|
Saturday, 25 April 2009 |
|
ለዚያ ብረቅ ኢትዩጲያዊ ለጥላአሁን ገሰሰ መታሰቢያ ትሁንልኝ
አርቆ ማሰቢያ እያለን አይምሮ
እንድምን ተሳነን ለማክበር ቀጠሮ
ሰለሞን ተሰማ ያኔ ገና ድሮ
ለዚያ ብረቅ ኢትዩጲያዊ ለጥላአሁን ገሰሰ መታሰቢያ ትሁንልኝ
አርቆ ማሰቢያ እያለን አይምሮ
እንድምን ተሳነን ለማክበር ቀጠሮ
ሰለሞን ተሰማ ያኔ ገና ድሮ
ጫጭሮ ሰቶታል እንዲሄድ ዘማምሮ
እንግዲህ ሄደብን ዘመንን ቆጣጥሮ
ጥላሁን አዚሙዋል ም እተ አመት
አንተ አንበሳ ጀግና የሀገር ኩራት
ዘንድሮ በቃኝ አልክ የፋሲካ እለት
ኪነ ጥበብ ሞተች ጥልሽ ከተታት
ጥላሁን አንጎራግር አዚም በምድሪቱ
ይውጣ ይታይልህ የታሪክ ቅሬቱ
አንተ ያዜምክለት ይታይ ነጻነቱ
ኪነ ጥበብ ጣርዛ ምሰሶ ወደቀ
የሀገሪቱ ቅሬት ተሙዋጦ አለቀ
ቴዲ አፍሮ ቀረ ወህኔ እየማቀቀ
አሙዋጠን ጨረስነው አለቀ ደቀቀ
በሰው ልብ ውስጥ አድሮ ሰው እንዲት ይሞታል
አውጥትው ካልጣሉት እንዲእት ብሎ ይወድቃል
ሰው በልቡ ይዞት እንዴት ይነጠቃል
የልብን ማህደር ማን ደፍሮ ይከፍታል
ሙት ብቻ ጨካኝ ነው ሲወስድም ያደምቃል
ለካ ከተበላ ምሰሶም ይወድቃል
በሰው መወደድም ለአምላክ ይታያል
ፍቅር ሰርቶ አዚሞ ሰዎችን አዋዱዋል
ለካስ ኑሮም ካሉት መቃብር ይሞቃል
የህገር ሀብት ወድቆ ህዝብን አስጨንቁዋል
እንግዲህ ምን እንበል ደህና ሁን ብለናል
ሞት እንኩዋን ጨክኖ ወስዶ ከሚያስቀረው
ምን አለ ደጋጉን ዳግመኛ ቢፈጥረው
ስንኝህ ብዙ ነው ማንስ ሊሰማህ
አርቲስት ነን ላሉ ህዝብን ለከዱብህ
ምን አለ ብትሄድ ዳግመኛ አዚመህ
ለኛ ብቻ አይደለም አምላክም ያይሀል
የይቅርታህ ዜማህ ዛሬም ያስተጋባል
በገነት ቢያኖርህ ሁሉም ተመኝቱዋል
መፅናኛ ትተሀል የማይሞት ትዝታ
ድምፅህ ያስተጋባል ጠዋትና ማታ
ጥላሁን ይመችህ በል እንግዲህ በርታ
ወንድወሰን ሰብስቤ
England coventery
2009 apr25
|