከእኩልነትና ፍትሕ መሆኑን!!

ከመብት ከእኩልነትና ፍትህ ጥያቄ በላይ በተለያዩ ሙያ መስክ የተሰማሩ ኢትዮጵያኖች በጋር የሚነጋገሩበት የጋራ ጉዳይ አለመኖሩን!!

ከመብት ከእኩልነትና ፍትህ ጥያቄ በላይ በተለያዩ የብሄረሰብ ክፍሎች ውስጥ የጋራ ጉዳይ እንደሌለ!!

በተለይ ደግሞ ከመብት ከእኩልነትና ፍት ጥያቄ በላይ መሁሮቻችንን አንድ የሚያደርግ የጋራ ጉዳይ በዋናነት ሊጠቀስ አለመቻሉን!! የምናሳይበት ብሄራው የሰልፍ ጥሪ ነው።

ይህንን ፅሁፍ አስመለክቶ ለፀህፊው የሚሉት ካለ

This e-mail address is being protected from spam bots, you need JavaScript enabled to view it






Reddit!Del.icio.us!Facebook!Slashdot!Netscape!Technorati!StumbleUpon!Newsvine!Furl!Yahoo!Ma.gnolia!Free social bookmarking plugins and extensions for Joomla! websites! title=
Comments (0)Add Comment

Write comment
quote
bold
italicize
underline
strike
url
image
quote
quote
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley
Smiley

security code
Write the displayed characters


busy
 

Useful Resources


Other top stories


Quick Jump

Ethio Date & Time

ዛሬ ቀኑ:

Calendar Converter




Daylight Saving